15.1.2.4. የሳይኖአትሪያል የልብ ምት ፍጥነት መቀነስ (sinus bradycardia)
የሳይኖአትሪያል የልብ ምት ፍጥነት መቀነስ የሚፈጠረው በሳይኖአትሪያል ኖድ ላይ በሚከሰት እክል ወይም በሳይኖአትሪያል ኖድ ላይ ተፅህኖ በማሳደር የልብን የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ የመፍጠር እና የመምራት አቅም በሚቀንሱ ሆኔታዎች የተነሳ የልብ ምት ፍጥነት በደቂቃ ከ 60 በታች ሆኖ ሲገኝ ነው።
ለረጅም ግዜ አካላዊ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ሰዎች ፣ በደም ውስጥ የሚገኘው የታይሮይድ ሆርሞን መጠን መቀነስ ፣ የሰውነት ሙቀት ከሚገባው በታች መቀነስ እንዲሁም የሲምፓተቲክ የነርቭ ሥርዓትን ተግባር የሚገድቡ ወይም የፓራሲምፓተቲክ የነርቭ ሥርዓትን ተግባር የሚያቀላጥፉ የተለያዩ መድኃኒቶች የሳይኖአትሪያል የልብ ምት ፍጥነት መቀነስ እንዲከሰት ከሚያደርጉ ሆኔታዎች መካከል ጥቂቶቹ ናቸው።
የሳይኖአትሪያል የልብ ምት ፍጥነት መቀነስ በሚከሰትበት ወቅት በኤሌክትሮካርዲዩግራም ምርመራ ውጤት ላይ በ አር ( R ) ሞገዶች መካከል የሚኖረው ርቀት የሚጨምር እና አያንድ አንዱ የ ኪው አር ኤስ (QRS) ኮምፕሌክስም የ ፒ (P) ሞገድን ተከትሎ የሚከሰት ይሆናል።