Course Content
ምዕራፍ አሥራ አራት : በልብ እና በደም ቧንቧ ሥርዓት አፈጣጠር ሂደት ወቅት የሚፈጠሩ የጤና ችግሮች
0/16
ምዕራፍ አሥራ አምሥት : ከልብ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ ጋር በተገናኘ የሚፈጠሩ የልብ የጤና ችግሮች (Cardiac electrical system abnormalities)
0/16
ምዕራፍ አስራ ሰባት : በልብ በሮች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Valvular heart diseases)
0/16
ምዕራፍ ሃያ አንድ : የልብ ድካምበሽታ (Heart failure )
0/1
ምዕራፍ ሃያ ሦስት : በደም ቧንቧዎች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Vascular diseases)
0/22
በልብ እና በደም ቧንቧ ሥር ዓት ክፍሎች ውስጥ ሊፈጠሪ የሚችሉ የጤና ችግሮች (Pathology of Cardiovascular System)

15.1.3. ከአትሪየም ውስጥ የሚነሱ የልብ ምት መዛባትቶች  (Atrial tachyarrhythmias)

   ከአትሪየም ውስጥ የሚነሱ የልብ ምት መዛባቶች የሚፈጠሩት በአትሪየም ውስጥ በሚያልፈው ወይም በሚፈጠረው የልብ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ ላይ እክል በሚያጋጥምበት ወቅት ነው። በእትሪየም ውስጥ የሚከሰት የልብ ምት መዛባቶች የሚፈጠሩት በአትሪየም ውስጥ የሚገኙ ሴሎች ከሳይኖአትሪያል ኖድ በላይ በሆነ ፍጥነት የልብን የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ መፍጠር እና መምራት በሚጀምሩበት ወቅት ነው።  

   በአትሪየም ውስጥ ከሚነሱ የልብ ምት መዛባት ዓይነቶች መካከል በእትሪየም ውስጥ የሚነሳ የልብ ምት ፍጥነት መጨመር (Atrial tachycardia) ፣ የአትሪየም ፍልተር (Atrial flutter) እና የአትሪየም ፊብሪሌሽን  (atrial fibrillation) ዋንኞቹ ናቸው።