Course Content
ምዕራፍ አሥራ አራት : በልብ እና በደም ቧንቧ ሥርዓት አፈጣጠር ሂደት ወቅት የሚፈጠሩ የጤና ችግሮች
0/16
ምዕራፍ አሥራ አምሥት : ከልብ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ ጋር በተገናኘ የሚፈጠሩ የልብ የጤና ችግሮች (Cardiac electrical system abnormalities)
0/16
ምዕራፍ አስራ ሰባት : በልብ በሮች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Valvular heart diseases)
0/16
ምዕራፍ ሃያ አንድ : የልብ ድካምበሽታ (Heart failure )
0/1
ምዕራፍ ሃያ ሦስት : በደም ቧንቧዎች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Vascular diseases)
0/22
በልብ እና በደም ቧንቧ ሥር ዓት ክፍሎች ውስጥ ሊፈጠሪ የሚችሉ የጤና ችግሮች (Pathology of Cardiovascular System)

17.1.2. በትራይካስፒድ በር ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Tricuspid valve problems) 

   በትራይካስፒድ በር ላይ የሚክሰቱ የጤና ችግሮች ከሌሎች በልብ በሮች ላይ ከሚከሰቱ የልብ የጤና ችግሮች ጋር ሲነጻጻር የመከሰት እድሎ በጣም አነስተኛ ነው። በትራይካስፒድ በር ላይ የሚከሰቱ የልብ የጤና ችግሮች ብዙሁን ግዜ የሚከሰቱት ከሌሎች የጤና ችግሮች ጋር በተገናኘ ነው። 

   ከስትሪፕቶኮካል ባክቲሪያ ኢንፌክሽን ጋር በተገናኘ በሰውነት የበሽታ መከላኪያ ፕሮቲኖች የተነሳ በልብ በሮች ላይ የሚክሰት ጉዳት እንዲሁም በተለያዩ የጤና ችግሮች የተነሳ የቀኝ ቬንትሪክል ከመጠን በላይ እንዲለጠጥ ወይም እንዲሰፋ የሚያደርጉ የጤና ችግሮች ዋንኞቹ በትራይካስፒድ በር ላይ ጉዳት እንዲከሰት የሚያደርጉ የጤና ችግሮች ናቸው። በትራይካስፒድ በር ላይ የሚከሰቱ ጉዳቶች የትራይካስፒድ በር መጥበብ ወይም የትራይካስፒድ መዘጋት አለመቻል የልብ የጤና ችግር ሊያስከትሉ ይችላሉ።