16.1.3. የፕሪንዝሜታል የደረት ህመም (Prinz metal angina)
የፕሪንዝሜታል የደረት ህመም በኮሮናሪ አርተሪ ግድግዳ ጡንቻ ላይ በሚከሰት ድንገተኛ መኮማተር የተነሳ የኮሮናሪ አርተሪ እንዲጠብ እና ወደ ልብ ሴሎች የሚደረሰው የደም መጠን እንዲቀንስ በማድረግ በልብ ሴሎች ላይ ጉዳት በማስከተል በደረት ላይ የሚሰማ ህምም እንዲሁም ሌሎች ምልክቶች እና የስሜት ለውጦች እንዲከሰቱ የሚያደርግ የጤና ችግር ነው።
ይህ የጤና ችግር አንድ አንድ ግዜ በኮሮናሪ አርተሪ ግድግዳ ላይ ከሚፈጠር የስብ ክምችት ጋር በተገናኘ ሊከሰት ቢችልም ከመላምቶች ባለፈ ለምን እና እንዴት የኮሮናሪ አርተሪ ግድግዳ ጡንቻ መኮማተር እንደሚከሰት በትክክል አይታወቅም። የፕሪንዝሜታል የደረት ህመም በማንኛውም ግዜ እና ሆኒታ ውስጥ ሊከሰት የሚችል የልብ የጤና ችግር ሲሆን ብዙሁን ግዜ በሴቶች ፣ ሲጋራ በሚያጤሱ እና የአልኮል መጠጥ በበዛት በሚውስዱ ሰዎች ላይ ይከሰታል።
የካልሲየም ተቀባዩችን የሚዘጉ መድኃኒቶችን (calcium channel blockers) በመጠቀም ከፕሪንዝሜታል የደረት ህምም ጋር በተገናኝ የሚከሰቱ ምልክቶችን እና የስሜት ለውጦችን ማከም ይቻላል። የካልሲየም ተቀባዩችን የሚዘጉ መድኃኒቶች የደም ቧንቧዎች እንዲሰፉ የሚያደረጉ መድኃኒቶቸ ናቸው።
የፕሪንዝሜታል የደረት ህመም በሽተኞችን ወደ ልብ ከሚደረሰው የኦክስጂን መጠን መቀነስ ጋር በተገናኘ ለሚፈጠር የከፋ የልብ የጤና ችግር ተጋላጭ ሊያደርጋቸው ይችላል። ስለሆነም በሽተኞች ሆኔታዎችን ለማስተካከል አስቸኳይ ህክምና ማግኘት ፣ በደም ቧንቧዎች ውስጥ ለሚፈጠር የደም መርጋት ፣ በኮሮናሪ አርተሪ ግድግዳ ላይ ለሚፈጠር የስብ ክምችት እና ለልብ ምት መዛባት አጋላጭ የሆኑ ሆኔታዎችን ማስወገድ ይኖርባቸዋል።