Course Content
ምዕራፍ አሥራ አራት : በልብ እና በደም ቧንቧ ሥርዓት አፈጣጠር ሂደት ወቅት የሚፈጠሩ የጤና ችግሮች
0/16
ምዕራፍ አሥራ አምሥት : ከልብ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ ጋር በተገናኘ የሚፈጠሩ የልብ የጤና ችግሮች (Cardiac electrical system abnormalities)
0/16
ምዕራፍ አስራ ሰባት : በልብ በሮች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Valvular heart diseases)
0/16
ምዕራፍ ሃያ አንድ : የልብ ድካምበሽታ (Heart failure )
0/1
ምዕራፍ ሃያ ሦስት : በደም ቧንቧዎች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Vascular diseases)
0/22
በልብ እና በደም ቧንቧ ሥር ዓት ክፍሎች ውስጥ ሊፈጠሪ የሚችሉ የጤና ችግሮች (Pathology of Cardiovascular System)

  16. ከኮሮናሪ አርተሪ ጋር በተገናኘ የሚከሰቱ የልብ  የጤና ችግሮች (Coronary artery diseases) 

   ልብ የሚጠበቅበትን ተግባር በትክክል መፈጸም እንዲችል የሚያስፈልገውን የኦክስጂን ወይም የደም መጠን  የሚያገኘው በኮሮናሪ አርተሪዎች በኩል ነው። ከትልቁ ደም ቅዳ ቧንቧ ላይ የሚነሱት የቀኝ እና የግራ የኮሮናሪ አርተሪዎች ወደ ተለያዩ የኮሮናሪ አርተሪ ቅርንጫፎች በመቀየር እና ወደ ተለያዩ የልብ ክፍሎች ውስጥ በመድረስ የልብ ሴሎች የሚያስፈልጋቸውን የደም ወይም የኦክሰጂን መጠን እንዲያገኙ ያደርጋሉ።

 የቀኝ ኮሮናሪ አርተሪ ደምን በአብዛኛው በቀኝ በኩል ለሚገኘው የልብ ክፍል የሚያደርስ ሲሆን የግራ ኮሮናሪ አርተሪ ደግሞ ለአብዛኛው ለግራ የልብ ክፍሎች ደም እንዲደርስ ያደርጋል።

ልብ የሚፈለግበትን የደም መርጨት ተግባር ያከናውን ዘንድ ከሌሎች የሰውነት ክፍሎች በተለየ ሆኔታ ክፍተኛ መጠን ያለው ሃይል ያስፈልገዋል። የልብ ሴሎች ሃይልን የማከማችተ ብቃት ስለሌላቸው የሚያስፈልጋቸውን ሃይል ለማግኘት የማያቋርጥ የኦክስጂን እና የንጥረምግቦች ወይም የደም ፍሰት አቅርቦት ማግኘት ያስፈልጋቸዋል። 

   አንደ ተቀረው የሰውነት ክፍል ሁሉ ወደ ልብ የሚደረሰው የደም መጠን በኮሮናሪ አርተሪዎች ውስጥ በሚገኘው የደም ግፊት መጠን እና በኮሮናሪ አርተሪዎች ውስጥ በሚገኘው የግድብት መጠን ላይ ይወሰናል። በኮሮናሪ አርተሪዎች ውስጥ የሚኖረው የደም ግፊት መጠን ሲቀንስ ወይም በኮሮናሪ አርተሪዎች ውስጥ የሚኖረው የግደብት መጠን ሲጨምር ወደ ልብ ሴሎች የሚደረሰው የደም መጠን የሚቀንስ ይሆናል። በተጨማሪም ወደ ልብ የሚደርሰው የደም መጠን ወይም የደም ፍሰት ከልብ ሴሎች በሚለቀቁ እና የኮሮናሪ አርተሪዎችን መስፋት እና መጥበብ በሚቁጣጠሩ ኬሜካሎች መጠን ላይ የሚወሰን ነው። 

      የልብ ጡንቻ ከፍተኛ ሥራ በሚሰራበት ወቅት በልብ ሴሎች ውስጥ የሚመረቱ እንደ ፖታሲየም ፣ አይድሮጂን ፣ ካርቦንዳይኦክሳይድ ፣ ናይትሪክኦክሳይድ ፣ ፕሮሰታግላንዲን እና እዲኖሲን ያሉ ሆርሞኖች እና ኬሚካሎች መጠን በከፍተኛ መጠን ይጨምራል። የእነዚህ ኬሚካሎች እና ሆርሞኖች መጠን መጨመር የኮሮናሪ አርተሪዎች እንዲሰፉ እና  ወደ ልብ ሴሎች የሚደረሰው የደም ፍሰት መጠን እንዲጨምር በማድረግ የልብ ሴሎች የሚያስፈልጋቸውን የኦክስጂን ወይም የደም መጠን የሚያገኙ ይሆናል። ይህ ዓይነት በሚያስፈልገው ደረጃ ወደተወሰነ የሰውነት ክፍል የሚደርሰውን የደም ፍሰት መጠን የመቆጣጠሪያ መንገድ የደም ፍሰትን በራስ አቅም የመቆጣጠር ችሎታ ወይም አቅም (autoregulation) ተብሎ ይጠራል።

   ወደ ልብ ሴሎች የሚደርስው የደም መጠን በሚቀንስበት ወይም በሚቋረጥበት ወቅት የልብ ሴሎች በቂ አክሲጂን እና ንጥረምግቦችን ማግኘት ስለማይችሉ ለከፍተኛ ጉዳት ወይም ለሞት የሚዳረጉ ይሆናል። የልብ ሴሎች በተጉዱበት ሆኔታ ውስጥ ልብ  ተግባሩን ማከናወን ወይም በበቂ መጠን ደምን መቀበል እና መርጨት ስለማይችል ለሌሎች የሰውነት ክፍሎች እና ልለብ ሴሎች ጭምር ደም በበቂ መጠን የሚደርስ ደም መርጨት አይችልም።

   ወደ ልብ ከሚደርሰው የኦክስጂን መጠን መቀነስ ጋር በተገናኘ በልብ ሴሎች ላይ የሚከሰት ጉዳት (Ischemia) ለልብ ሴሎች የሚያስፈልጋቸው የኦክስጂን መጠን ከፍላጎታቸው ጋር በተመጣጠነ መጠን እንዳይሆን በሚያደርጉ በተለያዩ ምክንያቶች የተነሳ ሊከሰት ይችላል። ከኦክሰጂን መጠን መቀነስ ጋር በተገናኘ  በልብ ሴሎች ላይ የሚፈጠረው ጉዳት ወደ ልብ የሚደረሰው የደም ወይም የኦክስጂን መጠን መቀነስ ወይም በልብ ሴሎች የኦክስጂን ፍላጎት መጠን መጨመር የተነሳ ሊፈጠር ይችላል። 

  ለልብ ሴሎች የሚደረሰው የደም ወይም የኦክስጂን መጠን እንዲቀንስ ከሚያደርጉ ሆኔታዎች መካከል በትልቁ ደም ቅዳ ቧንቧ ውስጥ የሚኖረው የግፊት መጠን መቀነስን ተከትሎ ወደ ኮሮናሪ አርተሪ ውስጥ የሚገባው የደም መጠን መቀነስ ፣ የልብ ግድግዳ ከመጠን በላይ መወፈር ፣ የኮሮናሪ አርተሪ ግድግዳ መጠንከር ወይም በበቂ መጠን መለጠጥ ወይም መስፋት አለመቻል ፣ በኮሮናሪ አርተሪ ውስጥ የሚፈጠር የስብ ክምችት (atherosclerosis) ፣ በኮሮናሪ አርተሪ ግድግዳ ላይ የሚፈጠር የደም መርጋት (thrombosis) ፣ የኮሮናሪ አርተሪ ቧንቧ እንዲጠብ የሚያደርጉ መድኃኒቶችን መጠቀም ፣ የልብ ምት ፍጥነት በከፍተኛ መጠን መጨመር ፣ የልብ ምት መዛባት ፣  የሰውነት ሙቀት በከፍተኛ መጠን መጨመር ፣ በሰውነት ውስጥ የተሰራጨ ኢንፊክሽን (sepsis) ፣ የደም ማነስ እንዲሁም ሌሎች በሰወነት ውሰጥ የሚገኘው የደም መጠን ፣ በደም ውስጥ የሚገኘው የኦክስጂን መጠን ወይም ወደ ልብ የሚደርሰው የደም መጠን እነዲቀንስ የሚያደርጉ ሆኔታዎች ዋንኞቹ ናቸው። 

   የኮሮናሪ አርተሪ መጥበብ በተከሰተበት ሆኔታ ውስጥ እንደ ከፍተኛ ጭንቀት ወስጥ መግባት ፣ ከፍተኛ እንቅሰቃሴ ማድረግ ፣ ከባድ አቃን ማንሳት ያሉ ሀኔታዎች የልብን የኦክስጂን መጠቀም ፍላጎት በመጨመር ወደ ልብ ሴሎች ከሚደርሰው የኦከሰጂን መጠን እና ለልብ ሴሎች በሚያስፈልገው የደም መጠን መካከል ከሚፈጠር አለመጣጣም ጋር በተገናኘ በልብ ሴሎች ላይ ከሚከሰት ጉዳት የተነሳ የልብ የጤና ችግር እንዲከሰት ሊያደርጉ ይችላሉ። 

በልብ እና በደም ቧንቧ ሥርዓት ላይ የጤና ችግሮች ከሚያስከትሉ ሆኔታዎች መካከል አንዱ እና ዋንኛው በኮሮናሪ አርተሪ ላይ በሚከሰት ጉዳት የተነሳ ወደ ልብ ከሚደርሰው የኦክስጂን መጠን መቀነስ ጋር በተገናኘ የሚፈጠር የልብ የጤና ችግር (Coronary Heart Disease / CHD) ዋንኛው ነው። 

  ምንም አንኳን በልብ እና በደም ቧንቧ ሥርዓት ላይ የሚፈጠሩ የጤና ችግሮችን ለመለየት የሚረዱ ዘመናዊ ቲክኖሎጂዎች በየግዜው እየተሻሻሉ ቢመጡም ፣ በልብ እና የደም ቧንቧ ሥርዓት ላይ የሚፈጠሩ የጤና ችግሮችን ለማከም የሚችሉ የሰለጠኑ በላሙያዎች ቁጥር በየግዜው አየጨመረ ቢመጣም እንዲሁም በልብ እና በደም ቧንቧ ሥርዓት ላይ ለሚከሰቱ የጤና ችግሮች ተጋላጭ ለሆኑ ሰዎች የሚሰጠው ህክምና ፣ እንክብካቤ እና ክትትል እየጨመረ ቢመጣም ከልብ እና ከደም ቧንቧ ሥርዓት የጤና ችግር በተለይም ከኮሮናሪ አርተሪ ጋር በተገናኘ ከሚከሰቱ የልብ የጤና ችግሮች ጋር በተገናኘ ህይወታቸውን የሚያጡ ሰዎች ቁጥር ግን በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ በመምጣት ላይ ይገኛል።

    በኮሮናሪ አርተሪ ላይ በሚፈጠር ጉዳት የተነሳ ወደ ልብ ከሚደርሰው የኦክስጂን መጠን መቀነስ ጋር በተገናኘ የሚፈጠር የልብ የጤና ችግር በተለያዩ ስያሜዎች ሊጠራ ይችላል። ከእነዚህም ስያሜዎች ውስጥ ወደ ልብ ሴሎች የሚደረሰው የኦክስጂን መጠን መቀነስ ጋር በተገናኘ የሚፈጠር የልብ የጤና ችግር (Ischemic Heart Disease) ወይም የኮሮናሪ አርተሪ የጤና ችግር (Coronary artery Disease / CAD) በተቀያያሪነት አንድን የበሽታ ዓይነት ለመግለጽ ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ። በእነዚህ የበሽታ ስሞች የሚገለፀው የልብ የጤና ችግር በኮሮናሪ አርተሪ ግድግዳ ላይ በሚፈጠር የስብ ክምችት የተነሳ ወይም በሌሎች በኮሮናሪ አርተሪ ላይ ጉዳት በሚያስከትሉ ሆኔታዎች የተነሳ ወደ ልብ ሴሎች የሚደረሰው የኦክሰጂን እና የንጥረምግቦች መጠን መቀነስ የተነሳ በልብ ሴሎች ላይ የሚደርስ ጉዳትን የሚያስከትል የጤና ችግር ነው። 

   ወደ ልብ ሴሎች በሚደረሰው የደም ፍሰት ውስጥ የሚገኘው የኦክስጂን መጠን የልብ ሴሎች ከሚያስፈልጋቸው የኦክስጂን መጠን ጋር ተመጣጣኝ በማይሆንበት ውቅት በልብ ሴሎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ይከሰታል። በዚህም ጉዳት የተነሳ ልብ ለራሱም ሆነ ለመላው የሰውነት አካል በቂ የሆነ የደም መጠን መርጨት ስለማይችል የልብ ምት መዛባት (arrhythmia) ፣ የልብ ድካም ወይም በድንገት የሚከሰት የሞት አደጋ ሊከሰት ይችላል። 

  ወደ ልብ ሴሎች በሚደረሰው ደም ውስጥ የሚገኘው የኦክስጂን መጠን መቀነስን ተከትሎ በልብ ሴሎች ላይ የሚፈጠረው ጉዳት በፍጥነት ካልታከመ ወይም ወደ ልብ ሴሎች የሚደረሰው የኦክስጂን መጠን በፍጥነት ካልተሻሻለ ጉዳት የደረሰባቸው ሴሎች ሊሞቱ እና የተጉዳው የልብ ክፍል ተመልሶ የቀደመ ተግባሩን ማከናን በማይችልበት ደረጃ ላይ ሊደርሰ ይችላል። 

   ወደ ልበ ሴሎች የሚደርሰው የደም ወይም የኦክሰጂን መጠን መቀነስን ተከትሎ በሚፈጠር የልብ ሴሎች መሞት የተነሳ ጉዳት የደረሰበት የልብ ጡንቻ ክፍል በቋሚነት ተግባሩን በማያከናውንበት ደረጃ ላይ የሚያደርስ ጉዳት በኮሮናሪ አርተሪ መሉ ለሙሉ መዘጋት የተነሳ የሚከሰት የልብ ሴሎች እረት ወይም መሞት (myocardial infarction) ተብሎ ይጠራል። በኮሮናሪ አረተሪ መሉ በሙሉ መዘጋት የተነሳ የሚከሰት የልብ ሴሎች እረት ወይም መሞት በድንገት በፍጥነት የሚከሰት የሞት አደጋን ሊያስከትል ስለሚችል አፋጣኝ ህክምና ያስፈልገዋል።

በኮሮናሪ አረተሪ ላይ በሚከሰቱ የጤና ችግሮች የተነሳ በልብ ሴሎች ላይ የሚፈጠር ጉዳት (CHD) በዋናነት የሚከሰተው በኮሮናሪ አርተሪ ውስጥ በሚፈጠር የስብ ክምችት (atherosclerosis) የተነሳ ቢሆንም ሌሎች ሆኔታዎችም የኮሮናሪ አርተሪ እንዲጠብ እና ወደ ልብ ሴሎች የሚደረስው የደም ወይም የኦክስጂን መጠን እንዲቀንስ በማድረግ በልብ ሴሎች ላይ የሚፈጠር ጉዳት ወይም እረት ሊያስክትሉ ይቻላሉ። በኮሮናሪ አርተሪ ግድግዳ ላይ የሚፈጠር የስብ ክምችት ቀስ በቀስ የኮሮናሪ አርተሪ ስፋት እንዲጠብ በማድረግ ለተለያዩ የልብ የጤና ችግሮች ተጋላጭነት እንዲጨምር ያደርጋል። በኮሮናሪ አርተሪ ግድግዳ ላይ የሚፈጠር የስብ ክምችት ፣  በኮሮናሪ አርተሪ ግድግዳ ላይ የሚፈጠር የደም መርጋት (thrombosis) ፣ የኮሮናሪ አርተሪ ግድግዳ ጡንቻ እንዲኮማተር እና እንዲጠብ (vasospasm) የሚያደርጉ ሆኔታዎች እንዲሁም በኮሮናሪ አርተሪ ግድግዳ ላይ በሚገኙ የኢንዶቲሊያል ሴሎች ላይ ጉዳት (endothelial injury) የሚያስከትሉ ሆኔታዎች ወይም የጤና ችግሮች የኮሮናሪ አርተሪ እንዲጠብ ወይም ሙሉ ለሙሉ እንዲዘጋ በማድረግ ወደ ተለያዩ የልብ ክፍሎች ውስጥ የሚደረሰው የደም መጠን እንዲቀንሰ ሊያደርጉ ይችላሉ።

   በኮሮናሪ አርተሪ ግድግዳ ላይ ከሚፈጠር የስብ ክምችት በተጨማሪ በደም ውስጥ ከሚገኘው የኦክሰጂን መጠን መቀነስ ጋር በተገናኘ በልብ ሴሎች ላይ ጉዳት ሊያስከትሉ ከሚችሉ ሆኔታዎች መካከል በአተነፋፈስ ሥርዓት ላይ ከሚከሰት የጤና ችግር ጋር በተያያዘ በደም ውስጥ የሚገኘው የኦክስጂን መጠን በከፍተኛ ደረጃ መቀነስ ( hypoxia) ፣ በሰውነት ውስጥ የሚገኘው አጠቃላይ የደም መጠን መቀነስ ወይም በደም ቧንቧዎች ውስጥ የሚኖረው የደም ግፊት መጠን መቀነስ ዋንኞቹ ናቸው። 

  አንድ አንድ ግዜም ምክንያቱ በትከክል የማይታወቅ በኮርናሪ አርተሪ ግድግዳ ጡንቻ ላይ በሚፈጠር ድንገተኛ መኮማተር የተነሳ የኮሮናሪ አርተሪ የደም ቧንቧ መጥበብ በማስከተል ወደ ልብ ሴሎች የሚደርሰው የደም መጠን እንዲቀንስ በማድረግ በልብ ሴሎች ላይ ጉዳት እንዲከሰት ሊያደርግ ይችላል።

  በኮሮናሪ አርተሪ ግድግዳ ላይ በሚፈጠር የስብ ክምችት የተነሳ በልብ ሴሎች ላይ ጉዳት እንዲከሰት ከሚያደርጉ አጋላጭ ሆኔታዎች መካከል በጾታ ወንድ መሆን ፣ የእድሜ መግፋት (በወንዶች 45 አመት በላይ መሆን እና በሴቶች ከ55 አመት በላይ መሆን) ፣ በቤተሰብ ውስጥ (በወንዶች ከ 55 አመት በታች ወይም በሴቶች ከ 65 እመት በታች በሆኑ የቤተሰብ አባላት) በኮሮናሪ አርተሪ ላይ በሚፈጠር ጉዳት የተነሳ በልብ የጤና ችግር የተጠቁ ሰዎች መኖር ወይም በቅርብ የቤተሰብ አባል ላይ በኮሮናሪ አርተሪ ላይ ከሚፈጠር ጉዳት የተነሳ የተከሰተ ድንገተኛ የሞት አደጋ መኖር ፣ በደም ውስጥ የሚገኘው የኮሌስትሮል መጠን መጨመር (ዝቅተኛ መጠን ያለው ሊፖፕሮቲን የያዘ ኮሌስትሮል (LDL) መጠን መጨመር እና ከፍተኛ መጠን ያለው ሊፖፕሮቲን የያዘ ኮሌሰትሮል (HDL) መጠን መቀነስ) ፣ ሲጋራ ማጤስ ፣ የደም ግፊት መጠን መጨመር ወይም የደም ግፊት መጠን መጨመር በሽታ ፣ የስኳር በሽታ እና ከመጠን ያለፈ የሰውነት ክብደት ዋንኞቹ  ናቸው። ከላይ የተገለጹት አጋላጭ ሆኔታዎችን በመከላከል ወይም በመቀነስ በልብ እና በደም ቧንቧ ሥርዓት ላይ የሚፈጠሩ የጤና ችግሮችን በከፍተኛ ደረጃ መቀነስ ይቻላል። 

  የልብ ሴሎች የሚጠበቅባቸውን ደምን የመቀበል እና የመኮማተር ወይም ደምን የመርጨት ተግባር በሚገባ ለማከናወን፣ የሚያስፈልጋቸውን ኦክስጂን ፣ ንጥረ ምግብ ወይም ሃይል በሚፈለገው መጠን እና ባልተቋረጠ መንገድ ማግኘት ያስፈልጋቸዋል። ወደ ሴሎች የሚደርሰው የኦክስጂን መጠን የልብ ሴሎች ከሚፈልጉት መጠን በታች በሚሆንበት ወቅት በልብ ሴሎች ላይ ጉዳት ይከሰታል። የልብ ሴሎች የሚያመርቱትን ሃይል በማጠራቀም ችግር በሚያጋጥማቸው ግዜ መጠቀም ስለማይችሉ ወደ ልብ ሴሎች የሚደረሰው የኦክስጂን መጠን ለጥቂት ደቂቃዎች እንኳን በሚቀንስበት ወይም ለጥቂት ሰከንዶች በሚቋረጥበት ወቅት ተግባራቸውን ለማከናወን የሚያስፈልጋቸውን ሃይል ለማምረት በቂ ኦክስጂን ስለማይኖራቸው የልብ ሴሎች ለከፍተኛ ጉዳት የሚጋለጡ ይሆናል። 

   በኮሮናሪ አርተሪ ላይ በሚፈጠር ጉዳት የተነሳ ወደ ልብ ከሚደርሰው የኦክስጂን መጠን ጋር በተገናኘ የሚፈጠር የልብ የጤና ችግር አብዛኛውን ግዜ የሚከሰተው ቀስ በቀስ በኮሮናሪ አርተሪ ግድግዳ ላይ በሚፈጠር የስብ ክምችት የተነሳ ነው። ስለሆነም አብዛኛዎቹ በኮሮናሪ አርተሪ ላይ ጉዳት የደረሰባቸው ወይም የኮሮናሪ አርተሪ መጥበብ የተከሰተባቸው ሰዎች ምንም ዓይነት ምልክት እና ለውጥ ሳያታይባቸው ለረጀም ግዜ ሊቆዩ ይችላሉ። በኮሮናሪ አርተሪዎች ግድግዳ ላይ የሚፈጠረው የስብ ክምችት የኮሮናሪ አርተሪ እንዲጠብ በማድረግ ወደ ልብ ሴሎች የሚደርሰውን የደም ፍሰት በመቀነስ በልብ ሴሎች ላይ ጉዳት ሊያስከትል የሚችለው የኮሮናሪ አርተሪ ቀደሞ ከነበረው መጠን ወይም ስፋት ውስጥ ከ 75 በመቶ በላይ ሲጠብ ወይም ሲዘጋ ነው። 

    መለስተኛ የሆነ የኮሮናሪ አርተሪ መጥበብ ወይም በኮሮናሪ አርተሪ ውስጥ የሚኖረው የደም ፍሰት በከፊል መዘጋት በልብ ሴሎች ላይ የከፋ ጉዳት ሳያስከትል ለረጅም ግዜ ሊቆይ ይችላል። 

   በኮሮናሪ አርተሪ ግድግዳ ላይ የሚፈጠር የስብ ክምችት በአንድ ወይም ከአንድ በላይ በሆኑ የኮሮኖሪ አርተሪዎች ወይም በዋናዎቹ በግራ እና በቀኝ የኮሮናሪ አርተሪዎች ወይም ከዋናዎቹ የኮሮናሪ አርተሪዎች ላይ በሚነሱ ቅርንጫፎች ውስጥ ሊከሰት ይችላል። በኮሮናሪ አርተሪ ግድግዳ ላይ የሚፈጠር የስብ ክምችት ቀስ በቀስ ወይም በሂደት የሚከሰት እና የኮሮናሪ አርተሪ በከፍተኛ መጠን እስኪጠብ ወይም አስኪዘጋ ድረስ ምንም ዓይነት ምልክት እና ለውጥ ሳያሳይ የሚቆይ የልብ የጤና ችግር ነው።

  በደም ቧንቧዎች ግድግዳ ላይ የሚገኙ የኢንዶቲሊያል ሴሎች ላይ በተለያዩ ምክንያቶች ( በደም ግፊት መጠን መጨመር በሽታ ፣ የስኳር በሽታ ፣ ሲጋራ ማጤስ እንዲሁም ከፍተኛ መጠን ያለው አልኮል መጠጥ መውሰድ ) ብግነት ወይም ጉዳት በሚከሰትበት ወቅት በደም ውስጥ የሚገኘው ሰብ ወይም ኮሌሰትሮል በተጎዱት ኢንዶቲሊያል ሴሎች ላይ መጣበቅ ወይም መከማቸት ይጀምራል። በሂደትም በኢንዶቲሊያል ሴሎች ላይ በተከማቸው ስብ ላይ በሚለጠፉ ነጭ የደም ሴሎች እና ደም እንዲረጋ የሚያደርጉ የፕሌትሌት ሴሎች የተነሳ በኮሮናሪ አርተሪ ግድግዳ ላይ የተከማቸው ስብ ወይም ኮሌስትሮል በመጠን እየጨመረ ይመጣል። በኮሮናሪ አርተሪ ግደግዳ ላይ የሚከማቸው የስብ ፣ የነጭ ፣ የቀይ እና የፕሌትሌት ሴሎች ክምችት በደም ቧንቧው ግድግዳ ላይ በሚያስከትለው ብግነት የተነሳ ተጨማሪ የስብ ክምችት ፣ ነጭ የደም ሴሎች ፣ የቀይ የደም ሴሎች እና የፕሌትሌት ሴሎች ክምችት በመጠን አየጨመረ ስለሚመጣ የኮሮናሪ አርተሪ አየጠበበ የሚመጣ ይሆናል። ይህ የሰብ ክምችት በጡንቻ ሴሎች እየተሸፈነ እና እየጠነከረ በመምጣት የኮርኖናሪ አርተሪ የበለጠ እንዲጠብ ወይም እንዲዘጋ ሊያደርግ ይችላል። ይህ ዓይነት በተለያዩ ሂደቶች ውሰጥ በሚያልፍ በደም ቧንቧ ግድግዳ ላይ በሚፈጠር የስብ ክምችት የተነሳ  የደም ቧንቧ የሚጠብበት ወይም የሚዘጋበት ሂደት አቴሮስክሌሮሲስ / atherosclerosis ተብሎ ይጠራል። 

በኮሮናሪ አርተሪ ግድግዳ ላይ የሚፈጠር የስብ ክምችት በመጠን ከፍተኛ ደረጃ ላይ እስከሚደርስ ምንም ዓይነት ምልክቶችን ሳያሳይ የሚቆይ ቢሆንም አካላዊ እንቅስቃሴ በሚደረግበት ፣ ሰውነት በከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ በሚገባበት ወቅት ወይም ከፍተኛ ጎልበት የሚጠይቅ ሥራ በሚሰራበት ወቅት ወይም በተለያዩ ምክንያቶች ለልብ ሴሎች የሚያስፈልገው እና የ የኦክስጂን መጠን በሚጨምርበት እና ለልብ ሴሎች በሚደርሰው የደም መጠን እና የልብ ሴሎች በሚያስፈልጋቸው የደም መጠን መካከል መጣጣም በማይኖርበት ወቅት በልብ ሴሎች ላይ ከሚፈጠረው ጉዳት ጋር በተገናኘ በደረት ላይ የሚሰማ ህመም ወይም ያለመመቸት እንዲፈጠር ሊያደርግ ይችላል። 

     ለልብ ሴሎች የሚያስፈልጋቸው እና የሚደርሳቸው የደም መጠን በማይጣጣምበት ወቅት በልብ ሴሎች ላይ ጉዳት በማስከትል በልብ ሴሎች ላይ ከሚፈጠር ጉዳት ጋር ተያይዘው የሚከሰቱ ምልክቶች እና ለውጦች መታየት የሚጀምሩ ይሆናል። በኮሮናሪ አርተሪዎች ግድግዳ ላይ በሚፈጠር የስብ ክምችት ለረጅም ግዜ የቆየ የኮሮናሪ አርተሪ መጥበብ ከተለመደው የህይወት ዘይቤ ወጣ ያለ እንቅስቃሴ በሚደረግበት ፣ ከፍተኛ ጉልበት የሚፈልግ ሥራ በሚሰራበት ወይም የልብ ሴሎች የኦክስጂን ፍላጎት በሚጨምርበት ወቅት የሚፈጠር  በደረት ላይ የሚሰማ ህምም የሚያስከትል የልብ የጤና ችግር አካላዊ እንቅስቃሴ በሚደረግበት ወቅት ወደ ልብ ከሚደረሰው የኦክስጂን መጠን መቀነስ ጋር በተገናኘ የሚፈጠር የደረት ህመም ወይም በእንቅስቃሴ ወቅት የሚከሰት የደረት ህመም (stable angina) ተብሎ ይጠራል።

   አካላዊ እንቅስቃሴ በሚደረግበት ወቅት የሚከሰት የደረት ህመም ወይም በእንቅስቃሴ ወቅት ወደ ልብ ከሚደረሰው የኦክስጂን መጠን መቀነስ ጋር በተገናኘ የሚፈጠር የደረት ህመም እንቅስቃሴ ማድረግ በሚቆምበት ወይም እረፍት በሚደረግበት ወይም የኮሮናሪ አርተሪ የደም ቧንቧ እንዲሰፋ የሚያደርጉ መድኃኒቶች በሚወሰዱበት ወቅት በደረት ላይ የሚሰማው ህመም እና ሌሎች ለውጦች መሉ በሙሉ የሚቀንሱ ወይም የሚጠፉ ይሆናል። የደረት ህመሙ በሌላ ግዜም በተደጋጋሚ ተመልሶ ሊመጣ ይችላል።

  በኮሮናሪ አርተሪ ግድግዳ ላይ የሚፈጠረው የስብ ክምችት አንድ አንድ ግዜ ከተከማቸበት ወይም ከተጣበቀበት ግድግዳ ላይ በከፊል ሊላቀቅ ይችላል። በኮሮናሪ አርተሪ ግድግዳ ላይ የሚፈጠረው የስብ ክምችት በከፊል በሚላቀቅበት ወቅት ከስብ ክምችቱ በተላቀቀው ግድግዳ ላይ ደም እንዲርጋ የሚያደርጉ የፕሌትሌት ሴሎች እንዲከማቹ ፣ የደም መርጋት ሥርዓት እንዲነቃቃ ፣ በደም ቧንቧው ግድግዳ ላይ የሚፈጠረው የደም መርጋት ሂደት እንዲፈጣን እና የኮሮናሪ አርተሪ መዘጋት እንዲጨምር በማድረግ ለልብ ሴሎች የሚደረሰው የደም ወይም የኦክስጂን መጠን በከፍተኛ ሆኔታ እንዲቀንስ  ያደርጋል። ይህንንም ተከትሎ በድንገት የሚከሰት በደረት ላይ የሚሰማ ህመም እና ሌሎች በኮሮናሪ አርተሪ ላይ በሚከሰት ጉዳት የተነሳ ወደ ልብ ሴሎች ከሚደርሰው የኦክስጂን መጠን መቀነስ ጋር በተገናኘ የሚፈጠሩ ምልክቶች እና ለውጦች የሚከሰቱ ይሆናል። ይህ ዓይነት ቀድሞ ከኮሮናሪ አርተሪ ላይ ከተፈጠረ ጉዳት ጋር በተገናኘ ወደ ልብ ሴሎች የሚደረሰው የደም መጠን በበለጠ መቀነስ ጋር በተገናኘ የሚከሰት የልብ የጤና ችግር አካላዊ እንቅስቃሴ በሚደረግበት ወይም በማይደረግበት ወቅት ወደ ልብ ከሚደረሰው የኦክስጂን መጠን መቀነስ ጋር በተገናኘ የሚፈጠር የደረት ህመም ወይም እንቅሰቃሴ በሚደረግበት ወይም በማይደረግበት ወቅት የሚፈጠር የደረት ህመም  (Unstable angina) ተብሎ ይጠራል።

  አካላዊ እንቅስቃሴ በሚደረግበት ወይም በማይደረግበት ወቅት ወደ ልብ ከሚደረሰው የኦክስጂን መጠን መቀነስ ጋር በተገናኘ የሚፈጠር የደረት ህመም (unstable angina) ከፍተኛ ጉልበት የሚጠይቅ ሥራ በሚሰራበት ወይም ሰውነት በከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ በሚገባበት ወይም ምንም ስራ በማየሰራበት ወይም እረፍት በሚደረግበት ወይም በማንኛውም ሆኔታ ውስጥ ሊከሰት የሚችል የልብ የጤና ችግር ነው። ይህ የልብ የጤና ችግር በሚከሰትበት ወቅት እረፍት በመውሰድ  ወይም የኮርናሪ አርተሪን የሚያሰፉ መድኃኒቶችን በመጠቀም ከበሽታው ጋር በተያያዘ የሚፈጠረውን በደረት ላይ የሚሰማ ህመም ወይም ሌሎች ለውጦችን መቀነስ አይቻልም።

    አካላዊ እንቅስቃሴ በሚደረግበት ወይም በማይደረግበት ወቅት ወደ ልብ ከሚደረሰው የኦክስጂን መጠን መቀነስ ጋር በተገናኘ የሚፈጠር የደረት ህመም (unstable angina) በሚከሰትበት ወቅት ወደ ልብ ሴሎች የሚደረሰው የደም ፍሰት ሙሉ በሙሉ ስለማይዘጋ እና እንድ አንዴም በኮሮናሪ አርተሪ ውስጥ የተፈጠረው የደም መርጋት (thrombosis) በራሱ መሰባበር ስለሚጀምር እንዲሁም ለልብ ሴሎች የሚደርሰው የደም ፍሰት መሉ በሙሉ ስለማይቋረጥ የልብ ሴሎች ሞት የሚከስት አይሆነም። ነገር ግን በአፋጣኝ ህክምና ማግኘት እና ሆኔታዎችን ማስተካከል ካልተቻለ በልብ ሴሎች ላይ የሚደርሰው ጉዳት የከፋ ደረጃ ላይ ሊደርስ ይችላል።

   ከኮሮናሪ አርተሪ መጥበብ ጋር በተገናኘ የሚከሰት የልብ ሴሎች ጉዳትን በአፋጣኝ ማስተካከል በማይቻልበት ወቅት የኮሮናሪ አርተሪው ሙሉ በሙሉ በመዝጋት እና ወደ ልብ ሴሎች የሚደርሰውን የደም ፍሰት ለረጀም ደቂቃዎች እንዲቋረጥ በማድረግ በልብ ሴሎች ላይ የተከሰተው ጉዳት የልብ ሴሎች አረት ወይም ሞት ሊይስከትል ይችላል። በኮሮናሪ አርተሪ ውስጥ በሚፈጠር የስብ ክምችት የተነሳ ለልብ ሴሎች የሚደረሰው የደም ወይም የኦክስጂን መጠን ሙሉ በሙሉ በሚቋረጥበት ወቅት በልብ ሴሎች መሞት የተነሳ የተወሰነ የልብ ክፍል በቋሚነት ተግባሩን በማያከናውንበት ደረጃ ላይ የሚያደርስ ጉዳት እንዲፈጠር ሊያደርግ ይችላል። ይህ ዓይነት ወደ ልብ ሴሎች የሚደረሰው የደም ወይም የኦክስጂን ፍሰት መቋረጥ ጋር በተገናኘ የልብ ሴሎች እረት ወይም መሞት የሚያስከትል የልብ የጤና ችግር ወደ ልብ ከሚደረሰው የኦክስጂን መጠን መቀነስ ጋር በተገናኘ የሚፈጠር የከፋ የልብ የጤና ችግር (myocardial infarction) እንዲፈጠር ያደርጋል።

  ወደ ልብ ከሚደረሰው የኦክስጂን መጠን መቀነስ ጋር በተገናኘ የሚፈጠር የከፋ የልብ የጤና ችግር (myocardial infarction) በሚያጠቃው የልብ ክፍል እና በኤሌክትሮካርዲዮግራም ምርመራ በሚገኘው ውጤት መሰረት ለሁለት ምድቦች ይከፈላል።

 በኮሮናሪ አርተሪ ግድግዳ ላይ ከሚፈጠር የስብ ክምችት የተነሳ ለልብ ሴሎች የሚደርሰው የደም ወይም የኦክስጂን መጠን ሙሉ ለሙሉ መቋረጥ ጋር ተያያዞ የተወሰነ የልብ ግድግዳ ክፍል ሙሉ በሙሉ አንዲጎዳ የሚያደርግ የልብ የጤና ችግር ኮኮሮናሪ አርተሪ ሙሉ በሙሉ መዘጋት ጋር በተገናኘ የ ኢስ ቲ (ST) ሴግመንት ክፍ እንዲል የሚያደርግ የከፋ የልብ የጤና ችግር (ST Elevation Myocardial Infarction / STEMI) ተብሎ ይጠራል።

 

      በተወሰነ የልብ የግድግዳ ክፍል ላይ የሚፈጠር ከኮሮናሪ አርተሪ ሙሉ በሙሉ መዘጋት ጋር በተገናኘ በልብ ሴሎች ላይ እረት ወይም መሞት የሚያስከትል እና በ ኤልክትሮካርዲዮግራም ምርመራ የ ኤስ ቲ ሴግመንት መገኘት ለሚኖርበት ቦታ ዝቅ ብሎ እንዲገኝ የሚያደርግ የጤና ችግር ከኮኮሮናሪ አርተሪ ሙሉ በሙሉ መዘጋት ጋር በተገናኘ የ ኤስ ቲ (ST) ሴግመንት ዝቅ እንዲል የሚያደርግ የከፋ የልብ የጤና ችግር (Non ST Elevation Myocardial Infarction / NSTEMI) ተብሎ ይጠራል።