Course Content
ምዕራፍ አሥራ አራት : በልብ እና በደም ቧንቧ ሥርዓት አፈጣጠር ሂደት ወቅት የሚፈጠሩ የጤና ችግሮች
0/16
ምዕራፍ አሥራ አምሥት : ከልብ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ ጋር በተገናኘ የሚፈጠሩ የልብ የጤና ችግሮች (Cardiac electrical system abnormalities)
0/16
ምዕራፍ አስራ ሰባት : በልብ በሮች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Valvular heart diseases)
0/16
ምዕራፍ ሃያ አንድ : የልብ ድካምበሽታ (Heart failure )
0/1
ምዕራፍ ሃያ ሦስት : በደም ቧንቧዎች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Vascular diseases)
0/22
በልብ እና በደም ቧንቧ ሥር ዓት ክፍሎች ውስጥ ሊፈጠሪ የሚችሉ የጤና ችግሮች (Pathology of Cardiovascular System)

 16.1. ከኮሮናሪ አርተሪ ጋር በተገናኘ በልብ ሴሎች ላይ የሚፈጠር ጉዳት  (Coronary Heart Diseases)  

   ከቀኝ እና ከግራ የትልቁ ደም ቅዳ የደም ቧንቧ ላይ የሚነሱት የቀኝ እና የግራ የኮሮናሪ አርተሪዎች ወደ ተለያዩ ቅርንጫፎቸ በመከፋፈል ለተለያዩ የልብ ክፍሎች በቂ የሆነ የደም ወይም የኦክስጂን መጠን እንዲደረስ ያደርጋሉ። በኮሮናሪ አርተሪ ላይ በሚከሰቱ የጤና ችግሮች የተነሳ በልብ ሴሎች ላይ የሚፈጠሩ ጉዳቶች በልብ ጡንቻ ወይም በልብ ሴሎች ላይ በሚያስከትሉት የጉዳት መጠን ፣ ጉዳቱን ተከትሎ በበሽተኛው ላይ በሚከሰቱ ምልክቶች እና የስሜት ለውጦች እንዲሁም በኤልክትሮካርዲዮግራም ምርመራ በሚገኘው የምርመራ ውጤት መሰረት ወይም በልብ ሴሎች ላይ ከሚደረሰው የጉዳት ደረጃ ጋር በተገናኘ ከልብ ሴሎች በሚለቀቁ እና በደም ውስጥ በሚገኙ የልብ ሴሎች ላይ ጉዳት መድረሱን በሚያሳዩ ፕሮቲኖች ወይም ኬሚካሎች መጠን መሰረት በተለያዩ ምድቦች ሊከፈሉ ይችላሉ።

    በኮሮናሪ አርተሪ ላይ በሚከሰቱ የጤና ችግሮች የተነሳ በልብ ሴሎች ላይ የሚፈጠር ጉዳት በዋናነት በአራት ምድቦች ይከፈላል። እነዚህም አካላዊ እንቅስቃሴ በሚደረግበት  ወቅት ወደ ልብ ከሚደረሰው የኦክስጂን መጠን መቀነስ ጋር በተገናኘ የሚፈጠር የደረት ህመም (stable angina) ፤ አካላዊ እንቅስቃሴ በሚደረግበት ወይም በማይደረግበት ወቅት ወደ ልብ ከሚደረሰው የኦክስጂን መጠን መቀነስ ጋር በተገናኘ የሚፈጠር የደረት ህመም (unstable angina) ፣ ከኮኮሮናሪ አርተሪ ሙሉ በሙሉ መዘጋት ጋር በተገናኘ የኤስ ቲ (ST) ሴግመንት ዝቅ እንዲል የሚያደርግ የከፋ የልብ የጤና ችግር (Non ST Elevation Myocardial Infarction / NSTEMI) እና  ኮኮሮናሪ አርተሪ ሙሉ በሙሉ መዘጋት ጋር በተገናኘ የኤስ ቲ (ST) ሴግመንት ክፍ እንዲል የሚያደርግ የከፋ የልብ የጤና ችግር (ST Elevation Myocardial Infarction / STEMI) ናቸው።

  ወደ ልብ ሴሎች የሚደረሰው የደም መጠን በከፍተኛ መጠን በሚቀንስብት ወቅት የልብ ሴሎች ይሞታሉ። የልብ ሴሎች በሚሞቱበት ወቅት በውስጣቸው የሚገኙ የተለያዩ ፕሮቲኖችን እና  ኬሚካሎችን ወደ ደም ውስጥ የሚለቁ ይሆናል። የእነዚህ ከልብ ሴሎች የሚለቀቁ እና በደም ውስጥ የሚገኙ ኬሚካሎች በደም ውስጥ መገኘት በልብ ሴሎች ላይ ጉዳት መድረሱን እና የልብ ሴሎች እረት ወይም ሞት መከሰቱን ያሳያል። የልብ ሴሎች በከፋ ደረጃ ለጉዳት በሚጋለጡበት ወቅት ከሚለቀቁ እና በደም ምርመራ ወቅት ሊገኙ የሚችሉ ኬሚካሎች መካከል ዋንኞቹ የትሮፖኒን (Troponin) ፣ ማዩግሎቢን (myoglobin) እና ክሪአቲን ካይኔስ (creatine kinase) እንዲሁም ላክቴት ዲአይድሮጂኔስ (lactate dehydrogenase) ዋንኞቹ ናቸው።

   አልፎ አልፎ በእንቅስቃሴ ወይም በከፍተኛ ጫና ወቅት ወደ ልብ የሚደረሰው የደም መጠን የልብ ሴሎችን የኦክስጂን ፍላጎት ማሟላት ካለመቻል ጋር ተያይዞ የሚፍጠር የደረት ህመም የሚከሰተው በረጅም ግዜ ውስጥ ቀስ በቀስ በኮሮናሪ አርተሪ ግድግዳ ላይ በሚፈጠር የስብ ክምችት የተነሳ ነው። ወደ ልብ ሴሎች ከሚደርሰው የደም መጠን መቀነስ ጋር በተገናኘ የሚከሰት ምልክት መታየት የሚጀምረው በሽተኞች ከፍተኛ ጎልበት የሚያስፈልገው እንቅስቃሴ በሚያደርጉበት ፣ በከፍተኛ ጫና ውስጥ በሚሆኑበት ወይም ከተለመደው መጠን በበለጠ ሆኔታ ለልብ የሚያስፈልገው የኦክስጂን መጠን በሚጨምርበት ወቅት እና የልብ የደም ቧንቧዎች ይህን ተጨማሪ የኦከሰጂን መጠን ለልብ ሴሎች ማድረስ በማይችሉበት ወቅት ነው።

      እንቅስቃሴ በሚደረግበት ወይም በማይደረግበት ወቅት ወደ ልብ ከሚደረሰው የኦክስጂን መጠን መቀነስ ጋር በተገናኘ የሚፈጠር የደረት ህመም (unstable angina) ብዙሁን ግዜ የሚከሰተው ለረጅም ግዜ በኮሮናሪ አርተሪ ግድግዳ ላይ የሚፈጠር የስብ ክምችት በድንገት ከተጣበቀበት ግድግዳ ላይ በመላቀቅ በደም ቧንቧው ግድግዳ ላይ ለደም መርጋት ምቹ ሆኔታ በሚፈጠርበት ወቅት ነው።  እንቅስቃሴ በሚደረግበት ወይም በማይደረግበት ወቅት ወደ ልብ ከሚደረሰው የኦክስጂን መጠን መቀነስ ጋር በተገናኘ የሚፈጠር የደረት ህመም በፍጥነት ማከም ወይም የደም ፍሰቱን ማስተካከል በማይቻልበት ወቅት ወደ ልብ ሴሎች የሚደርሰው የደም መጠን ሙሉ በሙሉ ሊቋረጥ ስለሚችል ወደ ልብ ከሚደረሰው የኦክስጂን መጠን መቀነስ ጋር በተገናኘ የሚፈጠር የከፋ የልብ የጤና ችግር (myocardial infarction) እንዲፈጠር ሊያደርግ ይችላል።

  እንቅስቃሴ በሚደረግበት እና በማይደረግበት ወቅት ወደ ልብ ከሚደረሰው የኦክስጂን መጠን መቀነስ ጋር በተገናኘ የሚፈጠር የደረት ህመም እና ወደ ልብ ከሚደረሰው የኦክስጂን መጠን መቀነስ ጋር በተገናኘ የሚፈጠር የከፋ የልብ የጤና ችግር የሚያሳዩት ምልክት እና ለውጥ ተመሳሳይ ሊሆን ስለሚችል በሚታዩ ምልክቶች እና የስሜት ለውጦችእነዚህን  ሁለቱ የልብ የጤና ችግሮች መለየት አስቸጋሪ ይሆናል። ስለዚህም እነዚህን ሁለት የጤና ችግሮች በአንድ በመጠቅለል የተሰጣቸው ስም በድንገት የሚከሰት በኮሮናሪ አርተሪ ላይ የሚከሰት ጉዳት (Acute Coronary Syndrome) ተብሎ ይጠራል። 

 የኮሮናሪ አርተሪ ጡንቻ ላይ በሚፈጠር ድንገተኛ መኮማተር የተነሳ የኮሮናሪ አርተሪ ቧንቧ መጥበብ እንዲከሰት በማድረግ ወደ ልብ ሴሎች የሚደርሰው የኦክስጂን መጠን እንዲቀንስ የሚያደርግ የልብ ጤና ችግር የፕሪንዝሚታል የደረት ህመም (Prinz metal angina) ተብሎ ይጠራል። ይህ በኮሮናሪ አርተሪ ላይ ከሚከሰተ ጉዳት ጋር በተገናኘ የሚከሰት የልብ የጤና ችግር በብዛት የሚፈጠረው ሲጋራ በሚያጤ ሴቶች ላይ ሲሆን በማንኛውም ግዜ ወይም ሰዓት ላይ ሊከሰት ይችላል።