Course Content
ምዕራፍ አሥራ አራት : በልብ እና በደም ቧንቧ ሥርዓት አፈጣጠር ሂደት ወቅት የሚፈጠሩ የጤና ችግሮች
0/16
ምዕራፍ አሥራ አምሥት : ከልብ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ ጋር በተገናኘ የሚፈጠሩ የልብ የጤና ችግሮች (Cardiac electrical system abnormalities)
0/16
ምዕራፍ አስራ ሰባት : በልብ በሮች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Valvular heart diseases)
0/16
ምዕራፍ ሃያ አንድ : የልብ ድካምበሽታ (Heart failure )
0/1
ምዕራፍ ሃያ ሦስት : በደም ቧንቧዎች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Vascular diseases)
0/22
በልብ እና በደም ቧንቧ ሥር ዓት ክፍሎች ውስጥ ሊፈጠሪ የሚችሉ የጤና ችግሮች (Pathology of Cardiovascular System)

15.1.2.1. በሳይኖአትሪያል ኖድ ውስጥ የሚከሰት የልብ ምት መዛባት (Sinoatrial arrythmia) 

   በሳይኖአትሪያል ኖድ ውስጥ የሚከሰት የልብ ምት መዛባት በሚፈጠርበት መንገድ እንዲሁም በኤሌክትሮካርዲዮግራም  ምርመራ በሚገኘው ውጤት ላይ በመመሰረት በተለያዩ ክፍሎች ላይ ሊመደብ ይችላል። በሳይኖአትሪያል ኖድ ውስጥ ከሚከሰቱ የልብ ምት መዛባት ዓይነቶች መካከል ጤነኛ የሳይኖአትሪያል ኖድ የልብ ምት መዛባት (physiological tachyarrhythmia) ፣ የሳይኖአትሪያል የልብ ምት ፍጥነት መጨመር (sinus tachycardia) ፣ የሳይኖአትሪያል የልብ ምት ፍጥነት መቀነስ (sinus bradycardia) እና ከአትሪየም የሚነሱ የልብ ምት መዛባቶች (atrial tachyarrhythmias) ዋንኞቹ ናቸው።