16.1.4. በፑልሞናሪ አርተሪ በር ላይ የሚክሰቱ የጤና ችግሮች (Pulmonary valve problems)
አብዛኛዎቹ በፑልሞናሪ አርተሪ በር ላይ የሚከሰቱ የልብ የጤና ችግሮች በልብ አፈጣጠር ሂደት ወቅት የሚፈጠሩ የልብ የጤና ችግሮች ናቸው። በተጨማሪም የግራ ቬንትሪክል ከመጠን በላይ በሚለጠጥበት ወቅት ወይም በልብ አፈጣጠር ሂደት ወቅት የልብ የጤና ችግሮችን ለማከም የቀዶ ጥገና ህክምና በሚደረግብት ወቅት በፑልሞናሪ በር ላይ በሚፈጠር ጉዳት የተነሳ ሊሆን ይቻላል። ዋንኞቹ በፑልሞናሪ በር ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች የፑልሞናሪ አርተሪ በር መጥበብ እና የፑልሞናሪ አርተሪ በር መዘጋት አለመቻል ናቸው።