Course Content
ምዕራፍ አሥራ አራት : በልብ እና በደም ቧንቧ ሥርዓት አፈጣጠር ሂደት ወቅት የሚፈጠሩ የጤና ችግሮች
0/16
ምዕራፍ አሥራ አምሥት : ከልብ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ ጋር በተገናኘ የሚፈጠሩ የልብ የጤና ችግሮች (Cardiac electrical system abnormalities)
0/16
ምዕራፍ አስራ ሰባት : በልብ በሮች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Valvular heart diseases)
0/16
ምዕራፍ ሃያ አንድ : የልብ ድካምበሽታ (Heart failure )
0/1
ምዕራፍ ሃያ ሦስት : በደም ቧንቧዎች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Vascular diseases)
0/22
በልብ እና በደም ቧንቧ ሥር ዓት ክፍሎች ውስጥ ሊፈጠሪ የሚችሉ የጤና ችግሮች (Pathology of Cardiovascular System)

16.1.1. እንቅስቃሴ በሚደረግበት ወቅት ወደ ልብ ከሚደረሰው የኦክስጂን መጠን መቀነስ ጋር በተገናኘ የሚፈጠር የደረት ህመም (stable angina)

   እንቅስቃሴ በሚደረግበት ወቅት ወደ ልብ ሴሎች ከሚደረሰው የኦክስጂን መጠን መቀነስ ወይም ወደ ልብ ሴሎች በሚደርሰው እና ለልብ ሴሎች በሚያስፍገው የኦክስጂን መጠን አለመጣጣም  ጋር በተገናኘ የሚፈጠር የደረት ህመም በተደጋጋሚ የሚከሰት የልብ የጤና ችግር ነው። በኮሮናሪ አርተሪ ግድግዳ ላይ የሚፈጠር የስብ ክምችት ቀስ በቀስ የኮሮናሪ አርተሪ እንዲጠብ በማድረግ የልብ ሴሎች የሚፈልጉት የኦክስጂን መጠን በሚጨምርበት ወቅት የሚያስፈልጋቸውን ተጨማሪ ኦክስጂን ማቅረብ ስለማይችል ወደ ልብ ሴሎች የሚደርሰው የደም መጠን የሚቀንስ ይሆናል። እንቅስቃሴ በሚደረግበት ወይም ሰውነት በከፍተኛ ጫና ውስጥ በሚሆንበት ወቅት (emotional strain) ወይም በተለያዩ ምክንያቶች ለልብ ሴሎች የሚያስፈልገው የኦክስጂን መጠን በሚጨምርበት ወቅት በጠበበው የኮሮናሪ አርተሪ ውስጥ የሚያልፈው የደም መጠን የልብ ሴሎች በሚፈልጉት መጠን ኦክሲጂንን ማቅረብ አይችልም። ይህም በልብ ሴሎች ላይ ጉዳት የሚያስከትል ይሆናል።

   ከዚህ የጤና ችግር ጋር በተገናኘ የሚፈጠር በደረት ላይ የሚሰማ ህመም (angina) በተደጋጋሚ ሊከሰት የሚችል ሲሆን እረፍት ማድረግ ወይም የኮሮናሪ አርተሪዎች እንዲሰፉ የሚያደርጉ መድኃኒቶችን መጠቀም ወይም በልብ ላይ የሚፈጠረውን ሥራ የሚቀንሱ መድጋኒቶችን መጠቀም የበሽታው ምልክት ወይም በደረት ላይ የሚሰማው ህመም እንዲቀንስ ያደርጋል።

  እንቅስቃሴ በሚደረግበት ወቅት ወደ ልብ ሴሎች ከሚደረሰው የኦክስጂን መጠን መቀነስ ጋር በተገናኘ በሚፈጠር የደረት ህመም የተጠቁ በሽተኞች ወደ ጤና መስጫ ጣቢያዎች በሚሂዱበት ወቅት በሚደረግላቸው የኤልክሮካርዲዮግራም ምርመራ ውጤት ላይ የሚታይ ለውጥ አይኖርም። ወደ ልብ ሴሎች የሚደርሰው የደም ፍሰት በሽተኞቹ በእርፍት ላይ በሚሆኑበት ወቅት የሚያስፈልጋቸውን የደም መጠን ወይም ኦክስጂን ማቅረብ ይችላል። በተጨማሪም ከኮሮናሪ አርተሪ መጥበብ ጋር በተገናኘ ወደ ሴሎች የሚደረሰው የደም ፍሰት መቀነስ በልብ ሴሎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያደርስ ስላልሆነ በደም ውስጥ የሚገኙ ጉዳት ከደረሰባቸው ሴሎች ውስጥ የሚለቀቁ ኬሚካሎች መጠን ሊጨምር አይችልም።

  እንቅስቃሴ በሚደረግበት ወቅት ወደ ልብ ከሚደረሰው የኦክስጂን መጠን መቀነስ ጋር በተገናኘ የሚፈጠር የደረት ህመም መከሰትን ለማወቅ ከሚረዱ የምርመራ መንገዶች መካከል የአካል እንቅስቃሴ በማድረግ ወይም የልብ ሥራን የሚጨምሩ መድኃኒቶችን በመጠቀም የ ኤልክትሮካረዲዮግራም ምርመራ (stress test) ማድረግ ዋንኛው ነው።

   የአካል እንቅስቃሴ በማድረግ ወይም የልብ ሥራን የሚጨምሩ መድኃኒቶችን በመጠቀም የሚሰራ የኤሌክትሮካርዲዮግራም  ምርመራ (stress test) በሚሰራበት ወቅት በሽተኛው በመሮጫ ማሽን ላይ እየሮጠ የደም ግፊትን ፣ የልብ ምት ፍጥነትን እነአ የኤሌክትሮካርዲዮግራም ምርመራ ውጤትን በመከታታል የልብ ሴሎች የሚደርሳቸውን የደም መጠን ሆኔታ እና የኮሮናሪ አርተሪን ደም የማሳለፍ ብቃት ለማወቅ የሚረዳ የምርመራ መንገድ ነው። አካላዊ እንቅስቃሴ በሚደረግበት ወቅት ለልብ ሴሎች የሚያስፈልገው የደም ወይም የኦክስጂን መጠን ስለሚጨምር የኮሮናሪ አርተሪ ይህንን የልብ የደም ፍላጎት የሚያሟላ የደም ፍሰት ማስተላለፍ መቻል እና አለመቻሉን ከኤሌክትሮካርዲዩግራም የምርመራ ውጤት ላይ ማግኘት ይቻላል።

  እንቅስቃሴ በሚደረግበት ወቅት ወደ ልብ ከሚደረሰው የኦክስጂን መጠን መቀነስ ጋር በተገናኘ የሚፈጠር የደረት ህመም ሊኖርባቸው ይችላል ተብለው የሚጠረጠሩ ወይም ለልብ እና የደም ቧንቧ ሥርዓት የጤና ችግሮች አጋላጭ ሆኔታዎች ያሉባቸው እና መንቀሳቀስ ወይም በመሮጫ ማሽን ላይ በመሮጥ የኤሌክትሪካርዲዮግራም ምርመራ ማድረግ የማይችሉ ሰዎች የልብ ጡንቻ እንዲኮማተር ወይም የልብን የመሥራት አቅም የሚጨምር መድኃኒት ለበሽተኞች ከተሰጣቸው በኋላ የኤሌክትሮካርዲዮግራም  ምርመራ በማድረግ የልብ ሴሎች የሚያስፈልጋቸውን የኦክስጂን መጠን መጨመርን ወይም የኮሮናሪ አርተሪ የልብን የደም ፍላጎት የሚያሟላ የደም ፍሰት ማስተላለፍ መቻል እና አለማቻሉን ከኤሌክትሮካርዲዩግራም የምርመራ ውጤት ላይ ማግኘት ይቻላል።

    በተጨማሪም ከዚህ በፊት በተደረገላቸው ምርመራ ጤነኛ ያልሆነ የኤሌክትሮካርዲዮግራም  ምርመራ ውጤት ያላቸው በሽተኞች አዲስ በሚሰራው የኤሌክትሮካርዲዮግራም  ምርመራ የሚከሰተውን አዲስ ለውጥ በትክክል ለመረዳት አስቸጋሪ ስለሚሆን የኢኮካርዲዩግራም (echocardiography) ምርመራ ማስራት አስፈላጊ ሊሆን ይችላል።