23.3.1. በፑልሞናሪ አርተሪ ውስጥ የሚገኘው የደም ግፊት መጠን መጨመር (Pulmonary artery hypertension)
ይህ የጤና ችግር ደምን ከግራ ቬንትሪክል ወደ ሳንባ በሚወስዱ የፑልሞናሪ አርተሪዎች ውስጥ የሚፈጠር የግፊት መጠን መጨመር የተነሳ የሚከሰት የጤና ችግር ነው። በፑልሞናሪ አርተሪ ውስጥ የሚገኘው የደም ግፊት መጠን መጨመር የጤና ችግር እንዲፈጠር ሊያደርጉ ከሚችሉ ሆኔታዎች መካከል በሳንባ እና በአየር ቧንቧ ሥርዓት ውስጥ የሚከሰቱ እና ለረጅም ግዜ የሚቆዩ የጤና ችግሮች ፣ የሰውነት የበሽታ መከላኪያ ሴሎች እና ከሰውነት የበሽታ የመከላከያ ሴሎች የሚመረቱ ፕሮቲኖች በልብ እና በሳንባ መካከል በሚገኙ የደም ቧንቧዎች ላይ በሚያደርሱት ጉዳት እንዲሁም በግራ የልብ ክፍል ውስጥ የሚፈጠር የልብ ደካም ዋንኞቹ ምክንያቶች ናቸው። አንድ አንድ ጊዜ ምክንያቱ በማይታውቅ ምክንያት የፑልሞናሪ አርተሪ ውስጥ የሚኖረው የደም ግፊት መጠን ሊጨምር ይችላል።