16.1.3. ወደ ልብ ከሚደረሰው የኦክስጂን መጠን መቀነስ ጋር በተገናኘ የሚፈጠር የከፋ የልብ የጤና ችግር (myocardial infarction)
ወደ ልብ ከሚደረሰው የኦክስጂን መጠን መቀነስ ጋር በተገናኘ የሚፈጠር የከፋ የልብ የጤና ችግር መከሰቱን ለማወቅ በሽተኛው የሚያሳያቸው ምልክቶችን እና የስሜት ለውጦችን፣ በኤሌክትሮካርዲዮግራም ምርመራ የሚገኘውን ውጤት እና በልብ ሴሎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት በሚደርስብት ወቅት ከልብ ሴሎች የሚለቀቁ ኬሚካሎችን መጠን መለካት አስፈላጊ ይሆናል።
በተጨማሪም የኢኮካርዲዮግራም ምርመራን ፣ በአንገት ወይም በብሽሽት አካባቢ በሚገኙ የደም ቧንቧዎች በኩል ቀጭን ቧንቧ ወይም ካቴተር በማሳለፍ እና በልብ ክፍሎች ውስጥ በመድረስ የልብ የጤንነት ሆኔታን ለማወቅ የሚደረግ ምርመራን ወይም የካርዲያክ ካቴተራይዜሽን ምርመራ (/cardiac catheterization) እንዲሁም በደም ሥር በኩል የሚሰጡ ጭረር አምንጭ ኬሜካሎችን በመጠቀም የልብን የጤንነት ሆኔታ ለማወቅ የሚደረግ ምርመራን (radionuclide scintigraphy) እና ሌሎች የምርመራ ዓይነቶችን ማድረግ አስፈላጊ ሊሆን ይችላል።
በድንገት የሚከሰት ከፍተኛ የሆነ በደረት ላይ የሚሰማ ህመም ፣ በግራ በኩል ወደሚገኘው አንገት ፣ ክንድ ፣ ትከሻ ፣ ፊት እና ጀርባ የሚሰራጭ ህመም ከኮሮናሪ አርተሪ መጥበብ ጋር በተገናኘ በልብ ሴሎች መሞት የተነሳ የተወሰነ የልብ ጡንቻ ክፍል በቋሚነት ተግባሩን በማያከናውንበት ደረጃ ላይ የሚያደርስ ጉዳት በሚከሰትበት ወቅት የሚፈጠሩ ምልክቶች ናቸው። በደረት ላይ ከሚፈጠረው ህመም በተጨማሪ የማቅለሽለሽ ፣ የማስታወክ እና በላብ መጠመቅ እንዲሁም የትንፋሽ ማጠር ሊከሰት ይችላል።
በልብ ሴሎች ላይ የሚፈጠረው ጉዳት ከፍተኛ ደረጃ ላይ በሚደርስበት ወይም በልብ ሴሎች ላይ ሞትን የሚያስከትል ጉዳት በሚፈጠርበት ወቅት በደረት ላይ የሚፈጠረው ህመም ቢያንስ ከሀያ ደቂቃዎች በላይ የሚቆይ ይሆናል። በደረት ላይ የሚፈጠረው ህመም እረፍት በሚደረግበት ወይም የኮሮናሪ አርተሪዎች እንዲስፉ የሚያደርጉ መድኃኒቶች በሚወስዱበት ወቅት የህመሙ ደረጃ የሚቀንስ ወይም የሚጠፋ አይሆንም።
አንድ አንድ ግዜ ወደ ልብ ከሚደረሰው የኦክስጂን መጠን መቀነስ ጋር በተገናኘ የሚፈጠር የከፋ የልብ የጤና ችግር (myocardial infarction) ከተከሰተ በኋላ ምንም ዓይነት ምልክት ሳያሳይ ሊቆይ እና በሌላ ግዜ የኤሌክትሮካርዲዮግራም ወይም ሌሎች ምርመራዎች በሚደረጉበት ወቅት በልብ ጡንቻ ላይ የተፈጠረው ጉዳት ሊታይ ይችላል.። ይህ ዓይነት በሽተኞች ምንም ዓይነት በደረት ላይ የሚሰማ ህመም ሳይፈጥርባቸው የሚከሰት ከኮሮናሪ አርተሪ መጥበብ ጋር በተገናኘ በልብ ሴሎች መሞት የተነሳ የልብ ክፍል በቋሚነት ተግባሩ በማያከናውንበት ደረጃ ላይ የሚያደርስ ጉዳት ህመም አልባ ወደ ልብ ከሚደረሰው የኦክስጂን መጠን መቀነስ ጋር በተገናኘ የሚፈጠር የከፋ የልብ የጤና ችግር (silent MI) ተብሎ ይጠራል። ይህ ዓይነት የልብ የጤና ችግር በብዛት የሚከሰተው በሴቶች ፣ እድሜያቸው በግፋ ሰዎች እና በስኳር በሽታ በተጠቁ በሽተኞች ላይ ሲሆን ለልብ እና ለደም ቧንቧ ሥርዓት የጤና ችግሮች ተጋላጭ በሆኑ ሰዎች ላይ በደረት ላይ የሚሰማ ህመም ሳይሆን ሌሎች እንደ አጠቃላይ የሰውነት የድካም ስሜት ፣ የማቅለሽለሽ ስሜት ፣ በጀርባ ላይ የሚከሰት ህመም እና ያልተለመደ የሆድ ህምም ስሜት ያሉ ምልክቶች በሚፈጠሩበት ወቅት ህመም አልባ ወደ ልብ ከሚደረሰው የኦክስጂን መጠን መቀነስ ጋር በተገናኘ የሚፈጠር የከፋ የልብ የጤና ችግር አለመከሰቱን ለማረጋጋጥ ጥልቀት ያለው ምርመራን ማደርግ አስፈላጊ ይሆናል።
ወደ ልብ ከሚደረሰው የኦክስጂን መጠን መቀነስ ጋር በተገናኘ የሚፈጠር የከፋ የልብ የጤና ችግር በሚከሰትበት ወቅት በኤሌክትሮካርዲዩግራም ምርመራ ውጤት ላይ ለውጥ እንዲከሰት ያደርጋል። በልብ ግድግዳ የተለያዩ ክፍሎች ውስጥ በሚገኙ ሴሎች ላይ በሚከሰተው ጉዳት መጠን መሰረት በኤሌክትሮካርዲዮግራም ምርመራ በሚገኘው ውጤት መሰረት የሚለያይ ነው። በተጨማሪም በልብ ሴሎች ላይ ጉዳት በተከሰተበት ወቅት እና የኤሌክትሮካርዲዮግራም ወይም ሌሎች ምርመራዎች በሚሰሩበት መካከል በሚኖረው የግዜ ልዩነት መሰረት በኤልክትሮካዲዮግራም ምርመራ የሚገኘው ውጤትም ሆነ የልብ ሴሎች ላይ የከፋ ጉዳት መከሰትን ተከትሎ ወደ ደም ውሰጥ የሚሊቀቁ ኬሚካሎች ወይም ፕሮቲኖች መጠን የተለያየ ሊሆን ይችላል።
ወደ ልብ ከሚደረሰው የኦክስጂን መጠን መቀነስ ጋር በተገናኘ የሚፈጠር የከፋ የልብ የጤና ችግር በሚፈጠርበት ወቅት በኤሌክትሮካርዲዩግራም ምረምራ ውጤት ላይ የ ኤስ ቲ (ST) ሴግመንት ለውጥ እንዲታይ ያደርጋል። ወደ ልብ ከሚደረሰው የኦክስጂን መጠን መቀነስ ጋር በተገናኘ የሚፈጠር የከፋ የልብ የጤና ችግር ከፍተኛ ወይም መካከለኛ መጠን ባለቸው የኮሮናሪ አርተሪዎች ውስጥ በሚከሰት የደም ፍሰት መዘጋት፣ የልብ ግድግዳን ከውጭኛው እስከ ውስጠኛው ክፍል ወይም በእንድ የተወሰነ የልብ ክፍል ውስጥ የሚገኝ የልብ ግድግዳ ላይ ሙሉ ለሙሉ ጉዳት በሚያስከትልበት ወቅት በኤሌክትሮካርዲዮግራም ምርመራ የ ኤስ ቲ (ST) ሴግመንት ከፍ ማለት (ST elevation) እንዲፈጠር ያደርጋል።
ወደ ልብ ከሚደረሰው የኦክስጂን መጠን መቀነስ ጋር በተገናኘ የሚፈጠር የከፋ የልብ የጤና ችግር የልብ ጡንቻን የውስጠኛ ክፍልን ብቻ ወይም በመጠን በጣም ትንሽ በሆነ የኮሮናሪ አርተሪ ቅርንጫፍ ውስጥ የሚከሰት የደም ፍሰት መዘጋት በውስጠኛው የልብ ግድግዳ ክፍል ላይ ብቻ ጉዳት በሚያደርስበት ወቅት ደግሞ የ ኤስ ቲ (ST) ሴግመንት ዝቅ ማለት (Non ST elevation) አንዲከሰት ያደርጋል። በተጨማሪም ከኮሮናሪ አርተሪ ሙሉ በሙሉ መዘጋት ጋር በተገናኘ በልብ ሴሎች ላይ የሚከሰት ጉዳት የ ቲ (T) ሞገድ መገልበጥ (inverted T wave) ወይም የሰፋ የ ኪው (Q) ሞገድ (wide Q wave) እንዲፈጠር ሊያደርግ ይችላል።
የ ኤስ ቲ (ST) ሴግመንት ከፍ ማለት (ST elevation) በሚታይበት ወቅት በሴሎች ላይ የሚፈጠረው ጉዳት እየቀጠለ መሆኑን ስለሚያሳይ በአፋጣኝ የተዘጋውን የደም ቧንቧ ለመክፈት ህክምና ማግኘት አጅግ በጣም አስፈላጊ ይሆናል።
ከኤልክትሮካርዲዮግራም ምርመራ በተጨማሪ ሌላው ለልብ እና ለደም ቧንቧ ሥርዓት የጤና ችግሮች ተጋላጭ በሆኑ ሰዎች ላይ ወደ ልብ ከሚደረሰው የኦክስጂን መጠን መቀነስ ጋር በተገናኘ የሚፈጠር የከፋ የልብ የጤና ችግር መከሰቱ በሚጠረጠርበት ወቅት የሚታዘዝ ምርመራ፣ ከልብ ሴሎች ውስጥ የሚለቀቀውን እና በደም ውስጥ የሚገኘውን የትሮፖኒን እና የሌሎች ኬሚካሎችን መጠን ለማወቅ የሚደረግ ምርመራ ነው።
ወደ ልብ ሴሎች የሚደረሰው የደም ወይም የኦክስጂን መጠን ሙሉ በሙሉ በሚቋረጥበት እና የልብ ሴሎች እረት ወይም ሞት በሚከሰትበት ወቅት ከልብ ሴሎች የሚለቀቁት በደም ውስጥ የሚገኙት የትሮፖኒን (troponin) ፣ ማይግሎቢን (myoglobin)፣ ክሪአቲን ካይኔስ (creatine kinase) እና ላክቴት ዲሃይድሮጂኒስ (lactate dehydrogenase) ተብለው የሚጠሩ ኬሚካሎች መጠን በከፍተኛ መጠን የሚጨምር ይሆናል። የእነዚህ ኬሚካሎች መጠን በደም ውስጥ መጨመር የልብ ሴሎች ወይም በሌሎች ሴሎች ላይ አየደረሰ ያለውን ጉዳት ሊያሳይ ይችላል። ከላይ ከተገለጹት ኬሜካሎች ውስጥ በተለይም የትሮፖኒን (Troponin I & Troponin T) እና በልብ ሴሎች ውስጥ የሚመረተው የክሪአቲን ካይኔስ ( CK – BM) ኬሜካሎች በልብ ሴሎች ውስጥ ብቻ ስለሚመረቱ የእነዚህ ኬሚካሎች መጠን በደም ውስጥ በከፍተኛ መጠን መገኘት በልብ ሴሎች ላይ የደረሰውን ጉዳት የሚያሳይ ይሆናል።
በልብ ሴሎች ውስጥ የሚመረተው የክሪአቲን ካይኔስ (CK -MB) ኬሜካል በልብ ሴሎች ላይ በሚከሰት ጉዳት ምክንያት ከተመረተ በኋላ በደም ውስጥ የሚኖረው መጠን በጥቂት ቀናት ውስጥ የሚቀንስ ይሆናል። በተቃራኒው የትሮፖኒን ኬሚካል መጠኑ በልብ ሴሎች ውስጥ ከሚመረተው የክሪአቲን ካይኔስ ዘግይቶ በደም ውስጥ የሚጨመር ቢሆንም ለብዙ ቀናት መጠኑ በደም ውስጥ እንደጨመረ የሚቀጥል ይሆናል። የትሮፖኒን ኬሚካል በልብ ሴሎች ውስጥ ከሚመረተው የክሪአቲን ካይኔስ በተሻለ ሆኔታ ወደ ልብ ከሚደረሰው የኦክስጂን መጠን መቀነስ ጋር በተገናኘ የሚፈጠር የከፋ የልብ የጤና ችግር (myocardial infarction) መከሰቱን ለማወቅ የሚረዳ ኬሚካል ሲሆን በደም ውስጥ የሚቆየው ለረጅም ቀናት ስለሆነ አዲስ ወይም እንደገና የተከሰተ ወደ ልብ ከሚደረሰው የኦክስጂን መጠን መቀነስ ጋር በተገናኘ የሚፈጠር የከፋ የልብ የጤና ችግር መከሰቱን ለማወቅ ብዙም አይጠቅምም።
በተቃራኒው ከኮሮናሪ አርተሪ ሙሉ በሙሉ መዘጋት ጋር በተገናኘ በልብ ሴሎች ላይ ለሚፈጠር የከፋ ጉዳት ተገቢውን ህክምና ከተሰጣቸው በኋላ እንደገና በድንገት በደረት ላይ የሚሰማ ህመም በሚከሰትበት ወይም የበሽተኛው የጤንነት ሆኔታ በማይሻሻልበት ወቅት በልብ ሴሎች ውስጥ የሚመረተው ክሪአቲን ካይኔስ አዲስ ወይም በድጋሚ የተከሰተ ወደ ልብ ከሚደረሰው የኦክስጂን መጠን መቀነስ ጋር በተገናኘ የሚፈጠር የከፋ የልብ የጤና ችግር መከሰቱን ለማወቅ የሚረዳ ኬሚካል ነው ።

ምስል 16 ክልብ ሴሎች የሚለቀቁ ኬሚካሎች በደም ውስጥ የሚጨምርበት እና የሚቀንስበት ሆኔታ
ወደ ልብ ከሚደረሰው የኦክስጂን መጠን መቀነስ ጋር በተገናኘ የሚፈጠር የከፋ የልብ የጤና ችግር በኮሮናሪ አርተሪ ግድግዳ ላይ ከሚፈጠር የስብ ክምችት በተጨማሪ በሰውነት ውስጥ የሚገኘው የደም መጠን ወይም የፈሳሽ መጠን በከፍተኛ መጠን እንዲቀንስ በሚያደርጉ ሆኔታዎች ፣ በደም ውስጥ የሚገኘው የኦክስጂን መጠን በከፍተኛ መጠን እንዲቀንስ ከሚያደርጉ የጤና ችግሮች ወይም ሆኔታዎች ፣ የኮሮናሪ አርተሪ ጡንቻ እንዲኮማተር በሚያደርጉ አንደ ኮኬይን ያሉ መድኃኒቶች እና የኮሮናሪ አርተሪ በሌሎች የደም ቧንቧዎች ውስጥ በተፈጠሩ የስብ ከምችቶች ወይም የደም መርጋት ስብርባሪዎች መዘጋት (emboli) የተነሳ ሊፈጠር ይችላል።