23.2.1.3. በትንንሽ የደም ቧንቧዎች ግድግዳ ላይ የሚከሰት ብግነት
በትንንሽ የደም ቧንቧዎች ግድግዳ ላይ የሚከሰት ብግነት ወይም ቁስለት እንዲፈጠር ከሚያደርጉ የጤና ችግሮች መካከል ግራኖሎማ የሚሰራ የደም ቧንቧዎች ግድግዳ ብግነት ወይም የዌገነር በሽታ (Granulomatosis with polyangiitis / Wegener) ፣ ከኢኦዚኖፊሊክ ሴሎች ጋር ግራኖሎማ የሚሰራ የደም ቧንቧ ግድግዳ ብግነት (Eosinophilic Granulomatosis with Polyangiitis EGPA / Churg – Strauss) በሽታ እንዲሁም የራይናውድስ በሽታ (Raynaud’s disease and Raynaud phenomenon) ዋንኞቹ የጤና ችግሮች ናቸው። ግራኖሎማ ማለት በተወሰነ የሰውነት ክፍል ላይ የሚፈጠር ቁስለት ሲሆን ችግሩ በሚፈጠርበት ክፍል ላይ በቀላሉ የሚደሙ በጣም ትንንሽ የሆን የደም ቧንቧዎች እንዲፈጠሩ ፣ ዕብጠት እንዲታይ እንዲሁም ህምም እንዲከሰት የሚያደርግ የጤና ችግር ማለት ነው።