Course Content
ምዕራፍ አሥራ አራት : በልብ እና በደም ቧንቧ ሥርዓት አፈጣጠር ሂደት ወቅት የሚፈጠሩ የጤና ችግሮች
0/16
ምዕራፍ አሥራ አምሥት : ከልብ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ ጋር በተገናኘ የሚፈጠሩ የልብ የጤና ችግሮች (Cardiac electrical system abnormalities)
0/16
ምዕራፍ አስራ ሰባት : በልብ በሮች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Valvular heart diseases)
0/16
ምዕራፍ ሃያ አንድ : የልብ ድካምበሽታ (Heart failure )
0/1
ምዕራፍ ሃያ ሦስት : በደም ቧንቧዎች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Vascular diseases)
0/22
በልብ እና በደም ቧንቧ ሥር ዓት ክፍሎች ውስጥ ሊፈጠሪ የሚችሉ የጤና ችግሮች (Pathology of Cardiovascular System)

23.2.3. ደምን ወደ አንጎል የሚያደርሱ የደም ቧንቧዎች  ግድግዳ መሳሳት እና መሰርጎድ  (aneurysm)

  የደም ቧንቧዎች ግድግዳ መሳሳት እና መሰርጎድ በደም ቧንቧ ግድግዳ ላይ ከሚፈጠሩ የተለያዩ ጉዳቶች ፣ ከተለያዩ የጤና ችግሮች ጋር በተገናኘ በደም ቧንቧ ግድግዳ  አፈጣጠር ሂደት ወቅት እክል በሚፈጥሩ ሆኔታዎች እንዲሁም የደም ግፊት መጠን መጨመር በሽታ ቀስ በቀስ በደም ቧንቧ ግዳግዳ ላይ በሚያስከትለው ጉዳት የተነሳ የደም ቧንቧ ግዳግዳ መቅጠን ወይም መሳሳት መሰፋት እና መሰርጎድ ጋር በተገናኘ የሚፈጠር የጤና ችግር ነው። የደም ቧንቧ ግድግዳ መቅጠን ፣ መስፋት እና መሰርጎድ የጤና ችግር በተለያዪ የሰውነት ክፍሎች ውሰጥ በሚገኙ የተለያዩ ዓይነት የደም ቧንቧዎች ላይ ሊከሰት ይችላል። 

       ደምን ወደ አንጎል የሚያደርሱ የደም ቧንቧዎች ግድግዳ መለጠጥ እና መሰርጎድ (aneurysm) በሚፈጠርበት ወቅት የሳሳው እና የተሰርጎደው የግድግዳ ክፍል በቀላሉ በመሽንቆር ፣ በመቀደድ ወይም በመፈንዳት ደም በአንጎል ክፍሎች ውስጥ እንዲፈስ  ሊያደርግ  ይችላል። በአንጎል ክፍሎች ውስጥ የሚፈሰው እና የሚከማቸው ደም የአንጎል ክፍሎችን በመጨፍለቅ እና ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ በተጉዳው የአንጎል ክፍል መሰረት የተለያዩ ምልክቶች እና ለውጦች እንዲፈጠሩ ያደርጋል።  

   ደምን ወደ አንጎል የሚያደርሱ የደም ቧንቧዎች ግድግዳ መሳሳት እና መሰርጉድ ብዙሁን ግዜ የሚከሰተው የደም ቧንቧዎች ለሁለት በሚከፈሉበት ክፍል ላይ ሲሆን በአንጎል ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ የደም ቧንቧዎች እርሰ በእርስ ግንኙነት የተነሳ የክብ ቅረጽ የሚፈጥረው የደም ቧንቧዎች ግንኙነት (circle of willis)  ዋንኛ በአንጎል ውሰጥ የደም ቧንቧ ግድግዳ መሳሳት እና መሰርጉድ  እንዲሁም የደም ቧንቧ ግድግዳ መሽንቆር እና የደም መፍሰስ የሚከሰትበት ክፍል ነው። ደምን ወደ አንጎል የሚያደርሱ የደም ቧንቧዎች ግድግዳ እንዲቀጥን ወይም እንዲሳሳ እና እንዲሰረጎድ ሊያደርጉ ከሚችሉ ሆኔታዎች መካከል በደም ቧንቧ ግድግዳ አፈጣጠር ሂደት ወቅት የሚከሰት እክል ወይም ጉድለት ፣ በደም ቧንቧ ግድግዳ ላይ የሚፈጠር የስብ ክምችት ፣ ለረጅም ግዜ የቆየ የደም ግፊት መጠን መጨመር እና በደም ቧንቧ ግድግዳ ላይ የሚፈጠር ኢንፌክሽን ወይም ብግነት ዋንኞቹ ናቸው። በተጨማሪም ሴጋራ ማጤስ እና የአልኮል መጠጥ ከመጠን በላይ መውሰድ ደምን ወደ አንጎል በሚወስዱ የደም ቧንቧዎች ግድግዳ ላይ ለሚፈጠር መለጠጥ እና መሰርጎድ ዋንኛ አጋላጭ ሆኔታዎች ናቸው።

  ደምን ወደ አንጎል የሚያደርሱ የደም ቧንቧዎች ግድግዳ ላይ ከሚፈጠር መለጠጥ እና መሰርጎድ ጋር በተገናኘ ሊከሰቱ የሚችሉ ምልክቶች እና ለውጦች ጉዳት በደረሰበት የደም ቧንቧ ዓይነት እንዲሁም  የደም ቧንቧው በሚገኝብት የአንጎል ክፍል ወይም ጉዳት በሚደርስበት የአንጎል ከፍል እና  መጠን ላይ የሚወስን ይሆናል። 

  በአንጎል ከፍሎች ውስጥ የሚፈሰው የደም መጠን በጣም አነሰተኛ በሚሆንበት ( ከደም ቧንቧው መሸንቆር፣ መቀደድ ወይም መፈንዳት በኃላ በአንጎል ውስጥ የሚፈሰው የደም መጠን ዝቅተኛ ስለሚሆን) ወይም ጉዳት የደረሰበት የአንጎል ክፍል መጠኑ በጣም ትንሽ በሚሆንበት ወቅት ምንም ዓይነት ምልክት እና ለውጥ ላያታይ ይችላል። በአንጎል ክፍሎች ወሰጥ የሚፈሰው የደም መጠን የበዛ በሚሆንበት ወይም ጉዳት የደረሰበት የአንጎል ከፍል መጠኑ ትልቅ በሚሆንበት ወይም ጉዳቱ ወሳኝ በሆነ የአንጎል ክፍል ላይ በሚፈጠርበት ወቅተ በድንገት የሚፈጠር እና የከፋ ደረጃ ላይ የደረሰ  ሰትሮክ ወይም የሞት አደጋ ሊያስከትል ይችላል። 

   ጉዳት ከደረሰበት የደም ቧንቧ ውስጥ ደም በትንሽ በትንሹ በሚፈስበት ወቅት ለረጅም ቀናት የሚቆይ የራስ ምታት እንዲፈጠር ሊያደርግ ይችላል። የሚፈሰው የደም መጠን አየጨመረ እና በአንጎል ክፍሎች ላይ የሚያስከትለው ጉዳት አየጨመረ ሲመጣ ደግሞ የራስ ምታትን ጨምሮ የተወሰነ የሰውነት ክፍል ላይ የሚከሰት መደንዝ ፣  መዛል መድከም ወይም የሰውነት ክፍል አለመታዘዝ እንዲሁም ማቅለሽለሽ ፣ ማስታወክ እና አንፍርፍሬት (seizure) ሊፈጠር ይችላል።

     በተጨማሪም በአንጎል ውስጥ የሚገኙ የደም ቧንቧዎች ግድግዳ መለጠጥ እና መሰርጎድን ተከትሎ የሚከሰት የደም ቧንቧ ግድግዳ መሽንቆር ወይም መቀደድ እና የደም ወደ አንጎል እና ህብለሰረሰር ፈሳሽ ውሰጥ መፍሰስ በሚፈጠርበት ወቅት በማጅራት እና በአንገት   ክፍል  ላይ  የሚፈጠር ህመም (Nuchal rigidity) ወይም አንገት ወደ ደረት በሚታጠፍበት ወቅት በአንገት ላይ የሚፈጠር ህመም ፣ ብርሃንን ማየት መቸገር ወይም ከብረሃን መራቅ (photophobia)፣ በአንድ ግዜ ሁለት ዓይነት አይታ ማየት ( diplopia) ወይም የእይታ ብዥታ መፈጠር ( blurred vision) ፣ የተወሰነ የሰውነት ክፍል መዛል ወይም መታዘዝ አለማቻል ፣ በሰውነት ክፍሎች ላይ የሚከሰትን ለውጥ ወይም ስሜት መረዳት አለመቻል (loss of sensation) ፣ በአንጎል ሴሎች ዕብጠት እና በጭንቅላት ቅል ውስጥ የሚኖረው የግፊት መጠን በከፍተኛ ደረጃ መጨመር የተነሳ የደም ግፊት መጠን መጨመር ፣ የልብ ምት ፍጥነት መቀነስ እና እራስን መሳት ሊከሰት ይችላል። 

በአንጎል ክፍሎች ውስጥ የደም መፍሰስ መከሰቱን ለማወቅ እና አሰፈላጊውን ህክምና በፍጥነት በማገኘት ሊከሰት የሚችውን የከፋ ጉዳተ ወይም የሞት አደጋ ለመቀነስ በአንጎል ክፍሎች ውስጥ የደም መፍሰስን ተከትሎ በበሽተኛው ላይ የሚከሰቱ ምልክቶችን እና ለውጦችን በፍጥነት መለየት በጣም አሰፈላጊ ይሆናል። የኮምዩትድ ቶሞግራፊ (CT) ምርመራ ፣ የኤም አር አይ (MRI) ምርመራ ፣ በአንጎል ውስጥ የሚገኙ የደም ቧንቧዎችን ለማየት የሚረዱ የምርመራመንገዶች (vascular imaging) እንዲሁም በህብለሰረሰር ፈሳሽ (Cerebrospinal fluid / CSF) ላይ የሚድረግ ምርመራ በአንጎል ክፍሎች ውስጥ ከሚፈጠር ደም መፍሰስ ጋር የሚከሰቱ የጤና ችግሮችን ለመለየት የሚረዱ የምርመራ ዓይነቶች ናቸው።

   በአንጎል ውስጥ የሚገኙ የደም ቧንቧዎች ግድግዳ መለጠጥ እና መሰርጎደን ተከትሎ በአንጎል ውስጥ የደም መፍሰስ በሚፈጠርበት ወቅት በፍጥነት የተሸነቆረውን ፣ የተቀደደውን ወይም የፈነዳውን የደም ቧንቧ በመጠገን ፧ በመዝጋት ወይም በመድፈን በተጨማሪነት ሊከሰቱ የሚችሉ የከፉ የጤና ችግሮችን መከላከል አስፈላጊ ሊሆን ይችላል። 

   በአንጎል ውስጥ በሚገኙ የደም ቧንቧዎች ግድግዳ ላይ የሚከሰት መለጠጥ እና መስርጎድን ለማከም ይቻል ዘንድ በአንጎል ውስጥ የሚገኙ የደም ቧንቧዎችን ለማየት የሚረዱ የምርመራ መንገዶችን ወይም የቀዶ ጥገና ህክምና መጠቀም ሊያስፈልግ ይቻላል።

በአንጎል ውስጥ የሚገኙ የደም ቧንቧዎች ግድግዳ መለጠጥ እና መሰርጎድን ተከትሎ በአንጎል ክፍሎች ውስጥ የደም መፍሰስ ከተፈጠረ በኋላ እንደገና በአንጎል ውስጥ የደም መፍሰስ ፣ ከደም መፍሰስ ጋር በተገናኘ በህብለሰረሰር ፈሳሽ ውስጥ ከሚደባለቀው ደም የተነሳ በሌሎች የአንጎል ክፍሎች ውስጥ የሚገኙ የደም ቧንቧዎች መዘጋት እንዲሁም ወደ ሌሎች የአንጎል ክፍሎች የሚደርሰው የደም መጠን መቀነስ ፣ በአንጎል ውስጥ የሚገኘው የህብለሰረሰር ፈሳሽ ፍሰት መዘጋት የተነሳ በአንጎል ውስጥ የሚከማቸው የህብለሰረሰር ፈሳሽ መጠን በከፍተኛ ደረጃ መጨምር (hydrocephalus) ፣ በአይፖታላመስ ዕጢ ላይ የሚከሰት ጉዳት ፣ እንፍርፍሬት እና ሞት ሊከሰት ይቻላል።