Course Content
ምዕራፍ አሥራ አራት : በልብ እና በደም ቧንቧ ሥርዓት አፈጣጠር ሂደት ወቅት የሚፈጠሩ የጤና ችግሮች
0/16
ምዕራፍ አሥራ አምሥት : ከልብ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ ጋር በተገናኘ የሚፈጠሩ የልብ የጤና ችግሮች (Cardiac electrical system abnormalities)
0/16
ምዕራፍ አስራ ሰባት : በልብ በሮች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Valvular heart diseases)
0/16
ምዕራፍ ሃያ አንድ : የልብ ድካምበሽታ (Heart failure )
0/1
ምዕራፍ ሃያ ሦስት : በደም ቧንቧዎች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Vascular diseases)
0/22
በልብ እና በደም ቧንቧ ሥር ዓት ክፍሎች ውስጥ ሊፈጠሪ የሚችሉ የጤና ችግሮች (Pathology of Cardiovascular System)

 23. በደም ቧንቧዎች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Vascular diseases) 

         እንደ ማንኛውም የሰውነት ክፍል በተለያዩ የሰውነት ክፍል ውስጥ የሚገኙ የደም ቧንቧዎችም በተለያዩ ዓይነት የጤና ችግሮች ሊጠቁ ይችላሉ። በተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ውስጥ የሚገኙ የደም ቧንቧዎች ላይ የሚፈጠር ጉዳትም በተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ውስጥ የሚከሰቱ የጤና ችግሮችን ሊያስከትል ይችላል። 

    በተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ውስጥ በሚገኙ የደም ቧንቧዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት በማስከትል በቀዳሚነት ከሚጠቀሱ የደም ቧንቧ የጤና ችግሮች መካከል በደም ቧንቧ ግድግዳ ላይ የሚፈጠር የስብ ክምችት ወይም አቴሮስክሌሮሲስ (atherosclerosis) ፣ ከእድሜ መግፋት ጋር በተገናኘ የደም ቧንቧ ግድግዳ ላይ የሚፈጠር የካልሲየም መከማቸት እና የደም ቧንቧ ግድግዳ ጠንካራ መሆን ወይም አርተሪኦስክሌሮሲስ (arteriosclerosis) እንዲሁም በደም ቧንቧ ግድግዳ ላይ የሚፈጠር ብግነት (vasculitis) ዋንኞቹ ናቸው። በተጨማሪም በተለያዩ የደም መልስ የደም ቧንቧዎች ውስጥ የሚፈጠሩ የደም ቧንቧ ግድግዳ መለጠጥ ፣ በደም መልስ ቧንቧዎች ውስጥ የሚገኙ ደምን በአንድ አቅጣጫ የመፍሰስ ሂደት በሚያቀላጥፉ በሮች ላይ የሚከሰት ጉዳት ወይም በደም መልስ ቧንቧዎች ውስጥ የሚፈጠር የደም መርጋት በደም መልስ የደም ቧንቧዎች ውስጥ የሚኖረውን የደም ዝውውርን በማስተጓጎል በተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ላይ የከፋ የጤና ጉዳትን ሊያስከትሉ ይችላሉ።

       በደም ቅዳ ቧንቧዎች ወይም አርተሪዎች ላይ በሚፈጠሩ ጉዳቶች የተነሳ በተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ውስጥ ሊከሰቱ ከሚችሉ የጤና ችግሮች መካከል ደምን ወደ ልብ በሚያደርሰው የኮሮናሪ አርተሪ ላይ በሚፈጠር ጉዳት የተነሳ የሚከሰት የልብ የጤና ችግር (coronary artery disease) ፣ ደምን ወደ አንጎል በሚያደርሱ የደም ቧንቧዎች ላይ በሚፈጠር ጉዳት የተነሳ የሚከሰት የነርቭ ሥርዓት የጤና ችግር ወይም ስትሮክ (cerebral vascular accident / stroke) ፣ በአግር ወይም በእጅ ውስጥ በሚገኙ የደም ቅዳ ቧንቧዎች ላይ በሚፈጠር ጉዳት የተነሳ የደም ፍሰት መቀነስ (peripheral artery disease) ዋንኞቹ ናቸው። በአግር የውስጠኛ ክፍል ውስጥ  በሚገኙ የደም መልስ ቧንቧዎች ውስጥ የሚፈጠር የደም መርጋት (deep vein thrombosis / DVT) ፣ በእግር በውጭኛው ወይም በቆዳ ሥር የሚገኙ የደም መልስ ቧንቧዎች ግድግዳ መለጠጥ (varicocele) እንዲሁም በደም መልስ የደም ቧንቧ ግድግዳ ላይ የሚገኙ የደም ማሳለፊያ በሮች ላይ በሚፈጠር ጉዳት የተነሳ የሚከሰት የጤና ችግር ዋንኞቹ በደም መልስ ቧንቧዎች ላይ በሚከሰቱ ጉዳቶች የተነሳ የሚፈጠሩ የደም ቧንቧ የጤና ችግሮች ናቸው።

    በደም ውስጥ የሚገኘው የኮሌስትሮል ወይም የስብ መጠን መጨመር ፣ በጾታ ወንድ መሆን ፣ በደም ውስጥ የሚገኘው የግሉኮስ መጠን መጨመር ወይም የስኳር በሽታ ፣ የተለያዩ የካንሰር የጤና ችግሮች ፣ በሰውነት ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ ክፍሎች ውስጥ የሚከሰት ብግነት እንዲፈጠር የሚያደርጉ የጤና ችግሮች ፣ ከመጠን ያለፈ የሰውነት  ክብደት ፣ የደም ግፊት መጠን መጨመር በሽታ ፣ ሲጋራ ማጤስ ፣ የቅርብ የቤተስብ አባል በደም ቧንቧዎች ግድግዳ ላይ በሚፈጠር የስብ ክምችት የተነሳ በሚፈጠር የጤና ችግር መጠቃት እንዲሁም የእድሜ መግፋት ዋንኞቹ በደም ቧንቧዎች ግድግዳ ላይ ለሚፈጠር የስብ ክምችት መከሰት አጋላጭ የሆኑ ሆኔታዎች ናቸው። 

  በደም ውስጥ የሚጨምረው የኮሌስትሮል መጠን የሚወሰነው በምግብ መልክ ወደ ሰውነት በሚገባው የኮሌስትሮል መጠን እና በጉበት ውስጥ በሚሰራው የኮሌስትሮል መጠን ላይ ነው። ኮሌስትሮል በደም ውስጥ የሚዘዋወረው ከፕሮቲን ጋር ተጣብቆ ሲሆን በደም ውስጥ ኮሌስትሮልን በተለያየ መጠን የሚያዘዋውሩ የፕሮቲን ዓይነቶች ሊፖፕሮቲን (lipoprotein) ተብለው ይጠራሉ። 

    ከፍተኛ ከብደት ካለው ሊፖፕሮቲን ጋር ተጣብቆ የሚጓጓዘው የኮሌስትሮል ዓይነት ወይም ከፍተኛ ክብደት ያለው ሊፖፕሮቲን የያዘ ኮሌስትሮል (HDL) ኮሌስትሮልን በተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ውስጥ ከሚገኙ የደም ቧንቧዎች ውስጥ በመሰብሰብ ወደ ጉበት በማድረስ በደም ውስጥ የሚገኘው ነጻ የኮሌስትሮል መጠን እንዲቀንስ ስለሚያደርግ ጥሩ ኮሌስትሮል (good cholesterol)l ተብሎ ይጠራል። 

   በተቃራኒው ዝቅተኛ ክብደት ካለው ሊፖፕሮቲን ጋር ተጣብቆ የሚጓጓዝ የኮሌስትሮል ዓይነት ወይም ዝቅተኛ  ክብደት ያለው ሊፖፕሮቲን የያዘ ኮሌስትሮል (LDL) በጉበት ውስጥ የሚሰራውን ኮሌስትሮል በደም ቧንቧዎች በኩል ወደ ተለያዩ የሰውነት ክፍሎች አንዲደርስ ያደርጋል። በዚህም በደም ውስጥ የሚገኘው ነጻ ኮሌስትሮል መጠን አንዲጨምር ይደርጋል። ይህ በደም ውስጥ በመጠን የሚጨምረው ነጻ ኮሌስትሮል በደም ቧንቧዎች ግድግዳ ላይ በመከማቸት እና ብግነት እንዲፈጠር በማድረግ በደም ቧንቧ ግድግዳ ላይ ከሚያደርሰው ጉዳት በተጨማሪ የደም ቧንቧው እንዲጠብ ወይም እንዲዘጋ ሊያደርግ ይችላል። ስለዚህም ይህ ዓይነት ኮሌስትሮል መጥፎ ኮሌስትሮል (bad cholesterol) ተብሎ ይጠራል። 

      በደም ውሰጥ የሚገኘው ከፍተኛ ክብደት ያለው ሊፖፕሮቲን የያዘ ኮሌስትሮል (HDL) መጠን እንዲጨምር በማድረግ እና በደም ውሰጥ የሚገኘውን ዝቅተኛ ክብደት ያለው ሊፖፕሮቲን የያዘ ኮሌስትሮል (LDL) መጠን በመቀነስ በደም ቧንቧዎች ውስጥ የሚፈጠረውን የኮሌስትሮል መጠን መጨመር እንዲሁም በደም ቧንቧ ግድግዳ ላይ መከማቸት እና በአጠቃላይም በልብ እና በደም ቧንቧ ሥርዓት ለይ የሚፈጠሩ የጤና ችግሮችን የመከሰት እድል መቀነስ ይቻላል። 

  የአመጋገብ ሥርዓትን በማስተካከል (ከእንሰሳት የሚገኙ ቅበታማ ምግቦችን ፣ ጣፋጭ መጠጦችን እና ምግቦችን ማሰወገድ ፣ አትክልት እና ፍራፍሬዎችን በብዛት መመገብ) እንዲሁም ዘወትር አካላዊ አንቅስቃሴ በማድረግ በደም ውስጥ የሚገኘውን የኮሌስትሮል መጠን መቆጣጠር የሚቻል ሲሆን በእነዚህ መንገዶች በደም ውስጥ የሚገኘውን የኮሌስትሮል መጠን መቆጣጠር በማይቻልበት ወቅት በተለያዩ መንገዶች በደም ውስጥ የሚገኘውን የኮሌስትሮል መጠን ለመቆጣጠር የሚረዱ መድኃኒቶችን መጠቀም አስፈላጊ ይሆናል።

      በደም ውስጥ የሚገኘው የኮሌስትሮል መጠን በሚጨምርበት ወቅት በተለያዩ ምክንያቶች ጉዳት በደረሰበት የደም ቧንቧ ግድግዳ ላይ የሚከማቸው የኮሌስትሮል መጠን እንዲጨምር ያደርጋል። ጉዳት በደረሰበት የደም ቧንቧ ግድግዳ ላይ የሚጣበቀው እና የሚከማቸው ኮሌስትሮል የበሽታ መከላኪያ ሴሎች የኮሌስትሮል ክምችት ወደተፈጠረብት ክፍል እንዲመጡ እና በክምችቱ የተነሳም ብግነት እንዲፈጠር ያደርጋል። ወደ ኮሌስትሮል ክምችቱ የሚመጡት የበሽታ መከላኪያ ሴሎች እና የሚያመርቷቸው የተለያዩ ኬሜካሎች በአካባቢው ተጨማሪ የበሽታ መከላኪያ ሴሎች እና ኮሌስትሮል እንዲከማች በማድረግ ከፍተኛ መጠን ያለው ኮሌስትሮል በበሽታ መከላኪያ ሴሎች ውስጥ እንዲገባ እና እንዲጠራቀም ያደርጋሉ። በተጉዳው የደም ቧንቧ ግድግዳ ላይ የኮሌስትሮል እና የበሽታ መከላኪያ ሴሎች በከፍተኛ መጠን ከመከማቸት በተጨማሪ በደም ቧንቧው ግድግዳ ላይ የሚገኙ የጡንቻ ሴሎችን ( smooth muscle cells) በማነቃቃት የተከማቸውን ኮሌትስሮል የሚሽፍን ጠንካራ ሽፋን እንዲፈጠር ያደርጋሉ። ይህ በተለያዩ ሂድቶች ውስጥ በማለፍ ከኮሌስትሮል ፣ ከበሸታ መከላኪያ ሴሎች እና ከደም ቧንቧ ግድግዳ ጡንቻ ሴሎች ክምችት የሚፈጠር ክምር በደም ቧንቧ ግድግዳ ላይ የሚፈጠር የኮሌስትሮል ክምችት (atheroma plaque) ተብሎ ይጠራል።

  በጠንካራ ሽፋን የተሸፈነው የኮሌስትሮል ክምችት በመጠን እየጨመረ ሲሄድ የደም ቧንቧው እንዲጠብ ወይም እንዲዘጋ እንዲሁም በደም ቧንቧው ውስጥ የሚኖረው የደም ፍሰት መጠን እንዲቀንስ ያደርጋል። አንድ አንድ ግዜ ጠንካራው ሽፋን በተለያዩ ምክንያቶች በሚቀደድበት እና የኮሌስትሮል ክምችቱ ከተጣበቀበት ግድግዳ ላይ በሚላቀቅበት ወቅት ሁለት ዓይነት ወሳኝ  ሆኔታዎች ሊከሰቱ ይችላሉ።

  በደም ቧንቧ ግድግዳ ላይ የሚፍጠረውን የስብ ክምችት የሚሸፍነው ጠንካራው ሽፋን በሚቀደድበት እና የኮሌስትሮል ክምችቱ በከፊል ከተጣበቀበት ግድግዳ ላይ በሚላቀቅበት ወቅት ደም እንዲረጋ የሚያደርጉ ፕሌትሌቶች ከኮሌስትሮል ክምችቱ በተላቀቀው የደም ቧንቧ ግድግዳ ላይ መጣበቅ ወይም መከማቸት ይጀምራሉ። ደም እንዲረጋ የሚደርጉ ፕሌትሌቶች በተጉዳው የደም ቧንቧ ግድግዳ ላይ የደም መርጋት በመፍጠር የደም ቧንቧው የበለጠ እንዲጠብ ወይም የደም ፍሰቱ ቀድሞ ከነበረው የበለጠ እንዲቀንስ ሊያደርጉ ይችላሉ። ይህም ሆኔታ የሰብ ክምችት በተላቀቀበት የደም ቧንቧ ግደግዳ ላይ የሚፈጠር የደም መርጋት (thrombus) የመፈጠር ሂደት ወይም ተሮምቦሲስ  (thrombosis) ተብሎ ይጠራል። 

   በሌላ መልኩ ጠንካራው ሽፋን በሚቀደድበት እና የኮሌስትሮል ክምችቱ ከተጣበቀበት ግድግዳ ላይ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል በሚላቀቅበት ወቅት የተላቀቀው የኮሌስትሮል ክምችት ስብርባሪ በደም ቧንቧ ውስጥ በመጓዝ እና በርቀት በሚገኙ ትንንሽ የደም ቧንቧዎች ውስጥ በመሰንቀር እና የደም ፍስትን በመዝጋት ወይም በመገደብ በሌላ የሰውነት ክፍል ላይ ከደም ፍሰት መጠን መቀነስ ወይም መዘጋት ጋር በተገናኘ የጤና ጉዳት እንዲከሰት ሊያደርግ ይችላል። 

      ይህ ከላይ በተገለጸው መንገድ የሚፈጠረው የኮሌስትሮል ክምችት መፈጠር በሰውነት ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ የደም ቧንቧዎች ወስጥ ሊፈጠር የሚችል ሲሆን በደም ቧንቧ ግድግዳ ላይ የኮሌስትሮል ክምችት በብዛት ከሚፈጠርባቸው የደም ቧንቧዎች መካከል ትልቁ ደም ቅዳ ቧንቧ ፣ ደምን ወደ ልብ የሚያደርሱ የደም ቧንቧዎች ወይም የኮሮናሪ አርተሪዎች ፣ ደምን ወደ አንጎል የሚያደርሱ የደም ቧንቧዎች ፣ ደምን ወደ ኮላሊት የሚያሰገቡ የደም ቧንቧዎቸ‍ ፣ ደምን ወደ ዓይን የሚያደርሱ የደም ቧንቧዎች እንዲሁም በእግር ውስጥ የሚገኙ የደም ቧንቧዎች ዋንኞቹ ናቸው።

    ደምን ወደ ልብ በሚያደርሱ የደም ቧንቧዎች ወይም በኮሮናሪ አርተሪዎች ላይ በሚከሰቱ ጉዳቶች የተነሳ በልብ ላይ የሚፈጠሩ የጤና ችግሮችን የበለጠ ለመረዳት ምዕራፍ  አሥራ አምስትን ይመልከቱ።