Course Content
ምዕራፍ አሥራ አራት : በልብ እና በደም ቧንቧ ሥርዓት አፈጣጠር ሂደት ወቅት የሚፈጠሩ የጤና ችግሮች
0/16
ምዕራፍ አሥራ አምሥት : ከልብ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ ጋር በተገናኘ የሚፈጠሩ የልብ የጤና ችግሮች (Cardiac electrical system abnormalities)
0/16
ምዕራፍ አስራ ሰባት : በልብ በሮች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Valvular heart diseases)
0/16
ምዕራፍ ሃያ አንድ : የልብ ድካምበሽታ (Heart failure )
0/1
ምዕራፍ ሃያ ሦስት : በደም ቧንቧዎች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Vascular diseases)
0/22
በልብ እና በደም ቧንቧ ሥር ዓት ክፍሎች ውስጥ ሊፈጠሪ የሚችሉ የጤና ችግሮች (Pathology of Cardiovascular System)

15.1.2. የልብ ምት መዛባት አፈጣጠር (cardiac arrhythmia)   

            በተለያዩ የልብ ክፍሎች ውስጥ በሚኖረው የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ ላይ እክል በመፍጠር ለሚከሰት የልብ ምት መዛባት መንስሄ የሚሆኑት በዋነኝነት ሦስት ሆኔታዎች ናቸው። ከእነዚህም ሦስት ሆኔታዎች መካከል በልብ ውስጥ የሚገኙ እና ያለምንም ውጪያዊ ጫና የልብ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴን መፍጠር እና መምራት የሚችሉ ሴሎች የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴን የመፈጠር እና የመምራት አቅም መጨመር (increased automaticity)  አንዱ ሲሆን ሁለተኛው መንገድ ደግሞ የልብ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴን መፍጠር እና መምራት በማይችሉ ተኮማታሪ የልብ ሴሎች ውስጥ በሚፈጠሩ የጤና ችግሮች የተነሳ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴን የመፍጠር እና የመምራት አቅም መፈጠር (triggered automaticity) ነው። 

  ሦስተኛው የልብ ምት መዛባት እንዲፈጠር የሚያደርገው ሆኔታ የልብ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ ባልተገባ መልኩ ከትክክለኛው የፍሰት መስመር በመውጣት ከተለያዩ የልብ ክፍሎች ጋር በሚፈጥረው ግንኙነት የተነሳ ወይም የልብ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ ፍሰት በተለያዩ የልብ ክፍሎች ውስጥ በሚኖረው ያልተገባ ግንኙነት የተነሳ በአንድ የተወሰነ የልብ ክፍል ውስጥ የልብ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ መሽከርከር (circus movement) ነው።

 በአጠቃላይ ከላይ በተገለጹት ሆኔታዎች እና በሌሎችም ምክንያቶች የተዛባ የልብ ምት ወይም ጤነኛ ያለሆነ የልብ ምት ሊፈጠር ይችላል። የልብ ምት በሚፈጠርበት መንገድ ፣ በሚፈጠርበት የልብ ክፍል እና በኤልክትሮካርዲዮግራም ምርመራ በሚገኘው ውጤት መሰረት ጤነኛ ያልሆነ የልብ ምት ወይም የልብ ምት መዛባት በተለያዩ ምድቦች ሊከፈል ይችላል።