17.1.1 በሚትራል በር ላይ የሚከሰተየ የልብ የጤና ችግሮች (Mitral valve problems)
የሚትራል በር በግራ አትሪየም እና በግራ ቬንትሪክል የሚገኝ የልብ በር ሲሆን በልብ ውስጥ ከሚገኙ የተለያዩ በሮች መካከል በተደጋጋሚ ለጉዳት የሚጋለጠው የልብ በር የሚትራል በር ነው። በሚትራል በር ላይ ሦስት ዓይነት የጤና ችግሮች ሊከሰቱ ይችላሉ። እነዚህም የሚትራል በር መጥበብ (mitral stenosis) ፣ የሚትራል በር በትክክል መዘጋት አለመቻል (mitral regurgitation) እና የሚትራል በር ከሚገኘበት ትክክለኛ ቦታ በመነሳት በአትሪየም ውስጥ መገኝት (mitral valve prolapse) ናቸው።