Course Content
ምዕራፍ አሥራ አራት : በልብ እና በደም ቧንቧ ሥርዓት አፈጣጠር ሂደት ወቅት የሚፈጠሩ የጤና ችግሮች
0/16
ምዕራፍ አሥራ አምሥት : ከልብ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ ጋር በተገናኘ የሚፈጠሩ የልብ የጤና ችግሮች (Cardiac electrical system abnormalities)
0/16
ምዕራፍ አስራ ሰባት : በልብ በሮች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Valvular heart diseases)
0/16
ምዕራፍ ሃያ አንድ : የልብ ድካምበሽታ (Heart failure )
0/1
ምዕራፍ ሃያ ሦስት : በደም ቧንቧዎች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Vascular diseases)
0/22
በልብ እና በደም ቧንቧ ሥር ዓት ክፍሎች ውስጥ ሊፈጠሪ የሚችሉ የጤና ችግሮች (Pathology of Cardiovascular System)

14.1. የቆዳ ቀለም ለውጥ የማያስከትሉ በልብ እና የደም ቧንቧ ሥርዓት አፈጣጠር ወቅት የሚፈጠሩ የጤና ችግሮች (non cyanotic congenital heart diseases)

   የቆዳ ቀለም ለውጥ የማያስከትሉ በልብ እና በደም ቧንቧ ሥርዓት አፈጣጠር ወቅት የሚፈጠሩ የጤና ችግሮች በቀኝ እና በግራ አትሪየም ወይም በቀኝ እና በግራ ቬንትሪክል መካከል በሚገኘው ግድግዳ አፍጣጠር ወቅት በሚፈጠሩ የአሰራር እክሎች ፣ በልብ በሮች ወይም በትልልቅ የደም ቧንቧዎች አፈጣጠር ወቅት ከሚፈጠሩ እክሎች ወይም ጉድለቶች እንዲሁም ከቀኝ የልብ ክፍል እና ከግራ የልብ ከፍል በሚነሱ የደም ቧንቧዎች መካከል ከሚፈጠር ተገቢ ያልሆነ ግንኙነት የተነሳ ሊከሰቱ ይችላሉ።

   የቆዳ ቀለም ለውጥ የማያስከትሉ በልብ እና በደም ቧንቧ ሥርዓት አፈጣጠር ወቅት የሚፈጠሩ የጤና ችግሮች እንዲከሰቱ ሊያደርጉ ከሚችሉ ሆኔታዎች መካከል በክሮምዞም ወይም ጂን ላይ የሚከሰቱ ለውጦች ( የዳውን ሲንድሮም (down syndrome) እና የተርነር ሲንድሮም (turner syndrome)) ፣ በአርግዝና ውቅት በእናትየው እና በፅንሱ ላይ የሚከሰቱ የተለያዩ ኢንፌክሽኖች (የጀርመን ኩፍኝ ኢንፌክሽን (Rubella infection) እና ሌሎች የተለያዩ በግብረሥጋ ግንኙነት የሚተላለፉ እና ወደ ፅንሱ መተላለፍ የሚችሉ ኢንፊክሽኖች) ፣ በእናትየው ላይ የሚፈጠሩ የጤና ችግሮች ( የስኳር በሽታ ) በአርግዝና ወቅት እናትየው የምትወስዳቸው መድኃኒቶች እና የአልኮል መጠጥ ዋንኞቹ  ናቸው።

 የቆዳ ቀለም ለውጥ የማያስከትሉ በልብ እና በደም ቧንቧ አፈጣጠር ወቅት የሚፈጠሩ የጤና ችግሮች ደም ከግራ የልብ ክፍል ወደ ቀኝ የልብ ክፍል (left to right shunt) እንዲገባ ያደርጋሉ።  በዚህም የተጣራው ደም ካልተጣራው ደም ጋር እንዲደባለቅ በማድረግ በቀኝ የልብ ክፍሎች ውስጥ የሚኖረው የደም መጠን እና የግፊት መጠን እንዲጨምር ያደራጋል። ይህም ሆኔታ የቀኝ ቬንትሪክል እንዲወፍር እና በፑልሞናሪ አርተሪ ውስጥ የሚኖረው የግፊት መጠንም እንዲጨምር ሊያደርግ ይችለል።  

  የቆዳ ቀለም ለውጥ የማያስከትሉ በልብ እና የደም ቧንቧ ሥርዓት አፈጣጠር ወቅት የሚፈጠሩ የጤና ችግሮች የሚያስከትሏቸው ምልክቶች እና ለውጦች በተፈጠረው የጤና ችግር ዓይነት እና ደረጃ ላይ በመመስረት የሚለያይ ቢሆንም አብዛኛዎቹ ህጻናት እንደተወለዱ ምንም ዓይነት ምልክትም ሆነ ለውጦችን የማያሳዩ ሲሆን አያደጉ በሚመጡበት ወቅት እንቅስቃሴን ሲያደርጉ የሚከሰት የድካም ስሜት ፣ የእድገት መቀጨጭ እና የልብ ድካም ምልክቶችን እና ለውጦችን ሊያሳዩ ይችላሉ። 

  በግራ የልብ ክፍል ውስጥ የሚገኘው የተጣራ ደም ወደ ቀኝ የልብ ክፍል ውስጥ መግባት በደም ውስጥ የሚገኘውን የኦክስጂን መጠን እንዲቀንስ አያደርገውም። ምክንያቱም ከግራ የልብ ክፍል ወደ ቀኝ የልብ ከፍል የሚገባው የተጣራ ደም በቀኝ የልብ ክፍል ውስጥ ከሚገኘው ያልተጠራ ደም ጋር ከተቀላቀለ በኋላም መልሶ በሳንባ በኩል አለፎ እንደገና ይጣራል። በዚህ የጤና ችግር የተጠቁ ህጻናት እንደ ተወለዱ ምንም ዓይነት የቆዳ ቀለም መለውጥ የማያሳዩ ሲሆን ከጤና ችግሩ ጋር በተገናኘ የሚከሰቱ ምልክቶች እና ለወጦች የሚታዩት ከተወለዱ ከረጅም ጊዜ በኋላ ሊሆን ይችላል።

  የቆዳ ቀለም ለውጥ የማያሰከትሉ በልብ እና የደም ቧንቧ ሥርዓት አፈጣጠር ወቅት ከሚፈጠሩ የጤና ችግሮች  ጋር በተገናኘ ሊከሰቱ ከሚችሉ ምልክቶች እና ለውጦች መካከል በቆዳ ላይ የቀለም ለውጥ አለመታየት ፣ ህጻናቱ እንቅስቃሴ በሚያደርጉበት ወቅት የሚፈጠር የትንፋሽ ማጠር ፣ አጠቃቃላይ የሆነ የድካም ስሜት መስማት ፣ በክፍተኛ ላብ መጠመቅ ፣ የፊት ቆዳ መግርጣት ፣ የልብ ምት ፍጥነት መጨመር ፣ ማቃሰት እና ባልተገባ መልኩ የጭንቅላት መወዛወዝ ዋንኞቹ ናቸው።

      በተጨማሪም የዕድገት መቀጨጭ ፣ በተደጋጋሚ በልብ እና በሳንባ ውስጥ የሚፈጠር ኢንፌክሽን እና የልብ ድካም በሽታ ሊፈጠር ይችላል። ከሚፈጠረው የልብ ድካም በሽታ ጋር በተገናኘም በሆድ ፣ በጉበት እና በእግር ውስጥ የሚፈጠር የፈሳሽ መጠራቀም ወይም የሰውነት እብጠት ፣ ቶሎ ቶሎ መተንፈስ ፣ የደም ግፊት መጠን መቀነስ ፣ እራስን መሳት ፣ በላብ መጠመቅ እና የሰውነት ወይም የቆዳ መቀዝቀዝ ሊከሰት ይችላል። 

  በአካላዊ ምርመራ እና የተለያዩ የመመርመሪያ መሳሪያዎችን በመጠቀም በልብ እና የደም ቧንቧ ሥርዓት አፈጣጠር ወቅት የሚፈጠረ የጤና ችግር መከሰቱን ማውቅ የሚቻል ሲሆን ከእነዚህም የምርመራ መንገዶች መካከል የደረት ራጅ (CXR) ፣ የኢኮካርዲዮግራም ( echo) ፣ የኤሌክትሮከርዲዮግራም (ECG)  ፣ የ ኤም አር አይ (MRI) እና የካርዲያክ ካቴተራይዜሽን ምርመራ (cardiac Catheterization)  እና የኮምፒዩትድ ቶሞግራፊ (CT) የምርመራ መንገዶች ዋንኞቹ ናቸው።

   የቆዳ ቀለም ለውጥ የማያሰከትሉ በልብ እና የደም ቧንቧ ሥርዓት አፈጣጠር ወቅት የሚፈጠሩ የጤና ችግሮችን  ለማከም ወይም የሚከሰቱ ምልክቶችን እና ለውጦችን ለመቆጣጠር በደም ውስጥ የሚፈጠርውን የኦክስጂን መጠን ለማስተካከል የሚረዳ በቂ የሆነ ኦክስጂን ፣ በፅንሱ  የደም ዝውውር ሂደት ውስጥ በልብ እና በደም ቧንቧ ሥርዓት ውስጥ የሚገኙ ማሻገሪያ ወይም የደክተስ አርተሪኦሰስ ማሻገሪያ እንደተከፈተ እንዲቆይ የሚያደርጉ መድኃኒቶችን (የፕሮስታግላንዲን ሆርሞንን በመድኃኒት  መልክ መጠቀም ) ፣ የፑልሞናሪ አርተሪ ቧንቧዎች እና ሌሎች የደም ቧንቧዎች እንዲስፉ የሚረዱ መድኃኒቶችን መጠቀም ፣ በሰውነት ውስጥ የሚገኘውን የፈሳሽ መጠን ለመቀነስ የሚረዱ መድኃኒቶችን (diuretics) መጠቀም ፣ የልብ የመኮማተር አቅምን የሚጨመሩ መድኃኒቶችን (የዲጆክሲን መድኃኒት) መጠቀም ፣ በልብ እና በሳንባ ውስጥ የሚከሰቱ ኢንፌክሽኖችን ለመከላከል የሚረዱ ጸረ ባክቲሪያ መድኃኒቶችን መጠቀም እንዲሁም ደረትን በመክፍት የሚሰራ የልብ እና የደም ቧንቧ ቀዶ ጥገና ህክምና ወይም  የካርዲያክ ካቴተራይዜሸን ምረመራ እና ህክምና ማድረግ አስፈላጊ ሊሆን ይችላል። 

     የተለያዩ የምርመራ እና የህክምና መንገዶችን በመጠቀም በልብ እና በደም ቧንቧዎቸ ሥርዓት አፈጣጠር ወቅት የሚፈጠሩ የጤና ችግርን ወይም ጉዳቶችን መለየት እንዲሁም ለተፈጠረው የጤና ችግር ወይም ጉዳት ተገቢውን ህክምና መስጠት በጣም አሰፈላጊ ይሆናል። በልብ አና የደም ቧንቧ ሥርዓት አፈጣጠር ወቅት ለሚፈጠሩ የጤና ችግሮች በተገቢው ግዜ ውስጥ እና መንገድ ህክምና መስጠት በማይቻልበት ወቅት ለዕድገት መቀጨጭ ፣ ለልብ ምት መዛባት ፣ በልብ ውስጥ ለሚፈጠር የደም መርጋት ፣ በልብ ውሰጥ የሚፈጠረው የደም መርጋት ወደ ተለያዩ የደም ቧንቧዎች ውስጥ መሰራጨት እና የደም ቧንቧዎችን በተለይም በአንጎል እና በልብ ውሰጥ የሚገኙ የደም ቧንቧዎች) መዝጋት (embolism) ፣ በተደጋጋሚ በልብ ውስጥ ለሚፈጠር እንፌክሽን (infective endocarditis) እንዲሁም በድንገት ለሚከሰት የሞት አደጋ ተጋላጭነት እንዲጨምር ሊያደርግ ይችላል።

   ይህን ዓይነት በልብ እና የደም ቧንቧ ሥርዓት አፈጣጠር ሂደት ወቅት የሚፈጠር የጤና ችግር እንዲከሰት ከሚያደርጉ ሆኔታዎች መካከል በግራ እና በቀኝ ቬንትሪክል መካከል የሚገኘው ግድግዳ ወይም የቬንትሪክል ሴፕተም መሽንቆር (ventricular septal defect / VSD) ፣ በግራ እና በቀኝ አትሪየም መካከል የሚገኘው ግድግዳ ወይም የአትሪየም ሴፕተም መሸንቆር (atrial septal defect / ASD) ፣ የደክተስ  አርትሪኦሰስ ማሻገሪያ ወይም ቅያሽ እንደተከፈተ መቅረት ወይም አለመዘጋት (Persistent Ductus Arteriosus / PDA) እንዲሁም የትልቁ ደም ቅዳ ቧንቧ መጥበብ (coarctation of the aorta) ዋንኞቹ የቆዳ ቀለም ለውጥ የማያሰከትሉ በልብ እና የደም ቧንቧ ሥርዓት አፈጣጠር ወቅት ሊፈጠሩ የሚችሉ የልብ እና የደም ቧንቧ ሥርዓት የጤና ችግሮች ናቸው።