22.3 በልብ ሽፋን ወይም በፔሪካርዲየም ላይ የሚከሰት ኢንፌክሽን ወይም ብግነት (Pericarditis)
በልብ ሽፋን ወይም በፔሪካርዲየም ላይ የሚከሰት ኢንፌከሽን ወይም ብግነት የሚፈጠረው በሴረስ ፒሪካርዲየም ላይ ኢንፌክሽን – አምጭ በሆኑ ህዋሳት አማካኘነት ከሚፈጠር ኢንፌክሽን ወይም በተለያዩ ምክንያቶች በፔሪካርዲየም ላይ ብግነት እንዲፈጠር ሊያደረጉ በሚችሉ ሆኔታዎች የተነሳ ነው። በፔሪካርዲየም ላይ የሚከሰት ኢንፌከሽን ብዙሁን ጊዜ የሚፈጠረው ኢንፌክሽን – አምጭ በሆኑ የተለያዩ ቫይረሶች ፣ ባክቴሪያዎች ፣ ፈንገሶች እና ሌሎች ኢንፌክሽን – አምጭ በሆኑ ተዋሲያን አማካኝነት ነው።
በልብ እና በፔሪካሪዲየም ላይ የሚፈጠር አደጋ ፣ የልብ የቀዶ ጥገና ህክምና ፣ ለጨረር መጋለጥ ፣ የተለያዩ ወደ ፔሪካርዲየም ሊሰራጩ የሚችሉ የካንሰር ዓይነቶች እንዲሁም ሥር ከሰደደ የኩላሊት በሽታ ጋር በተገናኝ በደም ውስጥ የሚገኘው የዩሪያ ናይትሮችጂን በከፍተኛ መጠን መጨመር ያሉ ሆኔታዎች በፔሪካርዲየም ላይ ብግነት እንዲፈጠር የሚያደርጉ ሆኔታዎች ናቸው።
በተጨማሪም የሰውነት የበሽታ መከላኪያ ሥርዓት የራስን የሰውነት አካል ከማጥቃት ጋር በተገናኘ የሚፈጠሩ እንደ ሎፐስ እሪተማቶሰስ (systemic lupus erythematosus) ፣ በአጥንት መገጣጠሚያዎች ላይ ጉዳት የሚያስከትል የጤና ችግር (ankylo spondylitis) ወይም የሪህ በሸታ ( gout) ያሉ የጤና ችግሮች እንዲሁም ወደ ልብ ሴሎች ከሚደረሰው የደም መጠን መቀነስ ጋር በተገናኘ የሚፈጠር የከፋ የልብ የጤና ችግር ዋንኞቹ በፔሪካርዲየም ላይ ብግነት አንዲፈጠር ሊያደርጊ የሚችሉ የጤና ችግሮች ናቸው።
እንደ ኢትዮጲያ ባሉ ታዳጊ ሀገራት ውስጥ የሳንባ ነቀርሳ በሽታ ወደ ፔሪካርዲየም በመሰራጨት የፔሪካርዲየም ብግነት እና የከፋ የልብ የጤና ችግር እንዲፈጠር ሊያደርግ ይችላል።
በፔሪካርዲየም ላይ ከሚፈጠር ኢንፌክሽን ወይም ብግነት ጋር በተገናኘ ሊከሰቱ ከሚችሉ ምልክቶች እና ለውጦች መካከል የሰውነት ሙቀት መጨመር ወይም ትኩሳት ፣ የትንፋሽ ማጠር ፣ የምግብ ፍላጎት መቀነስ ፣ የሰውነት ክብደት መቀነስ ፣ በሽተኛው ተንጋሉ በሚተኛበት ወቅት በድንገት የሚከሰት በደረት ላይ የሚሰማ የሚወጋ ህመም እና በሽተኛው ቀጥ ብሉ ወይም ወደፊት ጉንበስ ብሎ በሚቀመጠበት ወቅት ደግሞ በሚቀንስ የደረት ህመም ፣ በወስጠኛው እና በውጭኛው የሴረስ ፒሪካርዲየም መካከል በሚገኘው ክፍተት ውስጥ የሚፈጠር የፈሳሽ ክምቸት (pleural effusion) እንዲሁም የልብ ምት ድምጽ መሰማት አለመቻል ዋንኞቹ ናቸው።
በፔሪካርዲየም ላይ የሚከሰት ኢንፌክሽን ወይም ብግነት ለረጅም ግዜ በሚቆይበት ወቅት በተለይም በልብ ላይ ከሚደረግ የቀዶ ጥገና ህክምና ወይም ከሳንባ ነቀርሳ ኢንፌክሽን ጋር በተገናኘ የልብ ሽፋን መወፈር እና መጠንከር በሚፈጠርበት ወቅት የልብን ደም የመቀበል እና የመርጨት ተግባር በመገደብ የልብ ድካም በሽታን ጨምሮ የከፋ የጤና ችግር ሊያስከትል ይችላል።
በልብ ሽፋን ወይም በፔሪካርዲየም ላይ የሚከሰት ኢንፌክሽን ወይም ብግነት ለረጅም ግዜ በመቆየት በልብ ሽፋን ላይ ከሚያደርሰው ጉዳት ጋር በተገናኘ ከሚታዩ ምልክቶች እና ለውጦች መካከል በእንቅስቃሴ ወቅት የትንፋሽ ማጠር ፣ አጠቃላይ የድካም ስሜት ፣ በአንገት አካባቢ የሚገኙ የደም ቧንቧዎች መገታተር ፣ እንዲሁም በመቀመጥ እና በመነሳት ወቅት በሚደረጉ የደም ግፊት መጠን ልኬቶች ላይ ከሚጠበቀው በላይ የደም ግፊት መጠን መጨመር ለውጥ (pulsus paradoxus) መታየት ዋንኞቹ ናቸው።
በተጨማሪም በአካላዊ ምርመራ የልብ ምት ድምጸን መስማት አለመቻል ፣ በውጨኛው እና በወስጠኛው ፒሪካርዲየሞች መካክል የሚደረግ ፍትጊያ የተነሳ የሚፈጠር ድምጽ (friction rub) መሰማት እንዲሁም በ ኤሌክትሮካርዲዮግራም (ECG) ምርመራ ደግሞ በተለያዩ ሊዶች ላይ የሚታይ የ ኤስ ቲ ( ST) ሴግመንት ከፍ ማለት (ST segment elevation) እና የ ፒ አር (PR) ሴግመንት ዝቅ ማለት (PR depression) ሊታዩ ይችላል። በኢኮካርዲዮግራምም ምርመራ የልብ ሽፋን መወፈር እንዲሁም በልብ ሽፋን ላይ የተከማቸ ካልሲየም ሊታይ ይችላል።