Course Content
ምዕራፍ አሥራ አራት : በልብ እና በደም ቧንቧ ሥርዓት አፈጣጠር ሂደት ወቅት የሚፈጠሩ የጤና ችግሮች
0/16
ምዕራፍ አሥራ አምሥት : ከልብ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ ጋር በተገናኘ የሚፈጠሩ የልብ የጤና ችግሮች (Cardiac electrical system abnormalities)
0/16
ምዕራፍ አስራ ሰባት : በልብ በሮች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Valvular heart diseases)
0/16
ምዕራፍ ሃያ አንድ : የልብ ድካምበሽታ (Heart failure )
0/1
ምዕራፍ ሃያ ሦስት : በደም ቧንቧዎች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Vascular diseases)
0/22
በልብ እና በደም ቧንቧ ሥር ዓት ክፍሎች ውስጥ ሊፈጠሪ የሚችሉ የጤና ችግሮች (Pathology of Cardiovascular System)

16.1.2. እንቅስቃሴ በሚደረግበት ወይም በማይደረግበት ወቅት ወደ ልብ ከሚደረሰው የኦክስጂን መጠን መቀነስ ጋር በተገናኘ የሚፈጠር የደረት ህመም (Unstable angina)

  እንቅስቃሴ በሚደረግበት ወይም በማይደረግበት ወቅት ወደ ልብ ከሚደረሰው የኦክስጂን መጠን መቀነስ ጋር በተገናኘ የሚፈጠር የደረት ህመም የሚከሰተው ለረጅም ግዜ በኮሮናሪ አርተሪ ግድግዳ ላይ ሲከማች የነበረው ስብ በከፊል ከግድግዳው ላይ በሚላቀቅበት እና ከስብ ክምችቱ በተላቀቀው የኮሮናሪ አርተሪ ግድግዳ ላይ በሚፈጠረው የደም መርጋት የተነሳ የኮሮናሪ አርተሪው የበለጠ እንዲጠብ በማድረግ ወደ ልብ ሴሎች የሚደረስው የደም ፍሰት በከፍተኛ መጠን በሚቀንስበት ወቅት ነው።

      ይህ ዓይነት የልብ የጤና ችግር በሚፈጠርበት ወቅት ከፍተኛ የሆነ እና በድንገት የሚከሰት የደረት ህመም ፣ ማቅለሽለሽ ፣ ማስታወክ ፣ በላብ መጠምቅ እና የትንፋሽ ማጠር የመሳሰሉት ምልቶች እና የስሜት ለውጦች ሊከሰቱ ይችላሉ። ወደ ልብ ሴሎች የሚደረሰው የደም ፍሰት በአስቸኳይ ካልተስተካከለ ወይም ወደ ልብ ሴሎች የሚደረሰው የደም መጠን በመቀነስ ለረጅም ግዜ የሚቆይ ከሆነ በልብ ሴሎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት በማስከትል እና የልብ ሴሎች እንዲሞቱ በማድረግ ወደ ልብ ሴሎች ከሚደረሰው የኦክስጂን መጠን መቀነስ ጋር በተገናኘ የሚፈጠር የከፋ የልብ የጤና ችግር (myocardial infarction) እንዲፈጠር ሊያደርግ ይችላል።

  ይህ የጤና ችግር በሽተኛው በማንኛውም ሆኒታ ውስጥ ሆኖ ሊከሰት የሚችል የልብ የጤና ችግር ሲሆን እረፍት ማድረግ ወይም የኮርናሪ አርተሪ የደም ቧንቧ እንዲሰፋ የሚያደርጉ መድኃኒቶችን በመጠቀም የተከሰተውን በደረት ላይ የሚሰማ ህመም መቀነስ ወይም ማስታገስ አይቻልም። በዚህ የልብ የጤና ችግር ለተጠቁ በሽተኞች የኤሌክትሮካርዲዮግራም  ምርመራ እንዲሁም በልብ ሴሎች ላይ ጉዳት መድረስን ተከትሎ ከልብ ሴሎች የሚለቀቁ ከሚካሎችን መጠን ለማወቅ አስፈላጊ የሆነውን የደም ምርመራ ይሆናል። ይህ የጤና ችግር በሚከሰትበት ወቅት በኤሌክትሮካርዲዮግራም ምርመራ የ ኤስ ቲ (ST) ሴግመንት ወደ ታች ዝቅ ማለት (ST segment depression) የሚታይ ሲሆን በደም ውስጥ የሚገኙ ኬሚካሎችን ለማወቅ በሚደረግ የደም ምርመራ ደግሞ የኬሚካሎች መጠን መጠን መጨመር አይታይም። 

ይህ የልብ የጤና ችግር በሚፈጠርበት ወቅት በአፋጣኝ የህክምና ማግኘት አሰፈላጊ ሲሆን በኮሮናሪ አርተሪ መጥበብ ምክንያት በልብ ሴሎች ላይ ሊከሰት የሚችለውን ጉዳት ለመቀነስ እና ለመከላከል ከሚሰጡ ህክምናዎች መካከል በደም ውስጥ የሚኖረውን የኦክስጂን መጠን ለማሻሻል የሚረዳ ኦክስጂን ፣ የኮሮናሪ አርተሪ እንዲሰፋ እና ወደ ልብ ሴሎች የሚደርሰው የደም መጠን እንዲጨምር የሚያደርጉ መድኃኒቶችን፣ በደም ቧንቧ ውስጥ የሚከሰተውን የደም መርጋት ለመቀነስ ደም እንዲረጋ የሚያደርጉ የፕሌትሌት ሴሎች ከምችትን ለመከላከል የሚረዱ መድኃኒቶችን ፣ በደረት ላይ የሚሰማውን ህመም ለመቀነስ የሚረዱ የህመም ማስታገሻ መድኃኒቶችን ፣ የልብን ሥራ በመቀነስ የልብ ሴሎች የሚያስፈልጋቸውን የኦክስጂን መጠን የሚቀንሱ መድኃኒቶችን እና በደም ቧንቧዎች ውስጥ የተፈጠሩ የደም መርጋቶች እንዲሰባበሩ የሚያደርጉ መድኃኒቶችን መጠቀም አአፈላጊ ሊሆን ይችላል። 

     በተጨማሪም በደም ውስጥ የሚገኘውን የኮሌስትሮል እና የግሉኮስ መጠን እንዲሁም የደም ግፊት መጠንን ለመቆጣጠር የሚረዱ መድኃኒቶችን መጠቀም አስፈላጊ ሊሆን ይችላል።