15.1.3. ከአትሪየም ውስጥ የሚነሱ የልብ ምት መዛባትቶች (Atrial tachyarrhythmias)
ከአትሪየም ውስጥ የሚነሱ የልብ ምት መዛባቶች የሚፈጠሩት በአትሪየም ውስጥ በሚያልፈው ወይም በሚፈጠረው የልብ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ ላይ እክል በሚያጋጥምበት ወቅት ነው። በእትሪየም ውስጥ የሚከሰት የልብ ምት መዛባቶች የሚፈጠሩት በአትሪየም ውስጥ የሚገኙ ሴሎች ከሳይኖአትሪያል ኖድ በላይ በሆነ ፍጥነት የልብን የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ መፍጠር እና መምራት በሚጀምሩበት ወቅት ነው።
በአትሪየም ውስጥ ከሚነሱ የልብ ምት መዛባት ዓይነቶች መካከል በእትሪየም ውስጥ የሚነሳ የልብ ምት ፍጥነት መጨመር (Atrial tachycardia) ፣ የአትሪየም ፍልተር (Atrial flutter) እና የአትሪየም ፊብሪሌሽን (atrial fibrillation) ዋንኞቹ ናቸው።