ለ) ቀስ በቀስ በባክቴሪያ የተነሳ በልብ የውስጠኛ ክፍል ላይ የሚፈጠር ኢንፌክሽን (Subacute bacterial endocarditis)
ቀስ በቀስ ወይም በጥቂት ሳምንታት ውስጥ በባክቴሪያ የተነሳ በልብ የውስጠኛ ክፍል ላይ የሚፈጠር ኢንፌክሽን (Subacute bacterial endocarditis) የሚፈጠረው የተለያዩ የልብ የጤና ችግሮች በተለይም በልብ በር የጤና ችግር በተጠቁ ስዎች ላይ ነው። በአፍ ውስጥ በድድ እና በጥርስ ላይ የሚደረግ ወይም በሌሎች የሰውነት ክፍሎች ውሰጥ የሚደረግ የቀዶ ህክምና በሚወሰድበት ወቅት ወደ ደም ውስጥ ለመግባት የሚችሉ ባክቴሪያዎች ወደ ልብ በሮች በመድረስ ፣ በመጣበቅ እና በመራባት እንዲሁም ከደም ሴሎቸ ጋር በመጣበቅ ትንንሽ ክምቸቶች (vegetation) እንዲፈጠሩ ያደርጋሉ። ለዚህ ዓይነት የጤና ችግር ተጋላጭ ከሚያደርጉ የልብ የጤና ችግሮች መካከል በቀኝ እና በግራ ቬንትሪክሎች መካከል የሚገኝው ግድግዳ መሸንቆር (VSD) ፣ የልብ በሮች መጥበብ (valvular stenosis) ፣ የሰው ሰራሽ የልብ በሮች ንቅለ ተከላ ህክምና የተደረገላቸው ሰዎች (Prosthetic Valves) ፣ በልብ ክፍሎች ወስጥ የተተከለ ካቴተር (indwelling catheter) የሚጠቀሙ ሰዎች፣ ሁለት ተካፋች ወይም ካፕሲዶች ያለው የትልቁ ደም ቅዳ በር መኖር (Bicuspid Aortic Valve) ፣ የሚትራል በር በአትሪየም ውስጥ መግባት እንዲሁም የማርፋን ሲንድሮም (Marfan’s syndrome ) የመሳሰሉት ዋንኞች ናቸው።
ይህ ዓይነት የልብ የጤና ችግር በብዛት የሚከሰተው ስትሪፕቶኮከስ ቪሪዳንስ (streptococcus viridans) በተባለው ባክቴሪያ አማካኝነት ነው።
ቀስ በቀስ ወይም በጥቂት ሳምንታት ውስጥ በባክቴሪያ የተነሳ በልብ የውስጠኛ ክፍል ላይ ከሚፈጠር ኢንፌክሽን ጋር በተገናኘ ሊከሰቱ ከሚችሉ ምልክቶች እና ለውጦች መካከል የሰውነት ሙቅት መጨመር ወይም ትኩሳት ፣ ብርድ ብርድ ማለት ፣ የድካም ስሜት ፣ የምግብ ፍላጎት መቀነስ ፣ የሰውነት ክብደት መቀነስ ፣ ጤነኛ ያልሆነ የልብ ምት ድምጽ መሰማት ፣ ማሳል ፣ በቆዳ ላይ የሚታዩ ልዩ ልዩ ምልክቶች እና ቁሰለቶች እንዲሁም የቆሽት ዕብጠት ወይም የቆሸት በመጠን መጨመር (splenomegaly) ዋንኞቾ ናቸው።
በትልቁ እንጀት ካንሰር በሽታ የተጠቁ ሰዎች ስትሪፕቶኮከስ ቦቪስ (streptococcus bovis) በተባለ ባክቴሪያ አማካኝነት ለሚከሰት ቀስ በቀስ ወይም በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ለሚከሰት በባክቲሪያ የተነሳ በልብ የውስጠኛ ክፍል ላይ ለሚፈጠር ኢንፌክሽን ተጋላጭነታቸው ሊጨምር ይችላል። ።
በተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ላይ ከሚታዩ የበሽታው ምልክቶች መካከል በአይን ፣ በአፍ ውስጥ ፣ በእጅ እና በእግር ላይ የሚከሰት በቆዳ ሥር ደም መድማት (petechiae) ፣ በጥፍር ላይ የሚከሰት ባለደም ቀለም መስመር (Splinter hemorrhages) ፣ በጣቶች እና በመዳፍ ላይ የሚፈጠሩ የሚያሙ ትንንሽ ዕብጠቶች (Osler’s nodes) ፣ የደም ክምችት የሚመስሉ የማያሙ በጣቶች እና በእጅ መዳፍ ላይ የሚፈጠሩ ቁስለቶች ወይም የጠቆሩ ዕብጠቶች (Janeway lesions) እንዲሁም በአይን ረቲና ክፍል የሚታዩ በደም የተከበቡ ቁስለቶች (Roth’s Spots) የመሳሰሉት ዋንኞቹ ምልክቶች ናቸው። ከላይ ከተገለጹት ምልክቶች እና ለውጦች በተጨማሪ በድንገት እና በፍጥነት ለሞት ሊያደርስ የሚችል የልብ ምት መዛባት (Arrhythmia) እና/ ወይም የልብ ድካም በሽታ (Heart failure) ሊከሰት ይችላል።
በልብ በሮች ላይ ከሚፈጠረው የባክቴሪያ መራባት እና የደም ሴሎች ክምችት (vegetations) ላይ ተቆርጠው ወይም ተቀንጥሰው የሚነሱ የክምችት ስብርባሪዎች በደም ውስጥ በመዘዋወር በተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ውስጥ የሚገኙ ትንንሽ የደም ቧንቧዎችን በመዝጋት የተለያዩ የጤና ችግሮችን ሊያስከትሉ ይችላሉ። ከእነዚህም የጤና ችግሮች መካከል በአንጎል ውሰጥ በሚገኙ የደም ቧንቧዎች ላይ የሚከሰት የደም ቧንቧዎች መዘጋት የተነሳ የሚፈጠር ስትሮክ (embolic stroke) ፣ በጣፊያ ውስጥ የሚገኙ የደም ቧንቧዎችን በመዘጋት በጣፊያ ላይ የሚደረስ ጉዳት (splenic injury) ፣ በኩላሊት ውስጥ የሚገኙ የግሎመሩለስ ካፒላሪሶችን በመዘጋት በኩላሊት ክፍሎች ላይ የሚደርስ ጉዳት (kidney injury) እንዲሁም ደምን ወደ ልብ የሚያደርሱ የደም ቧንቧዎችን ወይም የኮሮናሪ አርተሪዎችን በመዝጋት በልብ ጡንቻ ላይ የሚከሰት ጉዳትን (myocardial ischemia / infarction) ዋንኞቹ ናቸው።
በባክቴሪያ የተነሳ በልብ የውስጠኛ ክፍል ላይ ከሚፈጠር ኢንፌክሽን ጋር በተገናኘ በኩላሊት የግሉመሩለስ ካፒላሪሶች ላይ በሚፈጠር ጉዳት የተነሳ በሽንት በኩል የሚወገደው የቀይ የደም ሴሎች እና ፕሮቲን መጠን እንዲጨምር እንዲሁም በፍጥነት የሚከሰት የኩላሊት ጉዳት እና የኩላሊት መድከም (acute renal failure) እንዲፈጠር ሊያደርግ ይችላል።
በባክቴሪያ የተነሳ በልብ የውስጠኛ ክፍል ላይ የሚፈጠር ኢንፌክሽን ከልብ በሮች መካከል የሚትራል በርን የበለጠ የሚያጠቃ ሲሆን የትራይካስፒድ በር ላይ ጉዳት የሚፈጠረው በደም ሥር በኩል የሚወሰዱ አደንዛዥ ወይም አነቃቂ መድኃኒቶችን በሚጠቀሙ ሰዎች ላይ ነው።
የልብ የወስጠኛ ክፍል ላይ የሚፈጠር ብግነት ኢንፌክሽን ባልሆኑ ሆኔታዎች ከሰውነት የበሽታ መከላኪያ የልብ ክፍሎች ላይ ጉዳት ከማስከተሉ የተነሳም ሊከሰት ይችላል። በልብ የውስጠኛ ክፍል ላይ ብግነት እንዲፈጠር ሊያደርገየ ከሚችሉ ሆኔታዎች ወይም የጤና ችግሮች መካከል የተለያዩ ዓይነት የካንሰር በሸታዎች ፣ የደም መርጋት የሚያስከትሉ የጤና ችግሮች እንዲሁም በተለያዩ የሰውነት ከፍሎች ውስጥ ብግነት እንዲፈጠር የሚያደርገው የሎፐስ እሪተማተስ (systemic lupus erythematosus) በሽታ በልብ የውስኛ ክፍል በተለይም በልብ በሮች ላይ ብግነት እንዲከሰት ሊያደርጉ የሚችሉ ሆኔታዎች ወይም የጤና ችግሮች ናቸው።
በልብ የውሰጠኛ ክፍል ውስጥ ከባክቴሪያ ጋር በተገናኘ ኢንፌክሽን መፈጠሩን ለማወቅ ከሚረዱ የምርመራ መንገዶች መካከል በደም ውስጥ የሚገኘውን የደም ሴሎች ቁጥር ለማወቅ የሚደረግ ምርመራ (CBC) ፣ ከብሽተኛው ደም ላይ በሚወሰድ ናሙና በላብራቶሪ በተዘጋጀ የህዋስ ማሳደጊያ ውስጥ ባክቴሪያውን ለማሳደግ እና ኢንፌክሽን አምጭ የሆነውን ባክቴሪያ ለመለየት የሚረዳ ምርመራ (Blood culture) ፣ የኢሌክትሮካርዲዮግራም (Electrocardiogram)፣ የኢኮካርዲዮግራም ምርመራ (Echocardiogram) ፣ የደረት ራጅ ምርመራ (CXR) እንዲሁም የኮምዩትድ ቶሞግራፊ (CT) እና የ ኤም አር አይ (MRI) ምርመራ ዋንኞቹ ናቸው።
ቀስ በቀስ ወይም በጥቂት ሳምንታት ውስጥ የሚከሰት በባክቴሪያ የተነሳ በልብ የውስጠኛ ክፍል ላይ የሚፈጠር ኢንፌክሽን መከሰትን በትከክል ለመለየት ወይም ለማወቅ የሚረዱ መሥፈርቶችን መጠቀም አስፈላጊ ይሆናል። ይህም መስፈረት የዱከስ መስፈረት (Duke’s criteria) ተብሎ ይጠራል። በዱክስ መስፈርት መሰረት በበሽተኛው ላይ የሚፈጠሩ ምልክቶቸን እና ለውጦችን ፣ በኢኮካርዲዮግራም ምርመራ በሚገኘው ውጤት ፣ ከደም የሚወሰድ ናሙና በመጠቀም ኢንፌክሽን አምጭ የሆነውን ባክቴሪያ በላብራቶሪ በማሳደግ ለመለየት በሚደረግ ምርመራ በሚገኘው ውጤት ላይ በመመስረት በባክቴሪያ የተነሳ በልብ የውስጠኛ ክፍል ላይ የሚፈጠር ኢንፌክሽን መከሰቱን ለማወቅ የሚረዱ መስፈርቶች ዋና መስፈርቶች (major criteria) እና ዋና ያልሆኑ መስፈርቶች (Minor Criteria) ተብለው በሁለት ይመደባሉ።
ዋና መስፈርቶች (major criteria) ፡ ዋና መስፈርቶች የሚባሉት ከብሽተኛው ደም ላይ በሚወሰድ ናሙና በላብራቶሪ በተዘጋጀ የህዋስ ማሳደጊያ ውስጥ ባክቴሪያውን በማሳደግ ቢያንስ ሁለት ጊዜ የተረጋጋጠ (positive blood culture) ኢንፌክሽን – አምጭ የሆነውን ባክቴሪያ ለመለየት የሚያስችል ውጤት ማግኘት እንዲሁም በልብ የወስጠኛ ከፍል ውስጥ በተለይም በልብ በሮች ላይ የባክቴሪያ መራባት እና የደም ሴሎች ክምችት (vegetation) መፈጠሩን የሚያረጋግጥ የኢኮካርዲዮግራም ምርመራ ውጤት ማግኘት ናቸው። በሽታው መከሰቱ በትክከል የሚረጋገጠው ሁለቱም ዋና መስፈርቶች በአንድ ላይ ሲገኙ ነው።
ዋና ያልሆኑ መስፈርቶች (minor criteria) ፡ ከላይ ከተገለጹት ዋና መስፈርቶች መካከል አንዱ ብቻ ሲገኝ እና ከሌሎች የበሽታው ምልክቶች እና ለውጦች መካከል ሦስቱ ሲገኙ በሽታው መከሰቱን በእርግጠኝነት ማወቅ ይቻላል። ከአንድ ዋና መስፈርት ጋር በመሆን የበሽታውን መከሰት ለማወቅ ከሚረዱ ዋና ያልሆኑ መስፈርቶች ወይም ምልክቶች እና ለውጦች መካከል የሰውነት ሙቀት መጨመር ወይም ትኩሳት ፣ ለበሽታው አጋላጭ የሚሆኑ የልብ የጤና ችግሮች መኖር ፣ በደም ሥር በኩል የሚወሰዱ አደንዛዥ ወይም አነቃቂ መድኃኒቶችን መጠቀም ፣ በልብ በሮች ላይ ከሚፈጠረው የተለያዩ ሴሎች እና የደም አካላት ከምችት በመነሳት እና በተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ውሰጥ በሚገኙ ትንንሽ የደም ቧንቧዎች ላይ ጉዳት ማድረስ ጋር በተገናኘ በተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ላይ የሚታዩ ምልክቶች (vascular Phenomena) እንዲሁም ከበሽተኛው የተወሰደ ደምን በመጠቀም በሽታ አምጭ የሆነውን ባክቴሪያ በላብራቶሪ ውስጥ ለማሳደግ በሚደረግ ምርመራ ባክቴሪያውን አንድ ገዜ ብቻ መለየት መቻል ናቸው። በሽታው በትክክል መከቱን ለማወቅ ቢያንስ አንድ ዋና መስፈርት እና ሦስት ዋና ያለሆኑ መስፈርቶች ውስጥ የሚጠቃለሉ ምልክቶች እና ለውጦች መከሰት ይኖርባቸዋል።
በባክቴሪያ የተነሳ በልብ የውስጠኛ ክፍል ላይ የሚፈጠር ኢንፌክሽንን በትክክል ለማከም ኢንፌክሽን – አምጭ የሆነውን የባክቴሪያ ዓይነት ለመለየት ከደም የሚወሰድ ናሙና በመጠቀም በላብራቶሪ ማሳደግ እና ባክቴሪያውን ሊያጠፋ የሚችል ትክክለኛ ጸረ ህዋስ መድኃኒትን ለመምረጥ የሚረዳ ምርመራ (culture and sensitivity test) ማድረግ አሰፈላጊ ይሆናል።
በሽተኛው በጠና የታመመ ከሆነ ወይም በግልጽ ለሚታውቁ እና ለተወሰኑ የባክቴሪያ አይነቶች የሚያጋልጡ ሆኔታዎች ሲፈጠሩ የደም ናሙናው ለምርመራ ከተወሰደ በኃላ የላብራቶሪ ወጤትን ሳይጠብቁ አስፈላጊውን የጸረ ህዋስ መድኃኒት በአስቸኳይ መጀመር አስፈላጊ ይሆናል።
በባክቴሪያ የተነሳ በልብ የውስጠኛ ክፍል ላይ የሚፈጠር ኢንፌክሽንን ለማከም የሚሰጡ መድኃኒቶች በሽታ አምጭ የሆኑ ባክቴሪያ በትክክል መግደል የሚችሉ ፣ በደም ሥር በኩል የሚሰጡ እና ብዙሁን ጊዜ ከአንድ በላይ ጸረ ባክቴሪያ መድኃኒት በመጠቀም ሲሆን የሚሰጡት ጸረ ባክቴሪያ መድኃኒቶችም ለሳምንታት መወስድ ይኖርባቸዋል።
በልብ ወስጥ ለሚፈጠር ንፌክሽን ተጋላጭ የሆኑ ሰዎች የአፍ እና የጥርስ ንጽህናቸውን እንዲጠበቁ እንዲሁም በየግዜው የጥርስ እና የአፍ ጤንነት ክትትል እንዲያደርጉ የምክር አግልግሉት ማግኘት ይኖርባቸዋል። በተጨማሪም በሽተኞች ወይም ተጋላጭ ሰዎች ከላይ የተገለፁት በልብ የውሰጠኛ ከፍሎች ውሰጥ ከሚፈጠር ኢንፌክሽን ጋር በተገናኘ የሚፈጠሩ ምልክቶች እና ለውጦች በሚታዩባቸው ወቅት በፍጥነት ወደ ህክምና መስጫ ጣቢያ በመሄድ ምርመራ እና አሰፈላጊውን ህክምና ማግኘት ይኖርባቸዋል።