Course Content
ምዕራፍ አሥራ አራት : በልብ እና በደም ቧንቧ ሥርዓት አፈጣጠር ሂደት ወቅት የሚፈጠሩ የጤና ችግሮች
0/16
ምዕራፍ አሥራ አምሥት : ከልብ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ ጋር በተገናኘ የሚፈጠሩ የልብ የጤና ችግሮች (Cardiac electrical system abnormalities)
0/16
ምዕራፍ አስራ ሰባት : በልብ በሮች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Valvular heart diseases)
0/16
ምዕራፍ ሃያ አንድ : የልብ ድካምበሽታ (Heart failure )
0/1
ምዕራፍ ሃያ ሦስት : በደም ቧንቧዎች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Vascular diseases)
0/22
በልብ እና በደም ቧንቧ ሥር ዓት ክፍሎች ውስጥ ሊፈጠሪ የሚችሉ የጤና ችግሮች (Pathology of Cardiovascular System)

17.1.3.1. የትልቁ ደም ቅዳ ቧንቧ በር መጥበብ (Aortic stenosis)

  በአደጉት ሀገራት ውስጥ ዋና የትልቁ ደም ቅዳ ቧንቧ በር መጥበብ መነሻ ምክንያት ከእድሜ መግፋት ጋር በተገናኘ በትልቁ ደም ቅዳ በር ላይ የሚፈጠር የካልሲየም ክምችት እና የትልቁ ደም ቅዳ በር ላይ የሚፈጠር ለውጥ ነው። በማደግ ላይ በሚገኙ ሀገራት ውስጥ ዋና የትልቁ ደም ቅዳ ቧንቧ በር መጥበብ መንስሄ ደ‍ግሞ በተደጋጋሚ ከሚከሰት የስትሪፕቶኮካል ባክቲሪያ ኢንፌክሽን ጋር በተገናኘ በሰውነት የበሽታ መከላኪያ ፕሮቲን በሚፈጠር ጉዳት የተነሳ በልብ በሮች ላይ የሚከሰት የጤና ችግር ነው።

  በትልቁ ደም ቅዳ ቧንቧ በር ላይ የሚፈጠረው የካልሲየም መከማቸት በጤነኛ የትልቁ ደም ቅዳ ቧንቧ በር ላይ ወይም በልብ አፈጣጠር ሂደት ወቅት በሚከሰተው የትልቁ ደም ቅዳ ባለሁለት ካስፕ ወይም ተካፋች (Bicuspid) በር ላይ ሊከሰትም ይችላል። የትልቁ ደም ቅዳ ቧንቧ ባለሁለት ካስፒድ በር ላይ የሚከሰት የካልሲየም ክምችት ቀስ በቀስ የሚፈጠር እና እድሜያቸው በገፋ ሰዎች ላይ የሚታይ የሚትራል በር መጥበብ ዓይነት ነው። ከስትሪፕቶኮካል ባክቲሪያ ኢንፌክሽን ጋር በተገናኘ በልብ በሮች ላይ የሚከሰት የጤና ችግር ደግሞ በዋናነት የሚከሰተው በልጆች እና በወጣቶች ላይ ነው።

   የትልቁ ደም ቅዳ ቧንቧ በር መጥበብ በቬንትሪክል ውስጥ የሚገኘው ደም ወደ ትልቁ ደም ቅዳ ቧንቧ ውስጥ እንዳይገባ ስለሚያደርግ በጠበበው የትልቁ ደም ቅዳ በር በኩል ደምን ለማሳለፍ የግራ ቬንትሪክል ጡንቻ በከፍተኛ መጠን መኮማተርን ተከትሎ በግራ ቬንትሪክል ውስጥ የሚገኝው የግፊት መጠን በከፍተኛ ደረጃ የሚጨምር ይሆናል።

 የትልቁ ደም ቅዳ ቧንቧ በር መጥበብ ቀስ በቀስ በሚፈጠርበት ወቅት የግራ ቬንትሪክል ግድዳ በመወፈር በጠበበው በር በኩል በቂ የሆነ የደም መጠን ለማሳለፍ የሚያስችል ብቃታ እንዲያገኝ ያስቸለዋል። በጠበበው የትልቁ ደም ቅዳ ቧንቧ በር  በኩል ደምን ለመግፋት የሚያስችል የግራ ቬንትሪክል ግድግዳ መወፈር እና በከፍተኛ መጠን መኮማተር የልብ ሴሎች የሚያስፍልጋቸው የኦክስጂን መጠን እንዲጨምር ያደርጋል። በዚህም የተነሳ ወደ ልብ ሴሎች የሚደረስው የኦክስጂን መጠን ለልብ ሴሎች ከሚያሰፈልጋቸው መጠን ጋር አለመጣጣም ጋር በተገናኘ የሚፈጠር የልብ የጤና ችግር (ischemia) እንዲከሰት ሊያደርግ ይችላል። ስለሆነም የትልቁ ደም ቅዳ ቧንቧ በር መጥበበ የልብ የጤና ችግር ያለባቸው ሰዎች በተደጋጋሚ የሚከሰት በደረት ላይ የሚሰማ ህመም (angina) ሊከሰትባቸው ይችላል። የትልቁ ደም ቅዳ ቧንቧ በር መጠበብ ከፍተኛ ደረጃ ላይ በሚደርስበት ወቅት በያአንድ አንዱ የቬንትሪክል መኮማተር ወቅት ከልብ የሚረጨው የደም መጠን በከፍተኛ ደረጀ እንዲቀንስ በማድረግ በግራ የልብ ክፍል ላይ የሚክሰት የልብ ድካም በሽታ እንዲከሰት ሊያደርግ ይችላል።

የትልቁ ደም ቅዳ ቧንቧ በር መጠበብ የልብ የጤና ችግርን ተክትሎ ሊከሰቱ ከሚችሉ ምልክቶች እና ለውጦች መካከል በተደጋጋሚ የሚከሰት በደረት ላይ የሚሰማ ህመም ፣ በያአንደ አንዱ የቬንትሪክል መኮማተር ወቅት ከልብ የሚረጨው የደም መጠን መቀንስን ተክትሎ ወደ አንጎል የሚደረሰው የደም መጠን ስለሚቀንስ በድንገት የሚከሰት እራስን መሳት (syncope) ፣ በተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ውስጥ የሚከሰተው የደም ቧንቧ ትርታ ሞገድ ደካማ እና የዘገየ መሆን (pulsus tardus et parvus) ፣ በካሮቲድ አርተሪ ውስጥ የሚሰማ ጤነኛ ያልሆነ ድምጽ እና ሲነካካ የሚሰማ የንዝረት ስሜት (carotid thrill) ፣ በትልቁ ደም ቅዳ ቧንቧ በር ውስጥ የሚሰማ ጤነኛ ያለሆነ የልብ ድምጽ (systolic murmur) እንዲሁም ዓይነት አራት ተጨማሪ የልብ ድምጽ (S4)  የመሳስሉት ምልክቶች ሊታዩ ይችላሉ።

   የትልቁ ደም ቅዳ ቧንቧ በር መጥበብ የልብ ጤና ችግር መፈጠሩን ለማወቅ ከሚረዱ የምርመራ መንገዶች  መካከል የኢሌክትሮካርዲዮግራም ምርመራ የግራ ቬንትሪክል መወፈርን ሊያሳይ ይችላል። 

 የደረት ራጅ ምርመራ የካልሲየም ክምችትን ፣ የልብ መጠን መጨመርን እና የተገታተሩ የፑልሞናሪ የደም ቧንቧዎችን ሊያሳይ ይችላል። የኢኮካርዲዩግራም ምርመራ የትልቁ ደም ቅዳ ቧንቧ በር መወፈር ፣ ከቬንትሪክል የሚረጨው የደም መጠን መቀነስን እና የግራ ቬንትሪክል መወፈርን ሊያሳይ ይችላል። 

የትልቁ ደም ቅዳ በር መጠበብ ዋንኛ ህክምና የተጎዳውን በር መቀየር ነው።