Course Content
ምዕራፍ አሥራ አራት : በልብ እና በደም ቧንቧ ሥርዓት አፈጣጠር ሂደት ወቅት የሚፈጠሩ የጤና ችግሮች
0/16
ምዕራፍ አሥራ አምሥት : ከልብ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ ጋር በተገናኘ የሚፈጠሩ የልብ የጤና ችግሮች (Cardiac electrical system abnormalities)
0/16
ምዕራፍ አስራ ሰባት : በልብ በሮች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Valvular heart diseases)
0/16
ምዕራፍ ሃያ አንድ : የልብ ድካምበሽታ (Heart failure )
0/1
ምዕራፍ ሃያ ሦስት : በደም ቧንቧዎች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Vascular diseases)
0/22
በልብ እና በደም ቧንቧ ሥር ዓት ክፍሎች ውስጥ ሊፈጠሪ የሚችሉ የጤና ችግሮች (Pathology of Cardiovascular System)

15.1.5 በቬንትሪክል ውስጥ የሚከሰት የልብ ምት መዛባት (ventricular arrhythmia) 

በቬንትሪክል ውስጥ የሚከሰት የልብ ምት መዛባት የሚፈጠረው በዋናነት በተወሰነ የቬንትሪክል ከፍል ውስጥ የሚገኙ የቬንትሪክል ሴሎች ባልተገባ መልኩ የልብ ኤሊከትሪክ እንቅስቃሴን መፍጠር እና መምራት በሚጀምሩበት ወቅት ነው። ይህ ሆኔታ እንዲፈጠር ከሚያደርጉ ሆኔታዎች መካከል  በቬንትሪክል ሴሎች ውስጥ የሚገኘው የረስቲንግ ሜምብሬን ፖቴንሺያል መጠን ወደ ፖዘቲቨ የተጠጋ እንዲሆን የሚያደረጉ ሆኔታዎች ናቸው። ለምሳሌ ፡ ለልብ ሴሎች ከሚደረሰው የኦክስጂን መጠን መቀነስ ጋር በተገናኘ በቬንትሪክል ሴሎች ላይ ጉዳት በሚከሰትበት ወቅት በሴሎች ሽፋን ላይ የሚፈጠረውን ጉዳት ተከትሎ ወደ ሴሎች ውስጥ የሚገባውን የሶዲየም አዮን ተከትሎ የቬንትሪክል ሴሎች በቀላሉ እና በፍጥነት  ትሪሾልድ ሚምብሬን ላይ የሚደርሱበት ሆኔታ ሊፈጠር ይችላል።  ይህም ሆኔታ የቬንትሪክል ሴሎች በፍጥነት አክሽን ፖቲንሺያል በመፍጠር የልብን የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴን መፍጠር እና መምራት እንዲችሉ ያደርጋል። 

   በኮሮናሪ አርተሪዎች ላይ በሚፈጠር ጉዳት የተነሳ ወደ ልብ ሴሎች ከሚደርሰው የደም ወይም የኦክስጂን መጠን መቀነስ ጋር በተገናኘ የሚፈጠር የልብ የጤና ችግር በቬንትሪክል ውስጥ ለሚነሱ የልብ ምት መዛባቶችን በመፍጠር  ዋንኛ የሞት መንስሄ ሊሆን ይችላል። 

በቬንትሪክል ውስጥ የሚከሰት የልብ ምት መዛባት በሚፈጠርበት ወቅት በኤሌክትሮካርዲዩግራም ምርመራ ውጤት ላይ የ ኪው አር ኤስ (QRS) ኮምፕሌክስ መስፋትን የሚያስከትል ሲሆን በቬንትሪከል ውሰጥ የሚፈጠረው የልብ ምት መዛባት አልፎ አልፎ የሚከሰትበት ሆኔታ በድንገት በቬንትሪክል ውስጥ የሚከሰት የልብ ምት መዛባት (Ventricular premature beat)  ተብሎ ይጠራል። 

በሌላ መልኩ በቬንትሪክል ውስጥ የሚከሰት የልብ ምት መዛባት በሚፈጠርበት ወቅት በኤሌክትሮካርዲዩግራም ምርመራ በተደጋጋሚ እና አንድ ዓይነት በሆነ መንገድ የሚከሰት የ ኪው አር ኢስ (QRS) ኮምፕሌክስ መስፋት  መታየት እንዲሁም በተከታታይ በሚታዩ የ አር  ( R ) ሞገዶች መካከል የሚኖረው ርቀት አኩል ሆኖ የሚገኝበት በቬንትሪክል ውስጥ የሚከሰት የልብ ምት መዛባት ዓይነት  በቬንትሪክል ውስጥ የሚከሰት የልብ ምት ፍጥነት እንዲጨምር የሚያደርግ የልብ ምት መዛባት (ventricular tachycardia) ተብሎ ይጠራል።

 በተወሰነ የቬንትሪክል ክፍል ውስጥ በሚፈጠር የኤሌከትሪክ እንቅስቃሴ የተነሳ በቬንትሪክል ውስጥ የሚከሰት የልብ ምት መዛባት በሚፈጠርበት ወቅት በኤሌክትሮካርዲዩግራም ምርመራ ውጤት ላይ ተመሳሳይ የሆነ በተደጋጋሚ የሚታይ የፍልተር ሞገድ ( ትከክለኛውን የኪው አር ኮምፕሌክስ (QRS) ኮምፕሌክስ የማይመስል) የሚከሰትበት ሆኔታ የቬንትሪክል ፍልተር (ventricular flutter) ተብሎ ይጠራል።

  ከቬንትሪክል ፍልተር ጋር በተገናኘ በኤልክትሮካርዲዩግራም ምርመራ ውጤት ላይ የፍልተር ሞገድ የሚታይ ሲሆን በደቂቃ ከ 250 እስከ 350 የሚደርስ የልብ ምት ፍጥነት መጨመር እንዲከሰት ያደርጋል። በዚህ ዓይነት የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ የቬንትሪክል ጡንቻ በማኮማተር በበቂ መጠን ደምን መርጨት ስለማይቻል በቬንትሪክል ፍልተር የተጠቁ  በሽተኞች የተፈጠረውን የልብ ምት መዛባት ለማስተካከል አስቸኳይ ህክምና ማግኘት ይኖርባቸዋል። የቬንትሪክል ፍልተር ያለምንም ህክምና ለጥቂት ግዜ በሚቆይበት ወቅት ለሰውነት የሚረጨው የደም መጠን ከመቀነስ በተጨማሪ ወደ ልብ የሚደረሰው የደም መጠን በከፍተኛ መጠን እንዲቀንስ ሊያደርግ ይችላል። 

  ለልብ ሴሎች የሚደረሰው የደም ወይም የኦክስጂን መጠን በሚቀንስበት ወቅት በብዙ የቬንትሪክል ክፍሎች ላይ በሚገኙ የልብ ሴሎች ላይ የሚያስከትለውን ጉዳት ተከትሎ ወደ ሴሎች ውስጥ በሚገባው የሶዲየም አዮን መጠን መጨመር የተነሳ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴን በራሳቸው መፍጠር እና መምራት የሚችሉ አያሌ የልብ ሴሎች የሚፈጠሩ ይሆናል። ከእነዚህ ሴሎች የሚነሱ እና በተለያዩ አቅጣጫዎች የሚሰራጨው የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ የልብን የመኮማተር እና የመለጠጥ ሂደት የተዛባ ወይም የተዘበራረቀ እንዲሆን ስለሚያደርጉ የቬንትሪክል ፊብሪሌሽን (ventricular fibrillation) ተብሎ የሚጠራው ለሞት ሊያደርስ የሚችል የልብ ምት መዛባት የጤና ችግር የሚፈጠር ይሆናል። የቬንትሪክል ፊብሪሌሽን በፍጥነት ካልታከመ በድንገት ለሞት የሚያደርስ የጤና ችግር ነው።