23.1.1 ደምን ወደ አንጎል ክፍሎች በሚያደርሱ የደም ቧንቧዎች መጥበብ ወይም መዘጋት የተነሳ የሚፈጠር ስትሮክ (ischemic stroke)
ደምን ወደ አንጎል ክፍሎች በሚያደርሱ የደም ቧንቧዎች መጥበብ ወይም መዘጋት የተነሳ የሚፈጠር ስትሮክ (ischemic stroke) የሚከሰተው ደምን ወደ አንጎል በሚያደርሱ የደም ቧንቧዎች ግደግዳ ላይ በሚከሰት የኮሌስትሮል ክምችት (atherosclerosis) ፣ ከእድሜ ጋር በተገናኘ በደም ቧንቧዎች ግድግዳ ላይ የካልሲየም መከማቸት ጋር በተገናኘ የአርተሪዎች ግድግዳ መጠንከር ( arteriosclerosis) ፣ በሌላ የሰውነት ክፍሎች ውስጥ በሚገኝ የደም ቧንቧ ግድግዳ ላይ የሚፈጠር የስብ ክምችት ከተጣበቀበት የደም ቧንቧ ላይ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል በመላቀቅ በአንጎል ወስጥ በሚገኝ የደም ቧንቧ ውስጥ በመሰንቀር የደም ፍሰትን በመዝጋት (embolism ፣ በደም ቧንቧ ግድግዳ ላይ የሚፈጠር የስብ ክምችት ከተጣበቀበት የደም ግድግዳ ላይ በከፊል በሚለቃቅበት የግድግዳው ክፍል ላይ ከሚፈጠር የደም መርጋት (thrombosis) ወይም በአንጎል ውሰጥ በሚገኙ የደም ቧንቧዎች ግደግዳ ላይ በሚፈጠር ብግነት ( vasculitis) የተነሳ ሊሆን ይችላል።
ከለይ የተገለጹት ሆኔታዎች ደምን ወደ አንጎል ክፍሎች በሚያደርሱ በተለያየ የአንጎል ክፍሎች ውስጥ በሚገኙ እና የተለያየ መጠን ባላቸው የደም ቧንቧዎች ላይ በሚያደረሱት ጉዳት የተነሳ የደም ቧንቧው በሂደት ቀሰ በቀስ እንዲጠብ እና ወደ አንጎጎል ክፍሎቸ የሚደርሰው የደም መጠን እንዲቀንስ ወይም እንዲቋረጥ በማድረግ በአንጎል የደም ቧንቧዎች ላይ በሚፈጠር ጉዳት የተነሳ በነርቭ ሥርዓት ላይ የሚከሰት የጤና ችግር ወይም ስትሮክ እንዲፈጠር ሊያደርጉ ይችላሉ።
በአጠቃላይ በአንጎል የደም ቧንቧዎች ላይ በሚፈጠር ጉዳት የተነሳ በነርቭ ሥርዓት ላይ ከሚከሰት የጤና ችግር ወይም ስትሮክ ውስጥ ደምን ወደ አንጎል በሚያደርሱ የደም ቧንቧዎች መጥበብ ወይም መዘጋት የተነሳ የሚፈጠር ስትሮክ ወደ 87 በመቶውን የሚይዝ ይሆናል።
የእድሜ መግፋት ፣ በጾታ ወንድ መሆን ፣ በዘር አፍሪካዊ መሆን ፣ የደም ግፊት መጠን መጨመር ፣ ከመጠን ያለፈ የሰውነት ክብደት ፣ ሲጋራ ማጤስ ፣ የስኳር በሽታ ፣ የካሮቲድ አርተሪ ግድግዳ ላይ የሚፈጠር የኮሌስትሮል ክምችት ፣ በደም ውስጥ የሚገኘው የኮሌስትሮል መጠን መጨመር ፣ ከልብ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ ጋር በተገናኘ የልብ ምት መዛባት ወይም የአተእሪየም ፊብሪሌሽን ( atrial fibrillation) መፈጠር እንዲሁም የቀይ የደም ሴሎች ቅረጽ እነዲለወጥ የሚያደርገው የሲክል ሴል በሽታ ( sickle cell disease) ዋንኞቹ ደምን ወደ አንጎል የሚውስዱ የደም ቧንቧዎች መጥበብ ወይም መዘጋት የተነሳ የሚፈጠር ስትሮክ እንዲፈጠር የሚያደርጉ አጋላጭ ሆኔታዎች ናቸው።
በልብ የግራ ክፍል ውሰጥ ወይም በቅርበት ከሚገኘው የትልቁ ደም ቅዳ በሚነሱ አርተሪዎች ግድግዳ ላይ የሚፈጠር የደም መርጋት ወይም የኮሌስትሮል ክምችት ከተጣበቀበት የልብ ክፍል ወይም የደም ቧንቧ ግድግዳ በመላቀቅ እና በደም ቧንቧ ውስጥ በመዘዋወር ከዚያም በአንጎል ውስጥ በሚገኙ ሌሎች የደም ቧንቧዎች ውስጥ በመሽንቆር የአንጎል የደም ቧንቧዎች እንዲጠቡ እና እንዲዘጉ በማድረግ ለአንጎል ክፍሎች የሚደርሰው የደም መጠን መቀነስ ወይም መቋረጥ እንዲፈጠር ሊያደርግ ይችላል። በዚህም የተነሳ ከአንጎል የደም ቧንቧዎች መጥበብ ወይም መዘጋት ጋር በተገናኘ የሚፈጠር ስትሮክ እንዲክሰት ሊያደርግ ይችላል።
በአንጎል ውሰጥ ከሚገኙ እና የስብ ክምችት በብዛት ክሚፈጠርባቸው የደም ቧንቧዎች መካከል የቀኝ እና የግራ የውስጠኛው የካሮቲድ አርተሪዎች ፣ የቀኝ እና የግራ ቨርቴብራል አርተሪዎች እንዲሁም የባዜላር አርተሪ ዋንኞቹ ናቸው። በእነዚህ የደም ቧንቧዎች ውስጥ የሚፈጠረው የስብ ክምችት በመጠን በመጨመር ወደ አንጎል የሰውነት ክፍሎች ውስጥ የሚደርሰው የደም ፍሰት በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ እንዲዘጋ ሊያደርግ ይችላል። በተጨማሪም በእነዚህ የደም ቧንቧዎች ላይ የሚፈጠረው የስብ ክምችት በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ በመላቀቅ እና በደም ውስጥ በመዘዋወር በአንጎል ውስጥ በሚገኙ ትንንሽ የደም ቧንቧዎች ውስጥ በመሽንቆር የደም ፍስትን በመቀነስ ወይም በመገደብ በአንጎል ክፍሎች ላይ ጉዳት እንዲፈጠር ሊያደርግ ይችላል።
በተወሰነ የአንጎል ክፍል ውስጥ የሚኖረው የደም ፍሰት በሚቀንሰበት ወይም በሚቋረጠበት እና ለአንጎል ሴሎች የሚደረሰው የኦክስጂን እና የንጥረ ምግቦች ፍሰት በሚቋረጥበት ወቅት በአንጎል ሴሎች ላይ ክፍተኛ የሆነ ጉዳት እና መሞት ስለሚከሰትል ጉዳት የደረሰበት የአንጎል ክፍል ሲያከናውነው በነበረው ተግባር ላይ አክል የሚፈጠር ይሆናል።
ወደ አንጎል ክፍሎች ደምን በሚያደርሱ የደም ቧንቧዎች ላይ በሚፈጠር መዘጋት የተነሳ በአንጎል ክፍሎች ላይ የሚፈጠረው የጉዳት ደረጃ በደም ቧንቧው ዓይነት ፣ የደም ፍሰቱ እንደተዘጋ በሚቆይበት ግዜ ፣ ጉዳት ከደረሰባቸው የአንጎል ሴሎች በሚመረቱ ኬሚካሎች ዓይነት እና መጠን ፣ የደም ፍሰት መዝጋቱን ተከትሎ በአንጎል ሴሎች ውስጥ በሚፈጠረው ዕብጠት ወይም የፈሳሽ መጠን መጨመር እና የተፈጠረው የአንጎል ሴሎች ዕብጠት እንደገና በአንጎል ክፍሎች ወስጥ በሚኖረው የደም ፍሰት ሆኔታ ላይ በሚያሳድረው ተፅህኖ እንዲሁም የአንጎል ሴሎች ዕብጠት በሌሎች የአንጎል ክፍሎች ላይ በሚያሳድረው ጫና ላይ የሚወሰን ይሆናል።
ወደ አንጎል ክፍሎች ከሚደርሰው የደም ፍሰት መዘጋት ወይም መቀነስ ጋር በተገናኘ ከ 24 ሰዓት ለሚያንስ ግዜ ብቻ የሚቆይ በተጉዳው የደም ቧንቧ ዓይነት እና የጉዳት ደረጃ መሰረት የሚከሰቱ ምልክቶች እና ለውጦች ሊታዩ ይችላሉ። ይህ ዓይነት ለጥቂት ደቂቃዎች ወይም ስዓታት ብቻ የሚቆይ ወደ አንጎል ክፍሎች ከሚደርሰው የደም ፍሰት መዘጋት ጋር በተገናኘ የሚከሰት የጤና ችግር ከ 24 ሰዓታት በታች ለሆነ ግዜ ብቻ የሚቆይ ስትሮክ (transient ischemic attack) ተብሎ ይጠራል። ከ 24 ሰዓታት በታች ለሆነ ግዜ ብቻ የሚቆይ ስትሮክ የሚፈጠረው ለጥቂት ሰከንዶች ወይም ደቂቃዎች ወደ አንጎል ክፍሎች የሚደረሰው የደም መጠን በሚቀንስበት ወይም በሚቋረጥበት እና በአንጎል ሴሎች ላይ የከፋ ጉዳት ሳይከሰት የደም ፍሰቱ እንደገና በፍጥነት በሚስተካከልበት ወቅት ነው።
ከ 24 ሰዓታት በታች ለሆነ ግዜ ብቻ በሚቆይ ስትሮክ የተጠቁ በሽተኞች ለደቂቃዎች ወይም ለጥቂት ሰዓታት የሚቆይ የተወሰነ የሰውነት ክፍል መደነዝዝ ወይም መታዘዝ አለመቻል ፣ ማየት አለመቻል ፣ በፊት ላይ የሚታይ መጣመም ወይም በትክክል ማውራት ወይም መናገር አለመቻል ሊታይባቸው ይችላል። እነዚህ በሽተኞች ወደ ፊት ከፍተኛ ጉዳት ሊያስከትል በሚችል ደምን ወደ አንጎል በሚያደርሱ የደም ቧንቧዎች ላይ በሚፈጠር ጉዳት ከደም ፍሰት መዘጋት ጋር በተገናኘ ለሚከሰት ስትሮክ የመጋለጥ እድላቸው ከፍተኛ ነው።
አንድ አንድ ግዜ በልብ ውስጥ ከሚፈጠሩ የተለያዩ የጤና ችግሮች ጋር በተገናኘ በልብ ውስጥ በተለይም በግራ የልብ ክፍል ውስጥ የሚፈጠር የደም መርጋት ከልብ ግድግዳ ላይ በመላቀቅ እና በደም ቧንቧዎች ውስጥ በመዘዋወር እና ደምን ወደ አንጎል ክፍሎች በሚያደርሱ የደም ቧንቧዎች ውስጥ በመሰንቀር ለአንጎል ክፍሎች የሚደርሰው የደም ፍሰት እንዲቀንስ ወይም እንዲዘጋ ሊያደርጉ ይችላሉ። በዚህም የተነሳ በተጉዳው የአንጎል ክፍል መስረት ሰትሮክ መፈጠሩን የሚያሳዩ የተለያዩ ምልክቶች እና ለውጦች የሚከሰቱ ይሆናል።
ወደ አንጎል ከሚደርሰው የደም ፍሰት መዘጋት ጋር በተገናኘ በአንጎል ክፍሎች ላይ ከሚፈጠረው ጉዳት የተነሳ በድንገት ሊከሰቱ ከሚችሉ ምልክቶች እና ለውጦች መካከል የግራ ወይም የቀኝ የተወሰነ የሰውነት ክፍልን (አጅን እና ክንድን ፣ እግርን ሁለቱንም ወይም አንዱን ሊሆን ይችላል) ማዘዝ አለመቻል ፣ በተወሰነ የስወነት ክፍል ላይ የሚፈጠር ስሜትን ወይም ለውጥን መረዳት አለመቻል (ሙቅት እና ቅዝቃዜ ፣ ህመም እና ሌሎች ስሜቶችን ወይም ለውጦችን መረዳት አለመቻል) ፣ የተወሰነ የሰውነት ክፍል መዛል ፣ መደንዘዝ ወይም መድከም ፣ በተወሰነ የሰውነት ክፍል ላይ የሚፈጠር ያልተለመደ የመቆጥቆጥ ፣ የመንዘር እና የመደንዘዝ ስሜት መሰማት ፣ ማውራት ወይም መናገር አልመቻል ፣ ቃላትን መረዳት ወይም ቃላትን መፍጠር አለመቻል ፣ ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል ወይም በተወሰነ ደረጃ ማየት አለመቻል ፣ አራስን መቆጣጠር አለመቻል ፣ የግራ ወይም በቀኝ በኩል የሚገኘውን የሰውነት ክፍል አንደ ራስ የሰውነት ክፍል አድርጎ መቆጠር አለመቻል ወይም በግራ ወይም በቀኝ በኩል የሚገኘውን የሰውነት ክፍል ከነመፈጠሩ መርሳት ፣ የራስ ምታት (ከፍተኛ የሆነ የራስ ምታት ብዙሁን ጊዜ የሚከሰተው በአንጎል ውስጥ የደም መፍሰስ በሚከሰትበት ወቅት ነው) እንዲሁም በቀኝ እና / ወይም በግራ ፊት ላይ የሚታየ ለወጥ መከሰት ( ሲሰቁ የአፍ ወደ አንድ አቅጣጫ መጣመም ፣ ዓይንነ መክደን አለመቻል ወይም ምላስን ቀጥ አድርጎ ከአፍ ማውጣት አለመቻል) ዋንኞቹ ናቸው።
ከላይ የተገለጹት ምልክቶች እና ለውጦች የሚከሰቱት በድንገት ሲሆን የሚፈጠረው ምልክት እና ለውጥ ጉዳት በደረሰበት የደም ቧንቧ ወይም የአንጎል ክፍል ላይ የሚወሰን ይሆናል። ለምሳሌ በመካከለኛው የሴረብራል አርተሪ ወይም በኋለኛው የሴረብራል አርተሪዎች ላይ ጉዳት በሚፈጠርበት ወቅት ጉዳት በደረሰበት የአንጎል ክፍል መሰረት የሚፈጠሩት ምልክቶች እና ለውጦች የተለያዩ አይነቶች ናቸው።
ስትሮክ መከሰቱን ለማወቅ ከሚረዱ ሆኔታዎች መካከል ከበሽተኛው የሚገኘው የበሽታው ታሪክ ፣ በአካላዊ ምርመራ የሚገኙ ውጤቶች እና በአንጎል ውስጥ የሚገኙ የአንጎል ክፍሎችን እና የደም ቧንቧዎችን ሊያሳዩ የሚችሉ የምርመራ መንገዶችን መጠቀም ዋንኞቹ ናቸው። በአንጎል ውስጥ የሚፈጠሩ ጉዳቶችን ለመለየት የኮምፒዩትድ ቶሞግራፊ (CT) ወይም የኤም አር አይ (MRI) ምርመራ ማድረግ አስፈላጊ ሲሆን በአንጎል ውስጥ የሚገኙ የደም ቧንቧዎችን የጤንነት ሆኔታ ለማየት እና በአንጎል ውስጥ በሚገኙ የደም ቧንቧዎች ላይ የተፈጠረውን ጉዳት ለመለየት ደግሞ የደም ቧንቧዎችን ለማየት የሚረዳ የኮምፒዩትድ ቶሞግራፊ (CT angiography) ወይም የኤም አር አይ ምርመራ ( MRI angiography) ምርመራ ሊያስፈልግ ይችላል።
በተጨማሪም በሌላ የሰውነት ክፍል ውስጥ ከሚገኘ የደም ቧንቧ ወይም የልብ ክፍል ውስጥ ከሚነሳ የኮሌስትሮል ክምችት ወይም የደም መርጋት የተነሳ ደምን ወደ አንጎል የሚያደርሱ የደም ቧንቧዎች መዘጋት ጋር የተገናኘ ጉዳት መከሰቱ በሚጠረጠርበት ወቅት መነሻ የሆነውን የልብ ወይም የደም ቧንቧ ክፍል ለማወቅ የደም ቧንቧዎች የአልትራሳውንድ ምርመራ ወይም የልብ የአልትራሳወንድ ምርመራ ወይም የኢኮካርዲዩግራም ምርመራ ማድረግ አስፈለጊ ሊሆን ይችላል።
ለተለያዩ የአንጎል ክፍሎች በተለይም በጥልቀት ለሚገኘው የውስጠኛው የአንጎል ክፍል ደምን የሚያደርሱ ትንንሽ የደም ቧንቧዎች በአንጎል ውስጥ ይገኛሉ። ወደ ውስጠኛው የአንጎል ክፍል በቂ ደም እንዲደረስ በሚያደርጉ ትንንሽ የደም ቧንቧዎች ላይ የሚፈጠር የደም ፍሰት መዘጋት (lacunar infarction) የአንጎል የውስጠኛ ክፍል ላይ ጉዳት በማድረስ የተለያዩ ምልክቶች እና ለውጦች እንዲከሰቱ ሊያደርግ ይችላል። ለውስጠኛው የአንጎል ክፍል ደም እንዲደርስ በሚያደርጉ የደም ቧንቧዎች መዘጋት የተነሳ ከሚፈጠሩ ምልክቶች እና ለውጦች መካከል በግራ ወይም በቀኝ የሰውነት ክፍልን ማዘዝ አለመቻል ፣ በግራ ወይም በቀኝ የሰውነት ክፍል ላይ የሚፈጠሩ ስሜቶችን እና ለውጦችን መረዳት አለመቻል ፣ የግራ ወይም የቀኝ የፊት ክፍል መውደቅ ወይም መታዘዝ አለመቻል ፣ መናገር ወይም ቃላትን ማውጣት አለመቻል እና የመሳሰሉት ምልክቶች እና ለውጦች ሊታዩ ይችላሉ። የኤም አር አይ ምርመራ ወደ አንጎል የወስጠኛ ክፍል ደም በሚያደርሱ የደም ቧንቧዎች ላይ የሚከሰቱ ጉዳቶችን ለመለየት ተመራጭ የምርመራ መንገድ ነው። ነገር ግን የኤም አር አይ (MRI) ውጤትን በፍጥነት ለማግኘት እና አስፈላጊውን ህክምና በፍጥነት ለመጀመር አስቸጋሪ ይሆናል።
ደምን ወደ አንጎል በሚያደርሱ የደም ቧንቧዎች መጥበብ ወይም መዘጋት የተነሳ ለሚፈጠር ስትሮክ የሜሰጠው ህክምና ቢያንስ ሦስት ዋና ግቦችን ለማሳካት ይሆናል። እነዚህም ሦስት ዋና ግቦች ጉዳት ወደ ደረሰበት የአንጎል ክፍል የሚደረሰውን የደም ፍሰት መዘጋት በፍጥነት እንዲከፈት በማድረግ ተጨማሪ ጉዳትን መቀነስ ፣ ተጨማሪ ደምን ወደ አንጎል የሚያደርስ የደም ቧንቧ መዘጋት አንዳይፈጠር መከላከል እና ከደረሰው ጉዳት ጋር በተገናኘ ለረጅም ግዜ የሚቆዩ እና በበሽተኛው የወድፊት ህይወት ላይ ጫና የሚያደርሱ ሆኔታዎችን መቀነስ ናቸው።
ደምን ወደ አንጎል ክፍሎች የሚያደርሱ የደም ቧንቧዎች መዘጋት በፍጥነት እንዲከፈት ለማድረግ እና የደም ፍሰቱን በፍጥነት ለመመለስ የተፈጠረውን የደም መርጋት የሚሰባበሩ መድኃኒቶችን መጠቀም (thrombolytics) ፣ በደም ቧንቧ ውስጥ ቀጭን ሽቦ መሰል መሳሪያ ወይም ካቴትር በማስገባት በአንጎል ውስጥ በሚገኙ የደም ቧንቧዎች ውስጥ የሚፈጠረውን የደም ቧንቧ መዘጋትን መክፍት ወይም ወደ አንጎል ከፍሎች የሚደርሰውን የደም መጠን ለመጨመር የሚረዱ ሌሎች መንገዶችን መጠቀም ሊያስፈልግ ይችላል።
ደምን ወደ አንጎል በሚያደርሱ የደም ቧንቧዎች መዘጋት የተነሳ የሚፈጠር ስትሮክን እንደገና የመከሰት እድል ለመቀነስ የሚረዱ በተለይም በደም ቧንቧ ግድግዳ ላይ የሚፈጠረውን የስብ ክምችት እና በልብ እና በተለያዩ የደም ቧንቧዎች ውስጥ የሚፈጠረውን የደም መርጋት ለመከላከል የሚረዱ የተለያዩ መድኃኒቶችን መጠቀም አሰፈላጊ ሊሆን ይችላል። በደም ውስጥ የሚገኙ ፕሌትሌቶች እርስ በእርስ በመያያዝ የደም መርጋት እንዳይፈጠሩ ለመከላከል በየቀኑ የአስፕሪን ወይም ሌሎች የፕሌትሌት ክምችትን ለመከላከል የሚረዱ መድኃኒቶችን መጠቀም ፣ ደም እንዲቀጥን የሚያደርጉ መድኃኒቶችን መጠቀም ፣ የደም ግፊት መጠንን ለመቆጣጠር የሚረዱ መድኃኒቶችን መጠቀም ፣ በደም ውስጥ የሚገኘውን የኮሌስትሮል መጠን ለመቆጣጠር የሚረዱ መድኃኒቶችን መጠቀም ፣ በደም ወሰጥ የሚገኘውን የግሉኮስ መጠን ለመቆጣጠር የሚረዱ መድኃኒቶችን መጠቀም እንዲሁም የደም ግፊት መጠንን ለመቆጣጠር ፣ የሰውነት ክብደትን ለማስተካክል እና በደም ውስጥ የሚኖረውን የኮሌሰእትሮል እና የግሎኮስ መጠንን ለመቆጣጠር የሚረዱ የህይወት እና የአኗኗር ዘይቤን (አመጋገብን እና ዘወትር አካላዊ እነቀሰቃሴ ማድረግ) ለውጦችን ማድረግ በጣም አስፈላጊ ይሆናል።
በተጨማሪም በሽተኛች ከሆስፒታል ውጥተው ወደ ቤታቸው ከሄዱ በኋላ ሊከሰቱ የሚችሉ የጤና ችግሮችን ለመከላከል ፣ ቀሪ ሀይወታቸውን በተሻለ የጤንነት ሆኔታ ስለሚመሩበት መንገድ ፣ ሰለሚውሰዷቸው መድኃኒቶች ጥቅም እና የጎኒዮሽ ጎዳቶች ፣ አመጋገብ እና አካላዊ እንቅሰቃሴ እንዲሁም በአጠቃለይ የጤንነት ሆኔታቸውን የሚጠብቁበትን እና ተጨማሪ የጤና ችግሮችን መከላከል ስለሚችሉበተ ሆኔታ በተገቢው ሆኔታ ማስተማር እና አስፈለጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ማስገንዘብ ወይም ምክር መስጠት በጣም አስፈላጊ ይሆናል። በሽተኞችን የማሰተማር እና ምክር የመሰጠት ሂደት ቤተሰቦቻቸውን ወይም እንክብካቤ የሚያደርጉላቸውን የቤተሰብ አባላት ባካተተ ሆኔታ ቀጣይነት ባለው መልኩ መታቀድ እና መተግበር ይኖርበታል።
ደምን ወደ አንጎል በሚያደርሱ የደም ቧንቧዎች ወሰጥ ከሚኖረው የደም ፍሰት መዘጋት ጋር በተናኘ በአንጎል ክፍሎች ላይ ጉዳት በሚፈጠርበት ወቀት በሸተኞች አሰቀድሞ ማድረግ የሚችሏቸው እነደ መመገብ እና የግል ንፅህናን መጠበቅ ያሉ የተለመዱ እንቅቃሴዎችን እና ተገባራትን ማከናወን እንዳይችሉ እንዲሁም በሆሰፒታል ወይም በቤታቸው ወሰጥ ለረጅም ግዜ እንዲተኙ ወይም የዘወትር እንቅሰቃሴያቸው እንዲቀንስ ሊያደረግ ይችላል። ይሀም ሆኔታ ለሌሎች የጤና ችግሮች መከሰት የሚኖራቸው ታጋላጭነት እነዲጨምር ያደርጋል። ስለሆነም በዚህ የጤና ችግር የተጠቁ በሽተኞች የሚታዘልላቸውን መድኒት በትክክል ከመውስድ በተጨማሪ ከተፈጠረው የጤና ችግር ጋር በተገናኘ ሊከሰቱ የሚችሉ ሌሎች የጤና ችግሮችን ለመከላክል በቂ የሆን ትምሀርት እና የምክር አገልግሉት ማግኘት ይኖርባቸዋል።
ደምን ወደ አንጎል በሚያደርሱ የደም ቧንቧዎች ወሰጥ ከሚኖረው የደም ፍሰት መዘጋት ጋር በተናኘ በአንጎል ክፍሎች ላይ ጉዳት በሚፈጠርበት ወቅት በወሰጠኛው የሰውነት ክፍል ውስጥ በሚገኙ የደም መልስ ቧንቧዎች ውስጥ የሚፈጠር የደም መርጋት ( DVT) እንዳይከሰት ፣ በሽተኛው በሚመገብበት ወይም በሚጠጣበት ወቅት ምግቡ ወይም መጠጡ ወደ አየር ቧንቧ ውስጥ በመግባት በሳንባ ላይ ጉዳት እንዳያስከትል (aspiration) ፣ በሽተኛው ለረጅም ግዜ በሚታኛበት ወይም በሚቀመጥበት ወቅት በሰውነት ክፍሎች ላይ ሊፈጠር የሚችለውን የሰውነት ቆዳ ቁስለት (pressure ulcer) ለመከላከል የሚረዱ ሆኔታዎችን ማመቻቸት እንዲሁም በሰውነት ላይ ከደረሰው ጉዳት ጋር በተገናኘ ከሚፈጠር የመውደቅ አደጋ (fall injury) መከላከል እንዲሁም ለመከላከል የሚረዱ ሆኔታዎችን ማስተካከል በጣም አስፈላጊ ይሆናል።