Course Content
ምዕራፍ አሥራ አራት : በልብ እና በደም ቧንቧ ሥርዓት አፈጣጠር ሂደት ወቅት የሚፈጠሩ የጤና ችግሮች
0/16
ምዕራፍ አሥራ አምሥት : ከልብ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ ጋር በተገናኘ የሚፈጠሩ የልብ የጤና ችግሮች (Cardiac electrical system abnormalities)
0/16
ምዕራፍ አስራ ሰባት : በልብ በሮች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Valvular heart diseases)
0/16
ምዕራፍ ሃያ አንድ : የልብ ድካምበሽታ (Heart failure )
0/1
ምዕራፍ ሃያ ሦስት : በደም ቧንቧዎች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Vascular diseases)
0/22
በልብ እና በደም ቧንቧ ሥር ዓት ክፍሎች ውስጥ ሊፈጠሪ የሚችሉ የጤና ችግሮች (Pathology of Cardiovascular System)

15.1.4. በአትሪየም እና በቬንትሪክል መገናኛ መካከል የሚነሳ የልብ መዛባት (Junctional arrhythmia)

  ከአትሪዩቬንትሪኪዩላር ኖድ ውጭ በአትሪየም እና በቬንትሪክል መካከል የሚገኘው ክፍል የተሰራው የኤሌክትሪክ እንቅስቅሴን ከአትሪየም ወደ ቬንትሪክል ውስጥ ማሳለፍ በማይችል ክፍል ነው። ስለሆነም በሳይኖአትሪይል ኖድ ውስጥ የሚፈጠረው የልብ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ ወደ ቬንትሪክል ውስጥ ማለፍ የሚችለው በአትሪዩቬንትሪኪዩላር ኖድ በኩል ብቻ ነው። በሳይኖአትሪያል ኖድ ውስጥ የሚፈጠረው የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ በአትሪየም ውስጥ በሚገኙ ሴሎች ውስጥ አልፎ ወደ አትሪዩቬንትሪኪዩላር ኖድ ውስጥ ይገባል። 

    የአትሪዩቬንትሪኪዩላር ኖድ ከአትሪየም የሚመጣውን የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ ለጥቂት ሰከንዶች ( 0.1 ሰከንዶች) እንዲዘገይ ካደረገ በኋላ የኤሌክትሪክ እንቅስቅሴን ወደ ዋና የልብ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ ማሳለፊያ  መንገድ (Bundle of His) የሚያሻገር የልብ የኤሌክትሪክ ሥርዓት ክፍል ነው።     በአትሪዩኦቬንትሪኪዩላር ኖድ በኩል የሚያልፈው እና በዋና የልብ ኤሌክትሪክ አንቅስቃሴ ማሳለፊያ መንገድ ውስጥ የሚደረሰው የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ በፍጥነት በቀኝ እና በግራ የልብ የ ኤልክትሪክ ሥርዓት ማሳላፊያዎች በኩል አልፎ በፑርኪንጂ ደሮች አማካኝነት ወደ ቬንትሪክል ተኮማታሪ ሴሎች ጋር የሚደርስ ይሆናል። በአትሪዩቬንትሪኪዩላር ኖድ ውስጥ የሚገኙ ሴሎች የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴን የሚያሳልፉበት ፍጥነት ከሌሎች የልብ ሴሎች ጋር ሲነጻጻር በጣም የዘገየ ነው። ይህም መዘግየት ለአትሪየም መኮማተር እና ለቬንትሪክል መለጠጥ የሚያስፈልገውን በቂ ግዜ ለመስጠት በጣም ወሳኝ ነው።

  በአትሪዩቬንትሪኪዩላር ኖድ ላይ ተጽህኖ የሚያሳድሩ የተለያዩ ሆኔታዎች የአትሪዩቬንትሪኪዩላር ኖድ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴን የማሳለፍ ብቃት እንዲጨምር ወይም እንዲቀንስ ሊያደርጉ ይችላሉ። በአትሪዩቬንትሪኪዩላር ኖድ ላይ ተጽህኖ በማስከትል የልብ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ እንዲጨምር የሚያደርግ ሆኔታ ጀንክሽናል የልብ ምት ፍጥነት መጨመር የሚያስከትል የልብ ምት መዛባት (Junctional thacyarrythemia) ተብሎ ይጠራል። በአትሪዩቬንትሪኪዩላር ኖድ ላይ ተጽህኖ በማስከትል የአትሪዩቬንትሪኪዩላር ኖድ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴን የማሳለፍ ብቃት እንዲቀንስ እና የልብ ምት ፍጥነት እንዲቀንስ የሚያደርግ ሆኔታ ደግሞ  ጀንክሽናል የልብ ምት ፍጥነት እንዲቀንስ የሚያደርግ የልብ ምት መዛባት (junctional brady arrhythmia) ተብሎ ይጠራል።

 የአትሪዩቬንትሪኪዩላር ኖድን የሚሰሩት የአትሪዩቬንትሪኪዩላር ሴሎች በጣም ትንንሽ መሆን ፣ በአትሪዩቬንትሪኪዩላር ሴሎች ላይ የሚገኙ የጋፕ ጀንክሽኖች ቁጥር አነስተኛ መሆን እንዲሁም በአትሪዩቬንትሪኪዩላር ሴሎች ውሰጥ የሚገኘው የረስቲንግ ሜምብሬን መጠን በጣም ወደ ነጊቲቭ የተጠጋ ከመሆኑ የተነሳ በአትሪዩቬንትሪኪዩላር ኖድ ውስጥ የሚኖረው የኤሌክትሪክ እንቅሰቃሴ ፍሰት በጣም የዘገየ ይሆናል። 

   በኤሌክትሮካርዲዮግራም ምርመራ ውጤት ላይ የሚታየው የ ፒ አር (PR) ሴግመንት የልብ የኤሌክትሪክ እቅስቃሴ በአትሪዩቬንትሪኪዩላር ኖድ ውስጥ ለማለፍ የሚፈጅበትን ግዜ የሚያመለክት ነው። የ ፒ አር (PR) ሴግመንት ርዝመት በሚጨምርበት ወቅት የ ፒ አር (PR) ርቀት ስለሚጨምር የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ በአትሪዩቬንትሪኪዩላር ኖድ ውስጥ ለማለፍ የሚወስደብት የግዜ መጠን በ ፒ አር (PR) ሴግመንት ወይም በ ፒ አር (PR)  ርቀት መጠን የሚለካ ይሆናል። በዚህም መሠረት በአትሪዩቬንትሪኪዩላር ኖድ ውስጥ የሚያልፈው የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ ፈጣን በሚሆንበት ወቅት የ ፒ አር (PR)  ርቀት አጭር  (short PR Interval)  የሚሆን ሲሆን በአትሪዩቬንትሪኪዩላር ኖድ ውስጥ የሚያልፈው የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ የዘገየ በሚሆንበት ወቅት ደግሞ  የ ፒ አር (PR) ርቀት የረዘም ይሆናል። 

   በአትሪዩቬንትሪኪዩላር ኖድ ውስጥ የሚኖረውን የልብ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ ፈጣን አንዲሆን ከሚያደርጉ ሆኔታዎች መካከል የሲምፓተቲክ የነርቭ ሥርዓት በአትሪዩቬንትሪኪዩላር ኖድ ላይ የሚያሳድረው ተጽህኖ መጨመር ፣ ከፍተኛ መጠን ያለው ቡና መጠጣት ወይም በቤታ አንድ ተቀባዩች ላይ ተጽህኖ የሚያሳድሩ መድኃኒቶች እና የመሳሰሉት ሆኔታዎች ዋንኞቹ ሲሆኑ በአትሪዩቬንትሪኪዩላር ኖድ ውስጥ የሚያልፈው የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ የዘገየ እንዲሆን ከሚያደርጉ ሆኔታዎች መካከል ደግሞ የፓራሲምፓተቲክ የነርቭ ሥርዓት መነቃቃት ወይም የፓራሲምፓተቲክ የነርቭ ሥርዓት እንዲነቃቃ የሚያደርጉ ነገሮች እና ሆኔታዎች ፣ የቤታ አንድ በሮችን የሚዘጉ መድኃኒቶች (beta 1 blockers) ፣ የካልሲየም በሮችን የሚዘጉ መድኃኒቶች (calcium channel blockers) እና የዲጂታሊስ መደኃኒት (digitalis)  ዋንኞቹ ናችው።