Course Content
ምዕራፍ አሥራ አራት : በልብ እና በደም ቧንቧ ሥርዓት አፈጣጠር ሂደት ወቅት የሚፈጠሩ የጤና ችግሮች
0/16
ምዕራፍ አሥራ አምሥት : ከልብ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ ጋር በተገናኘ የሚፈጠሩ የልብ የጤና ችግሮች (Cardiac electrical system abnormalities)
0/16
ምዕራፍ አስራ ሰባት : በልብ በሮች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Valvular heart diseases)
0/16
ምዕራፍ ሃያ አንድ : የልብ ድካምበሽታ (Heart failure )
0/1
ምዕራፍ ሃያ ሦስት : በደም ቧንቧዎች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Vascular diseases)
0/22
በልብ እና በደም ቧንቧ ሥር ዓት ክፍሎች ውስጥ ሊፈጠሪ የሚችሉ የጤና ችግሮች (Pathology of Cardiovascular System)

ለ) የታካያሱ የደም ቧንቧዎች ብግነት በሽታ (Takayasu Arteritis) 

            ይህ የጤና ችግር የትልቁ ደም ቅዳ ቧንቧ እና ከትልቁ ደም ቅዳ ቧንቧ በሚነሱ ቅርንጫፍ አርተሪዎች ግድግዳ ላይ ብግነት ወይም ቁስለት የሚያስከትል የደም ቧንቧ ብግነት በሽታ ዓይነት ነው። የታካያሱ የደም ቧንቧ ብግነት በሽታ የተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ውስጥ የሚገኙ ትልልቅ የደም ቧንቧዎችንም ሊያጠቃ ይችላል። የትልቁ ደም ቅዳ ቧንቧ ከልብ ወደ ተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ደምን የሚያስተላልፍ በሰውነት ውስጥ ከሚገኙ አርተሪዎች ውስጥ በመጠን ትልቁ አርተሪ ነው። የታካያሱ የደም ቧንቧ ብግነት በሽታ መንስሄ በትክክል የሚታወቅ ባይሆንም የሰውነት የበሽታ መከላኪያ ሥርዓት ክፍል ሴሎች እና የበሽታ መከላኪያ ፕሮቲኖች የራስን የሰውነት ክፍል በማጥቃት የደም ቧንቧዎች ግድግዳ ላይ ቁስለት ወይም ብግነት እንዲፈጠር ሊያደርጉ እንደሚችሉ ይታመናል።

      ይህ የጤና ችግር ብዙ ጌዜ የሚከሰተው እድሜያቸው  ከ 40 ዓመት በታች በሚገኙ ሰዎች ላይ ሲሆን በብዛት በኢሲያ፣ በህንድ እና በሚክሲኮ አካባቢ በሚኖሩ ሰዎች ላይ ይታያል። 

  የታካዩሱ የደም ቧንቧ ብግነት በሽታ የደም ቧንቧዎች እንዲጠቡ ፣ እንዲሰፉ ፣ እንዲዘጉ ወይም እንዲሰረጎዱ ሊያደርግ ይችላል። በታካያሱ የደም ቧንቧ ብግነት በሽታ የተጠቁ ሰዎች ላይ ሊታዩ ከሚችሉ ምልክቶች እና ለውጦች መካከል የድካም ስሜት ፣ የሰውነት ሙቀት መጠን መጨመር ወይም ትኩሳት ፣ የሰውነት ክብደት መጠን መቀነስ ፣ በተለያየ የሰውነት ክፍል ላይ የሚሰማ ህመም ፣ እራስ ማዞር ፣ የራስ ምታት ፣ ከላይኛው የሰውነት ክፍል ላይ ብቻ የሚከሰት የደም ግፊት መጠን መጨመር ፣ የግራ መጋባት ስሜት ወይም የአይምሮ መቃወስ ፣ በደረት ላይ የሚሰማ ህመም እና የማየት ችግር የመሳሰሉት ዋንኞቹ ናቸው።