Course Content
ምዕራፍ አሥራ አራት : በልብ እና በደም ቧንቧ ሥርዓት አፈጣጠር ሂደት ወቅት የሚፈጠሩ የጤና ችግሮች
0/16
ምዕራፍ አሥራ አምሥት : ከልብ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ ጋር በተገናኘ የሚፈጠሩ የልብ የጤና ችግሮች (Cardiac electrical system abnormalities)
0/16
ምዕራፍ አስራ ሰባት : በልብ በሮች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Valvular heart diseases)
0/16
ምዕራፍ ሃያ አንድ : የልብ ድካምበሽታ (Heart failure )
0/1
ምዕራፍ ሃያ ሦስት : በደም ቧንቧዎች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Vascular diseases)
0/22
በልብ እና በደም ቧንቧ ሥር ዓት ክፍሎች ውስጥ ሊፈጠሪ የሚችሉ የጤና ችግሮች (Pathology of Cardiovascular System)

22.4 በልብ ጡንቻ ላይ የሚከሰት ኢንፌከሽን ወይም ብግነት  (Myocarditis)

በልብ ጡንቻ ላይ የሚከሰት ኢንፌክሽን ወይም ብግነት ማለት በተለያዩ መነሻ ምክንያቶች የተነሳ በፍጥነት ወይም በረጅም ግዜ ውስጥ በልብ ጡንቻ ላይ በሚፈጠር ኢንፌክሽን ወይም ብግነት የተነሳ የሚከሰት  የልብ ጡንቻ የጤና ችግር ማለት ነው።   ባደጉት ሀገራት ውስጥ ለልብ ጡንቻ ኢንፌክሽን በዋና መንስሄነት የሚጠቀሰው የቫይረስ ኢንፌክሽን ሲሆን ከእነዚህም ቫይረሶች ውስጥ አይነት 19 ፓርቮቫይረስ 19 (parvovirus 19) ፣ የኮክሳኪ ቫይረስ (coxsackievirus) እና የአዲኖ ቫይረስ (adenovirus) ዋንኛቹ ናቸው። የተለያዩ የባክቲሪያ ፣ የፈንገስ ፣ የሪኬትሺያል (Rickettsial) እና የፕሮቶዞዋ (protozoans) ዝርያዎችም በልብ ጡንቻ ላይ የሚከሰት ኢንፌክሽን ወይም ብግነት እንዲፈጠር ሊያደርጉ ይችላሉ።  

   በተጨማሪም በሰውነት ውስጥ በሚፈጠሩ የተለያዩ የጤና ችግሮች ፣ ሰውነት ለተለያዩ መድኃኒቶች በሚሰጠው የመቆጣት ምላሽ እንዲሁም ወደ ሰውነት ውስጥ በሚገቡ ወይም በሰውነት ውስጥ በሚመረቱ ቶክሲን ኬሚካሎች የተነሳ በልብ ጡንቻ ላይ ብግነት ሊፈጠር ይችላል። በልብ ጡንቻ ላይ የሚፈጠር ብግነት በአንድ የተወሰነ የልብ ግድግዳ ክፍል ላይ ወይም የልብን ጡንቻ ሙሉ በሙሉ ወይም ሁሉንም የልብ ግድግዳ ክፍሎች  የሚሸፍን ሊሆን ይችላል።

   በልብ ጡንቻ ላይ የሚከሰት ኢንፌክሽን ወይም ብግነት መነሻ በሚሆነው መንስሄው ላይ በመመሰረት ሙሉ ለሙሉ ከበሽታው ከማገገም ወይም ከመዳን ጀምሮ እስከ ሞት ሊያደርስ የሚችል የጤና ጉዳት ሊያስከትል ይችላል። አንድ አንድ ግዜ በሽተኞች ከበሽታው ካገገሙ ከረጅም ግዜ በኋላ የሚከሰት የልብ ድካም በሽታ ወይም የልብ ጡንቻ ከመጠን በላይ መለጠጥ የጤና ችግር ሊፈጠርባቸው ይችላል።

     በልብ ጡንቻ ላይ ከሚከሰት ኢንፌክሽን ወይም ብግነት ጋር በተገናኘ ሊከሰቱ ከሚችሉ ምልክቶች እና ለውጦች መካከል የሰውነት ሙቀት መጠን መጨመር ወይም ትኩሳት ፣  አጠቃላይ የህመም ስሜት መሰማት (malaise) ወይም የጤነኘንት ስሜት አለመሰማት  ፣ በደረት ላይ የሚሰማ ህመም ፣ የልብ ምት መዛባት ፣ የሰውነት ዕብጠት ፣ በጡንቻ ላይ የሚሰማ ህመም ፣ ሳል ፣ የሆድ ህመም እና ተቅማጥ ዋንኞቹ ናቸው። 

   በልብ ጡንቻ ላይ ኢንፊክሽን ወይም በግነት በሚከሰትበት ወቅት በበደም ውስጥ የሚገኘው ከልብ ሴሎች የሚለቀቀው እና በደም ውስጥ የሚገኘው የትሮፖኒን ፕሮቲን መጠን እንዲጨምር ሊያደርግ ይችላል። በደም ውስጥ የሚገኘው የበሽታ መከላኪያ ሴሎች ወይም የነጭ የደም ሴሎች መጠን ወይም ቁጥር የሚጨምር ይሆናል። በደረት ራጅ ምርመራ ፣ በኤሌክትሮካርዲዮግራም ምርመራ (ECG) ፣  በኢኮካርዲዮግራም ምርመራ እንዲሁም በኤም አር አይ  (MRI) ምርመራ በልብ ጡንቻ ላይ ከሚከሰት ኢንፌክሽን ወይም ብግነት ጋር በተገናኘ በልብ ጡንቻ ላይ የሚፈጠሩ ምልክቶችን እና ለውጦችን በመለየት በሽታው መከሰቱን ማወቅ ይቻላል።  

  አንድ አንድ ግዜ ጉዳት ከደረሰበት የልብ ጡንቻ ክፍል ላይ ናሙና በመወሰድ የሚደረግ ምርመራ (biopsy)  ማድረግ አስፈላጊ ሊሆን ይችላል።