23.2. 1. የደም ቧንቧ ግድግዳ ላይ የሚፈጠር ብግነት ዓይነቶች (types of vasculitis)
የደም ቧንቧ ግድግዳ ላይ የሚከሰት ብግነት በሚያጠቃው የደም ቧንቧ መጠን መሠረት በሦስት ዋና ዋና ምድቦች ይከፈላል። እነዚህም የደም ቧንቧ የብግነት ዓይነቶች በትልልቅ የደም ቧንቧዎች ግድግዳ ላይ የሚከሰት ብግነት ፣ መካከለኛ መጠን ባላቸው የደም ቧንቧዎች ግድግዳ ላይ የሚከሰት ብግነት እና በትንንሽ የደም ቧንቧዎች ላይ የሚከሰት ብግነት ናቸው።