20.4. የህይወት እና የኗኗር ዘይቤን በማሻሻል የደም ግፊት መጠንን መቆጣጠር (nonpharmacologic therapy)
የደም ግፊት መጠን መጨመር መከሰቱ በሚታወቅበት ወቅት በበሽተኛው እድሜ ፣ በደም ግፊት መጠን መጨመር ደረጃ እና በሌሎች ተጓዳኝ የጤና ችግሮች ላይ በመመስረት ከሦስት አስከ ሥድሰት ወር ድረስ ውስጥ የደም ግፊት መጠን መጨመርን የህይወት እና የአኗኗር ዘይቤን በማሻሻል መቆጣጠር ይቻላል። ይህ ዓይነት የህክምና መንገድ በተለይም የደም ግፊት መጠን መጨመር በሽታ በደረጃ አንድ ላይ በሚገኘበት ወቀት ፣ የደም ግፊት መጠን መጨመርን የህይወት እና የአናኗር ዘይቤንበማሻሻል ለመቆጣጠር ከፍተኛ ፍላጎት ለሚያሳዩ ሰዎች እንዲሁም በልብ እና በደም ቧንቧ ሥርዓት ላይ ለሚከሰቱ የጤና ችግሮች እነስተኛ ተጋላጭነት ላላቸው ሰዎች ተመራጭ በቅድሚያ የሚሞከር የህክምና መንገድ ነው። የህይወት እና የአኗኗር ዘይቤን ለማሻሻል ከሚተገበሩ ሆኔታዎች መካከል የሰውነት ክብደትን መቀነስ ፣ የደም ግፊት መጠን መጨመርን ለመቆጣጠር የሚረዱ ምግቦችን መመገብ ( በምግበ እና በመጠጥ ወሰጥ ወደ ሰውነት የሚገባውን የጨው መጠን መቀነስ ፣ አትክልት እና ፍራፍሬዎችን በብዛት መመገብ ፣ ስብ ወይም ቅባት የበዛባቸውን ምግቦችን እና ስኳር የበዛባቸው ጣፋጭ ምግቦችን መቀነስ) ፣ አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ፣ የአልኮል መጠጥን መቀነስ ፣ ሲጋራ ማጤስን ማቆም ፣ በደም ውስጥ የሚገኘውን የስብ ወይም የኮሌሰትሮል መጠን መቆጣጠር ፣ በደም ውስጥ የሚገኘውን የግሎኮስ መጠን መቆጣጠር እና በህይወት ውስጥ የሚፈጠሩ ጫናዎችን እና ጭንቀትን ማስወገድ ዋንኞቹ ናቸው።
የህይወት እና የአኗኗር ዘይቤን በማሻሻል የሚሰጠውን ህክምና እና የሚያስከትለውን ውጤት በሚከተለው ሰንጠረዥ ውስጥ መመልክት ይቻላል።
|
ህክምና |
ከህክምናው የሚጠበቀው ውጤት |
የሚጠበቀው የሲስቶሊክ የደም ግፊት መጠን መቀነስ |
|
|
የሰውነት ክብደት መጠን መቀነስ |
ጤነኛ የሰውነት ክብደት ወይም ጤነኛ የሆነ የሰውነት ክብደት እና ቁመት ተነፃፃሪ መጠን ( 18 – 25 ኬሎ ግራም / ሜትር 2)
|
አንድ ኬሎ ግራም የሰውነት ክብደት መቀነስ አንድ ሚሊ ሚትር አፍ ሚርኮሪ / mmHg የደም ግፊት መጠን መቀነስ እንዲከሰት ያደርጋል። |
|
|
ምግብ
አካላዊ እንቅስቃሴ |
የደም ግፊት መጠን መጨመርን ለመቆጣጠር የሚረዳ የምግብ አይነት / Dilatory Approaches to Stop Hypertension (DASH) |
በአትክልት እና በፍራፍሬ የበለጸጉ ምግቦችን እንዲሁም ጥራጥሬዎችን መመገብ
ሳቹሬትድ / saturated እና trans saturated /ትራንስ ሳቹሬትድ የስብ አይነቶችን ማስወገድ |
11 ሚሊ ሜትር ኦፍ ሜርኮሪ ( 11 mm Hg)
|
|
የሶዲየም መጠንን መቀነስ
|
በየቀኑ የሚወሰደው የሶዲየም መጠን ከ 200 ሚሊግራም በታች እንዲሆን ማድረግ |
5 – 6 ሚሊ ሜትር ኦፍ ሜርኮሪ ( 5–6 mm Hg |
|
|
የፖታሲየም መጠንን መጨመር
|
በየቀኑ የሚወሰደው የፖታሲየም መጠን 3.5–5 g እንዲሆን ይመከራል |
4 – 5 ሚሊ ሜትር ኦፍ ሜርኮሪ (4–5 mm Hg)
|
|
|
የአልኮል መጠጥን መቀነስ
|
♂: በየቀኑ ≤ 2 መደበኛ መጠጥ ♀: በየቀኑ ≤ 1 መደበኛ መጠጥ
አልኮል መጠጥ በሚያቆሙበት ሆኔታ ላይ የምክር አገልግሉት ማግኘት
|
4 ሜትር ኦፍ ሜርኮሪ (4 mm Hg)
|
|
|
ኦክስጂን በመጠቀም የሚደረግ አካላዊ እንቅስቃሴ (Aerobic exercise) ምሳሌ፡ እርምጃ ፣ ዱብ ዱብ ማለት ፣ ሳይክል መንዳት |
በየሳምንቱ 90–150 ደቂቃዎች |
5 – 8 ሚሊ ሜትር ኦፍ ሜርኮሪ (5–8 mm Hg)
|
|
|
ጡንቻዎች እንዲሳሳቡ ወይም እንዲለጠጡ የሚያደርግ አካላዊ አንቅስቃሴ (dynamic exercise) ምሳሌ ፡ ክብደት ማንሳት
|
በየሳምንቱ ለ 90–150 ደቂቃዎች |
4 ሚሊ ሜትር ኦፍ ሜርኮሪ (4 mm Hg)
|
|
|
ጡንቻዎች እንዲኮኮማተሩ የሚያደርግ አካላዊ እንቅስቃሴ (isometric exercises) ምሳሌ ፡ ግድግዳ መግፋት |
በሳምንት ሦስት ግዜ የሚሰራ የአካል እንቅስቃሴ |
5 ሚሊ ሜትር ኦፍ ሜርኮሪ ( 5 mm Hg)
|
|
(መደበኛ የአልኮል መጠጥ / standard drinks : መደበኛ የአልኮል መጠጥ በውስጡ 14 ግራም የሆነ አልኮል የያዘ መጠጥ ማለት ነው። መደበኛ የአልኮል መጠጥ የሚባሉት 350 ሚሊ ሊትር 5 % አልኮል ቢራ ፣ 150 ሚሊ ሊትር 12 % የወይን መጠጥ ፣ 50 ሚሊ ሊትር 40% የአልኮል መጠጥ ዋንኞቹ ናቸው።)