Course Content
ምዕራፍ አሥራ አራት : በልብ እና በደም ቧንቧ ሥርዓት አፈጣጠር ሂደት ወቅት የሚፈጠሩ የጤና ችግሮች
0/16
ምዕራፍ አሥራ አምሥት : ከልብ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ ጋር በተገናኘ የሚፈጠሩ የልብ የጤና ችግሮች (Cardiac electrical system abnormalities)
0/16
ምዕራፍ አስራ ሰባት : በልብ በሮች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Valvular heart diseases)
0/16
ምዕራፍ ሃያ አንድ : የልብ ድካምበሽታ (Heart failure )
0/1
ምዕራፍ ሃያ ሦስት : በደም ቧንቧዎች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Vascular diseases)
0/22
በልብ እና በደም ቧንቧ ሥር ዓት ክፍሎች ውስጥ ሊፈጠሪ የሚችሉ የጤና ችግሮች (Pathology of Cardiovascular System)

19.4 በረጅም ጊዜ ወሰጥ የሴረስ ፔሪካርዲየም መወፈር ወይም መጠንከር የሚያሰከትል የፔሪካርዲየም ብግነት  (Constrictive pericarditis)

  ይህ ዓይነት በሴረስ ፔሪካርዲየም ላይ የሚከሰት የጤና ችግር የሚፈጠረው በፔሪካርዲየም ላይ የሚከሰት ኢንፌክሽን ወይም ብግነት ያለበቂ ህክምና ለረጅም ግዜ በሚቆይበት እና የሴረስ ፔሪካርዲየም ከሚገባው መጠን በላይ መወፈር ፣ መጠንከር ፣ የውጭኛው እና የውስጠኛው ፔሪካርዲየሞች እርስ በእርሳቸው መጣበቅ ወይም  በፔሪካርዲየሞች ላይ የካልሲየመ‍እ መከማቸት በሚፈጠርበት  ወቅት ነው። ይህ በሚሆንበት ወቅት የሴረስ ፔሪካርዲየም በትክክል ተግባሩን ማከናወን ስለማይችል በልብ የመለጠጥ እና የመኮማተር አቅም ላይ እክል ወይም ችግር የሚፈጠር ይሆናል።

በፍጥነት የሚከሰት የፔሪካርዲየም ብግነት እንዲፈጠር የሚያደርጉ ሆኔታዎች አንድ አንድ ግዜ ለረጅም ወራት እና ዓመታት የሚቆይ የፔሪካርዲየም ብግነት እንዲከሰት ሊያደርጉ ይችላሉ። ለረጅም ግዜ የሚቆይ የልብ ሽፋን ብግነት ወይም ኢንፌክሽን እንዲፈጠር በማድረግ የልብ ደምን የመቀበል እና የመርጨት ተግባርን በሚገድብ መልኩ የፔሪካርዲየም መጠንከር እና መወፈር ከሚያስክትሉ ሆኔታዎች መካከል የሳንባ ነቀርሳ ወይም የቫይርስ ኢንፌክሽን ፣ ለጨርር መጋለጥ ፣ በልብ ላይ የሚደረግ የቀዶ ጥገና ህክምና ፣ ሰር ከሰደደ የኩላሊት በሽታ ጋር በተገናኘ በደም ውስጥ የሚገኘው የዩሪያ ናይትሮጂን መጠን በከፍተኛ መጠን መጨመር  ፣ ወደ ልብ ሴሎች የሚደርሰው የደም ወይም የኦክስጂን መጠን መቀነስን ተከትሎ በልብ ጡንቻ ላይ የሚከሰት ጉዳት እና ሌሎች በተለያዩ የሰውነት ክፍሎች እና በፔሪካርዲየም ላይ ብግነት እንዲፈጠር የሚያደርጉ ከሰውነት የበሽታ መከላኪያ ሥርዓት ጋር የተገናኙ የጤና ችግሮች ዋንኞቹ ናቸው።  

በረጅም ጊዜ ወሰጥ የፔሪካርዲየም መወፈር ወይም መጠንከር የሚያሰከትል የፔሪካርዲየም ብግነት መፈጠር ጋር በተገናኘ ሊከሰቱ ከሚችሉ ምልክቶች እና ለውጦች መካከል የትንፋሽ ማጠር ፣ የድካም ስሜት መሰማት ፣ የልብ ምት ፍጥነት መጨመር ፣ የልብ ምት መሰማት ፣ የሆድ ህመም ፣ በሆድ እቃ ውስጥ የፈሳሽ መጠራቀም ፣ የጉበት እና የቆሽት መጠን መጨመር ፣ የእግር እብጠት ፣ በአንገት አካባቢ የሚገኙ የደም መልስ ቧንቧዎች መገታተር እንዲሁም አየር ወደ ሳንባ በሚገባበት ወቅት በአንገት አካባቢ በሚገኙ የደም ቧንቧዎች ላይ የሚታየው የመገታተር ወይም በአንገት አካባቢ በሚገኙ የደም መልስ ቧንቧዎች ውስጥ የሚፈጠረው የግፊት መጠን መጨመር (Kussmaul’s sign) የሚታዩ ይሆናል። 

በኤሌክትሮካርዲዮግራም ምርመራ የቲ (T) ሞገድ አለመኖር ሊታይ የሚችል ሲሆን በደረት ራጅ ምርመራ ደግሞ በፔሪካርዲየም ላይ የተከማቸ ካልሲየም ሊታይ ይችላል። በኢኮካርዲዮግራም ምርመራ ፣ በኮምፒዮትድ ቶሞግራፊ ( CT ) ወይም በኤም አር አይ (MRI) ምርመራ የሴረስ የፔሪካርዲየም መወፈርን መለየት ይችላል።

  በረጅም ጊዜ ወሰጥ የፔሪካርዲየም መወፈር ወይም መጠንከር የሚያሰከትል የፔሪካርዲየም ብግነትን ለማከም ፈሳሽ ከሰውነት እንዲወገድ የሚያደርጉ መድኃኒቶችን መጠቀም እንዲሁም በምግብ እና በመጠጥ መልክ ወደ ሰውነት የሚገባውን የጨው መጠን መቀነስ ያስፈልጋል። በተለያዩ የህክምና መንገዶች በቂ የህክምና ምላሽ በማይገኝበት ወቅት በቀዶ ጥገና ህክምና የሴረስ የልብ ሽፋንን ከሰውነት ማስወገድ ሊያስፈልግ ይችላል።