16.1.1.3. የሚትራል በር በአትሪየም ውስጥ መገኝት (mitral valve prolapse)
የሚትራል በር ትክክለኛ መገኛ ክፍል በአትሪየም እና በቬንትሪክል መካከል በሚገኘው ግድግዳ ላይ ነው። የሚትሪል በር በእትሪየም ውስጥ መገኘት ከ 2 -3 በመቶ በሚሆኑ ሰዎች ላይ ሊከሰት የሚችል የልብ የጤና ችግር ሲሆን በተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ውስጥ ከሚከሰቱ ሌሎች የጤና ችግሮች ጋር አብሮ ሊከሰት ይችላል። የሚትራል በር በአትሪየም ውስጥ መገኝት የተነሳ የሚከሰት የልብ የጤና ችግር ብዙውን ግዜ ምንም ዓይነት ምልክት እና ለውጥ ሳያስይ ለረጅም ግዜ መቆየት የሚችል የጤና ችግር ነው። ምልክት የሚያሳዩም ከሆነ ብዙ ግዜ የሚታየው ምልክት የልብ ምት መዛባት ነው። በአካላዊ ምርመራ ወቅት ጤነኛ ያለሆነ የልብ ምት ድምጽ (systolic click) የሚሰማ ይሆናል።
የሚትራል በር በእትሪየም ውስጥ መገኘት አንድ አንድ ግዜ የከፋ የጤና ችግር ሊያስከትል ይችላል። የሚትራል በር በእትሪየም ውስጥ መገኘት ከሚያስከትላቸው የከፉ የጤና ችግሮች መካከል የልብ ምት መዛባት ፣ ከልብ የጤና ችግር ጋር በተያያዘ በድንገት የሚከሰት ሞት ፣ የልብ ድካም በሽታ ፣ በልብ ውስጥ የሚፈጠር ኢንፌክሽን ፣ በሚትራል በር ላይ የሚፈጠር የካልሲየም መከማቸት (calcification of valves) ፣ ወደ አንጎል የሚደርሰው የደም ፍሰት መቋረጥ የተነሳ ለጥቂት ሰዓታት የሚቆይ በአንጎል ክፍሎች ላይ የሚስከት ጉዳት (transient ischemic attack / TIA) እና የመሳሰሉት ሆኔታዎች ሊከሰቱ ይችላሉ።
የሚትራል በር በእትሪየም ውስጥ መከሰትን በኢኮካርዲዩግራም ምርመራ ማወቅ የሚቻል ሲሆን ቬንትሪክል በሚኮማተርበት ወቅት የሚትራል በር ወደ አትሪየም ውስጥ ሲገባ የሚታይ ይሆናል። ለሚትራል በር በእትሪየም ውስጥ መገኘት የልብ የጤና ችግር ብዙሁን ግዜ ምንም ዓይነት ህክምና አያስፈልገውም።
የልብ ምት መሰማት (palpitation) ወይም የልብ ምት ፍጥነት በከፍተኛ መጠን በሚጨምርበት ወቅት በልብ ሴሎች ሽፋን ላይ የሚገኙ የቤታ በሮችን የሚዘጉ መድኃኒቶችን (Beta blockers) መጠቀም ሊያስፈልግ ይችላል። አንድ አንድ ግዜ በቀዶ ጥገና ህክምና የሚትራል በርን በሰው ሰራሽ በር መቀየር አስፈላጊ ሊሆን ይቻላል።