ሀ) በፍጥነት በባክቴሪያ የተነሳ በልብ የውስጠኛ ክፍል ላይ የሚፈጠር ኢንፌክሽን (Acute bacterial endocarditis)
በፍጥነት በባክቴሪያ የተነሳ በልብ የውስጠኛ ክፍል ላይ የሚፈጠር ኢንፌክሽን ብዙሁን ጊዜ የሚከሰተው ጤነኛ የልብ በር ባላቸው ሰዎች ላይ ነው። በደም ውስጥ በመዘዋወር ወደ ልብ ውስጥ የሚደረሰው ባክቴሪያ በልብ በሮች ላይ በመከማቸት እና በመራባት በልብ በሮች ላይ ኢንፌክሽን እና ቁስለት እንዲፈጠር ያደርጋል። በቆስለቱ ላይ የተለያዩ የደም ሴሎች እና የደም አካሎች በመጣበቅ እና በመከመር ትልቅ ክምቸት (vegetation) ይፈጠራሉ። ይህም ክምችት የልብ በሮች ላይ በፍጥነት የሚከሰት ከፍተኛ ጎዳት ያደርሳል።
አንድ አንድ ጊዜ በልብ በሮች ላይ ከሚፈጠረው ትልቅ ክምቸት (vegetation) ላይ የሚነሳውየክምችት ሰብረባሪ (emboli) በደም ውስጥ በመጓዝ በተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ( በዓይን ፣ በአንጎል ፣ በኩላሊት) ውስጥ የሚገኙ በጣም ትንንሽ የደም ቧንቧዎች እንዲዘጉ ሊያደርግ ይችላል። በእነዚህ በተዘጉ ትንንሽ የደም ቧንቧዎች ደም ያገኙ የነበሩ የሰውነት ክፍሎች ላይም የከፋ የጤና ችግር ሊያስከትል ይችላል።
ይህ ዓይነት በውስጠኛው የልብ ክፍሎች ውስጥ በፍጥነት የሚከሰት የባክቲሪያ ኢንፌክሽን በብዛት የሚከሰተው ስታፊሎኮከስ አውሪስ (Staphylococcus aureus) በሚባለው ባክቴሪያ አማካኘነት ነው። በደም ሥር በኩል የሚወሰዱ አደንዛዥ ወይም አነቃቂ መድኃኒቶችን የሚጠቀሙ ሰዎች ለዚህ የጤና ችግር በከፍተኛ ደረጃ ተጋላጭ ናቸው።
በፍጥነት የሚከሰት በባክቴሪያ የተነሳ በልብ የውስጠኛ ክፍል ላይ የሚፈጠር ኢንፌክሽን የተጠቁ ሰዎች በድንገት የሚከሰት በጠና የመታመም ምልክቶችን እና ለውጦችን ያሳያሉ። ከእነዚህም ምልክቶች እና ለውጦች መካከል የሰውነት ሙቀት መጠን መጨመር ወይም ትኩሳት (fever) ፣ ብርድ ብርድ ማለት(chills and rigorous) ፣ አጠቃላይ የሆነ የሰውነት ድካም ስሜት መሰማት (fatigue) እንዲሁም ከልብ በሮች ላይ በተፈጠረው ክምችት ስብርባሪ (vegetation emboli) የተነሳ በዓይን ፣ በኩላሊት ፣ በአንጎል እና በቆዳ ክፍሎች ላይ ከሚፈጠሩ ጉዳቶች ጋር በተገናኘ የሚፈጠሩ ምልክቶች እና ለውጦች ሊከሰቱ ይችላሉ።