Course Content
ምዕራፍ አሥራ አራት : በልብ እና በደም ቧንቧ ሥርዓት አፈጣጠር ሂደት ወቅት የሚፈጠሩ የጤና ችግሮች
0/16
ምዕራፍ አሥራ አምሥት : ከልብ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ ጋር በተገናኘ የሚፈጠሩ የልብ የጤና ችግሮች (Cardiac electrical system abnormalities)
0/16
ምዕራፍ አስራ ሰባት : በልብ በሮች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Valvular heart diseases)
0/16
ምዕራፍ ሃያ አንድ : የልብ ድካምበሽታ (Heart failure )
0/1
ምዕራፍ ሃያ ሦስት : በደም ቧንቧዎች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Vascular diseases)
0/22
በልብ እና በደም ቧንቧ ሥር ዓት ክፍሎች ውስጥ ሊፈጠሪ የሚችሉ የጤና ችግሮች (Pathology of Cardiovascular System)

ለ) ከኢኦዚኖፊሊክ ጋር ግራኖሎማ የሚሰራ የደም ቧንቧ ብግነት (Eosinophilic Granulomatosis with Polyangiitis)

ይህ የጤና ችግር በተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ውስጥ በሚገኙ በመጠን ትንንሽ  የሆኑ የደም ቧንቧዎች ግድግዳ ላይ ብግነት ወይም ቁስለት እንዲፈጠር የሚያደርግ በሽታ ነው። ከኢኦዚኖፊሊክ ጋር ግራኖሎማ የሚሰራ የደም ቧንቧ ብግነት በሽታ ከሚገለጽባቸው ሆኔታዎች መካከል የአፍንጫ አለርጂ ( ከአፍንጫ የሚወጣ ፈሳሽ ፧ የአፍንጫ መታፈን እንዲሁም በተደጋጋሚ ማስነጠስ እና በአፍንጫ ውሰጥ ማሳከክ ወይም የመቆጥቆጥ ስሜት መሰማት) ፣ በቆዳ ላይ የሚታይ ሽፍታ ወይም ችፍታ ፣ የአስም በሽታ ፣ በሰውነት ላይ አለረጂ ለሚያስነሱ ነገሮች (Allergen) ሲጋለጡ ወይም ሰውነት በሆድ ውስጥ በሚፈጠሩ ትላትሎች (parasites) ሲጠቃ የኢኦዚኖፊሊክ የነጭ ደም ሴሎች መጠን  በከፍተኛ ደረጃ መጨመር ዋንኞቹ ናቸው። 

   ከኢኦዚኖፊሊክ ጋር ግራኖሎማ የሚሰራ የደም ቧንቧ ብግነት በተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ውስጥ የሚገኙ ትንንሽ የደም ቧንቧዎች ግድግዳ ላይ ብግነት ወይም ቁስለት እንዲፈጠር ሊያደርግ የሚችል ሲሆን በተለይም በሳንባ ፣ በአንጀት ፣ በቆዳ ፣ በልብ እና በነርቭ ሥርዓት ውስጥ በሚገኙ የደም ቧንቧዎችን በተለየ ሆኔታ ሊያጠቃ ይችላል። በተጨማሪም በሽታው በነርቭ ሥርዓት እንዲሁም በልብ እና በደም ቧንቧ ሥርዓት ተግባር ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል። እድሜያቸው በ 50 ዎቹ የእድሜ ክልል ወስጥ የሚገኙ ሰዎችን በብዛት የሚያጠቃ ሲሆን የበሽታው መነስሄ በትክክል አይታወቅም። የሰውነት የበሽታ መከላኪያ ሥርዓት በራሱ የሰውነት ክፍል ላይ በሚያደርሰው ጉዳት የተነሳ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል።

  ከኢኦዚኖፊሊክ ሴሎች ጋር ግራኖሎማ በሚሰራ የደም ቧንቧ ብግነት በሽታ በተጠቁ በሽተኞች ላይ የሚከሰቱ ምልክቶች እና ለውጦች ጉዳት በደረሰበት የደም ቧንቧ በኩል  ደም በሚደርሰው የሰውነት ክፍል ዓይነት ይለያያል። ከበሽታው ጋር በተገናኘ ሊከሰቱ ከሚችሉ ምልክቶች መካከል የስውነት ሙቀት መጠን መጨመር ወይም ትኩሳት ፣ አጠቃላይ የሆነ የድካም ሰሜት መሰማት ፣ የክብደት መጠን  መቀነስ፣ በጡንቻዎች እና በአጥንት መገጣጠሚያ ክፍሎች ውስጥ የሚሰማ ህመም ፣ በእጅ እና በእግር ጣቶች ላይ የሚከስት መደንዘዝ እንዲሁም በመርፌ የመወጋት የሚመስል ህመም ፣ የደረት ህመም እና የልብ ምት መሰማት፣ የትንፋሽ ማጠር ፣ ሳል እና የአየር ማጠር ፣ በደም ቧንቧዎች ውስጥ የሚፈጠር የደም መርጋት ፣ የሆድ ህመም እና ደም የቀላቀለ አይነ ምድር መታየት ዋንኞቹ ናቸው።

   ከኢኦዚኖፊሊክ ሴሎች ጋር ግራኖሎማ በሚሰራ የደም ቧንቧ ብግነት በሽታ በተጠቁ በሽተኞች ላይ የሚታዩ ምልክቶችን እና ለውጦችን በመለየት ፣ አካላዊ ምርመራ በማድረግ ፣ በላብራቶሪ ምርመራ እና በበሽታው ከተጠቁ የሰውነት ክፍሎች ላይ በሚወሰድ ናሙና ላይ በሚደረግ የፓቶሎጂ ምርመራ በሽታው መከሰቱን መለየት ይቻላል። በተለይም ከደም ምርመራ የሚገኘው ጸረ ኒዩክለስ  ሳይቶፕላዝሚክ አንቲቦዲ ( anti nuclear cytoplasmic antibodies / ANCA) በሽታውን በትክክል በመለየት ረገድ የሚኖረው ሚና ከፍተኛ ነው። 

     የሰውነት በሽታ መከላኪያ አቅምን የሚቀንሱ መድኃኒቶችን በመጠቀም ከበሽታው ጋር በተገናኘ  የሚከሰቱ ምልክቶችን እና ለውጦችን መቆጣጠር ወይም በሽታውን ማከም ይችላል።