Course Content
ምዕራፍ አሥራ አራት : በልብ እና በደም ቧንቧ ሥርዓት አፈጣጠር ሂደት ወቅት የሚፈጠሩ የጤና ችግሮች
0/16
ምዕራፍ አሥራ አምሥት : ከልብ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ ጋር በተገናኘ የሚፈጠሩ የልብ የጤና ችግሮች (Cardiac electrical system abnormalities)
0/16
ምዕራፍ አስራ ሰባት : በልብ በሮች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Valvular heart diseases)
0/16
ምዕራፍ ሃያ አንድ : የልብ ድካምበሽታ (Heart failure )
0/1
ምዕራፍ ሃያ ሦስት : በደም ቧንቧዎች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Vascular diseases)
0/22
በልብ እና በደም ቧንቧ ሥር ዓት ክፍሎች ውስጥ ሊፈጠሪ የሚችሉ የጤና ችግሮች (Pathology of Cardiovascular System)

ሐ) የራይናውድ በሽታ (Raynaud’s disease) 

     ይህ የጤና ችግር በእጅ እና በእግር ጣቶች ላይ የሚገኙ በጣም ትንንሽ የደም ቧንቧዎች ግድግዳ ላይ ቁስለት ወይም ብግነት እንዲከሰት የሚያደርግ በሽታ ነው። የራይናውድ በሽታ ሰውነት ለቀዝቃዛ የአየር ሆኔታ በሚጋለጥበት ውቅት ወይም በሽተኛው ለከፍተኛ ጭንቀት በሚጋለጥበት ወቅት በደም ቧንቧ ግዳግዳ ላይ የሚገኙ ጡንቻዎች እንዲኮማተሩ እና እንዲጠቡ በማድረግ የደም ፍስትን በመቀነስ የእጅ እና የእግር ጣት ጫፎች ቀለም መቀየርን ወይም መንጣት እና መገርጣትን ያስከትላል። 

 ከእጅ እና ከእግር ጣቶች በተጨማሪ በአፍንጫ ፣ በጆሮ ፣ በጡት ጫፍ እና በከንፍር ላይ ሊከሰት ይቻላል። ይህ በሽታ በቀዝቃዛ አካባቢ የሚኖሩ ሰዎች ላይ በብዛት የሚከሰት ሲሆን በተለይም እድሜያቸው ከ 30 አመት በላይ በሚሆኑ ሴቶች ላይ በብዛት ይታያል።  ከራይናውድ በሽታ ጋር በተገናኘ የሚፈጠረው የደም ቧንቧ መጥበብ ወይም መዘጋት ለረጅም ጊዜ በሚቆይበት ወቅት በጣቶች ላይ በሚፈጠረው የደም ፍሰት መቋርጥ የተነሳ ለሴሎች መሞት እና ለጣት መቆረጥ ምክንያት ሊሆን ይችላል። 

  ሁለት ዓይነት የራይናውድ የጤና ችግሮች አሉ። እነዚህም የራይናውድ በሽታ (Raynaud disease) እና የራይናውድ ክስተት (Raynaud phenomenon) ተብለው ይታወቃሉ። 

    የራይናውድ በሽታ መንስሄው በትክክል የማይታወቅ ሲሆን ከራይናውድ ክስተት ጋር ሲነጻጸር የሚገለጽበት ሆኔታ ወይም የሚያስከትለው ጉዳት በጣም ዝቅተኛ ነው። የራይናውድ ክስተት ትክክለኛው መንስሄው የማይታወቅ ሲሆን  ከሌሎች የጤና ችግሮች ጋር በተገናኘ የሚከሰት የጤና ችግር ነው። የራይናውድ ክስተትን ከሚያስከትሉ የጤና ችግሮች መካከል በደም ቧንቧዎች ግድግዳ ላይ የሚፈጠር ብግነት ፣ በእጅ እና በእግር ላይ በሚገኙ የደም ቧንቧዎች ላይ ተጽህኖ በሚያሳድሩ ነርቮች ላይ የሚከሰት ጉዳት ፣ ለተለያዩ ኬሚካሎች መጋለጥ እንዲሁም የደም ቧንቧዎች እንዲጠቡ የሚያደርጉ መድኃኒቶች ዋንኞቹ ናቸው። በሁለቱም ዓይነት ሆኔታዎች ላይ በሽተኛው ለቀዝቃዛ አየር እና ጭንቀት ሲጋልጥ የደም ቧንቧዎች መጥበብ ይከሰታል።

   በበሽተኛው ላይ የሚከሰቱ ምልክቶች እና ለውጦች ታሪክ ፣  የአካላዊ ምርመራ ፣ ሰውነት ለቅዝቃዜ እንዲጋለጥ በማድረግ የሚደረግ ምርመራ (cold stimulation test) እንዲሁም በጣት ጥፍር ላይ በሚደረግ ምርመራ የካፒላሪሶች የደም ቧንቧዎችን የመመልከት ምርመራ (nailfold capillaroscopy) በማድረግ በሽታውን ለማወቅ ይቻላል።