Course Content
ምዕራፍ አሥራ አራት : በልብ እና በደም ቧንቧ ሥርዓት አፈጣጠር ሂደት ወቅት የሚፈጠሩ የጤና ችግሮች
0/16
ምዕራፍ አሥራ አምሥት : ከልብ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ ጋር በተገናኘ የሚፈጠሩ የልብ የጤና ችግሮች (Cardiac electrical system abnormalities)
0/16
ምዕራፍ አስራ ሰባት : በልብ በሮች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Valvular heart diseases)
0/16
ምዕራፍ ሃያ አንድ : የልብ ድካምበሽታ (Heart failure )
0/1
ምዕራፍ ሃያ ሦስት : በደም ቧንቧዎች ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች (Vascular diseases)
0/22
በልብ እና በደም ቧንቧ ሥር ዓት ክፍሎች ውስጥ ሊፈጠሪ የሚችሉ የጤና ችግሮች (Pathology of Cardiovascular System)

23.1 ደምን ወደ አንጎል በሚያደርሱ የደም ቧንቧዎች ላይ በሚፈጠር ጉዳት የተነሳ የሚከሰት የጤና ችግር (Cerebrovascular accidents) 

  የተለያዩ የአንጎል ክፍሎች ደምን የሚያገኙት በተለያየ አቅጣጫ ወደ ጭንቅላት ውስጥ በሚገቡ በሁለት የተለያዩ የደም ቧንቧዎች በኩል ነው። እነዚህም ሁለት የደም ቧንቧዎች በፊተኛው የአንጎል ክፍል ውስጥ ለሚገኙ የአንጎል ክፍሎች ደም እንዲደርስ በሚያደርጉት የቀኝ እና የግራ የውስጠኛው ካሮቲድ አርተሪዎች ( internal carotid arteries) እና በኋለኛው የአንጎል ክፍል ውስጥ ለሚገኙ የአንጎል ክፍሎች ደም እንዲደርስ በሚያደርጉት በቀኝ እና በግራ ቨርቴብራል አርተሪዎች (vertebral arteries) በኩል ነው። 

   የካሮቲድ አርተሪዎች ወደተለያዩ ቅርንጫፍ የደም ቧንቧዎች በመከፋፈል ለለፊተኛውን የአንጎል ክፍል (frontal lobe) ፣ ለፓራይታል የአንጎል ክፍል (parietal lobe) ፣ ለለቴምፖራል የአንጎል ክፍል (temporal lobe) ፣ ለባዛል ጋንግሊያ የአንጎል ክፍል (basal ganglia) ፣ ለታላመስ (thalamus) እና ለአይፖታላመስ (hypothalamus) የአንጎል ክፍሎች ደም እንዲደረሳቸው የሚያደርጉ የደም ቧንቧዎች ናቸው።

     የቀኝ እና የግራ የቨርቴብራል አርተሪዎች ወደ ጭንቅላት ቅል ውስጥ ከገቡ በኋላ አንድ ላይ በመገናኘት የባዜላር አርተሪን (basilar artery) ይፈጥራሉ። የባዚላር አርተሪ ከፈጠረ በኋላ ወደ ተለያዩ ቅርነጫፍ የደም ቧንቧዎችን በመከፋፈል በኋለኛው የአንጎል ክፍል ውስጥ ለሚገኙት ለመካከለኛው እና የታችኛው ቴምፖራል የአንጎል ክፍል ፣ ለኃለኛው occipital የአንጎል ክፍል ( occipital lobe) ፣ ለሴረበለም የአንጎል ክፍል  (cerebellum) እና ለዋና የአንጎል ግንድ ክፍል (brain stem) ደም እንዲደርስ የሚያደርጉ የደም ቧንቧዎች ናቸው። ዋና የአንጎል ግንድ ክፍል (brain stem) በውስጡ የሚዶላ ኦብሎንጋታ ( medulla oblongata) ፣ የፖንስ (pones) እና የመካከኛው የአንጎል ክፍል (midbrain) ክፍሎችን የያዘ ወሳኝ የአንጎል ክፍል ነው።  

      የቀኝ እና የግራ የውስጠኛው የካሮቲድ አርተሪዎች እያንድ አንዳቸው ወደ መካከለኛ የሲረበራል አርተሪ ( middle cerebral artery) እና ወደ ፊተኛው ሲረበራል አርተሪዎች ( anterior cerebral artery) በመከፋፈል በአጠቃላይ የፊተኛው እና በጎን በኩል የሚገኘው የአንጎል ክፍል ደም አንዲያገኝ ያደርጋሉ። በተጨማሪም የቀኝ እና የግራ የፊተኛው ሲረበራል አርተሪዎች በፊተኛው የእንጎል ክፍል ውስጥ የሚገናኙ ይሆናል።

    የባዜላር አርተሪ ደግሞ ወደ ኋለኛው የሴርበራል አርተሪ (posterior cerebral artery) ፣ የላይኛው የሴሪብለም አርተሪ ( superior cerebellar artery) ፣ የፊት ለፊት የታችኛው የሴረበለም አርተሪ ( anterior inferior cerebellar artery) ፣ የኋለኛው የታኛው የሴረበለም አርተሪ ( posterior inferior cerebellar artery) እና ወደ ሌሎች የተለያዩ ትንንሽ የደም ቧንቧዎች በመከፋፈል ለአንጎል የተለያዩ ክፍሎች ደም ያሚያደርሱ ይሆናል።

   በአጠቃላይ ለፊተኛው እና ለኋለኛው የአንጎል ክፍሎች ደም እንዲደርስ የሚያደርጉ የደም ቧንቧዎች በአንጎል የወስጠኛ ክፍል ውስጥ አንድ ላይ ወይም እርስ በእርስ በመገናኘት እና የክብ ቅርጽ ያለው የደ ቧንቧዎች ግንኙነት (Circle of Willis) በመፍጠር እንዲሁም በተለያየ መጠን እና እቅጣጫ በመከፋፈል ሁሉም የአንጎል ክፍሎች ደም በበቂ መጠን እንዲያገኙ ያደርጋሉ።

   እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ለአንጎል የተለያዩ ክፍሎች ደምን የሚያደርሱ የደም ቧንቧዎች በተለያየ ምክንያት በሚጉዱበት ፣ በሚጠቡበት ፣ በሚዘጉበት እንዲሁም በሚፈነዱበት ወይም በሚቀደዱበት ወቅት ወደ ተለያዩ የአንጎል ክፍሎች የሚደረስው የደም መጠን ስለሚቀንስ ጉዳት በደረሰበት የደም ቧንቧ ዓይነት እና በደረሰው የጉዳት አይነት እና ደረጃ መጠን መሰረት በአንጎል ተግባር ላይ እክል የሚፍጠር ይሆናል። ከላይ በተገለፀው መልኩ ደምን ወደ አንጎል በሚያደርሱ የደም ቧንቧዎች ላይ ከሚከሰት ጉዳት የተነሳ በአንጎል ክፍሎች ላይ የሚፈጠር የአንጎል የጤና ችግር በአንጎል የደም ቧንቧዎች ላይ በሚፈጠር ጉዳት የተነሳ በነርቭ ሥርዓት ላይ የሚከሰት የጤና ችግር ወይም ስትሮክ (stroke) ተበሎ ይጠራል። 

  ደምን ወደ አንጎል በሚያደርሱ የደም ቧንቧዎች ላይ ሊከሰቱ ከሚችሉ ጉዳቶች መካከል ዋንኞቹ ደምን ወደ አንጎል በሚያደርሱ የደም ቧንቧዎች  ግደግዳ ላይ የሚከሰት የኮሌስትሮል ክምችት ( atherosclerosis) ፣ ከእድሜ ጋር በተገናኘ በአርተሪዎች ግድግዳ ላይ የሚፈጠር የካልሲየም መከማቸት እና የአርተሪዎች ግድግዳ መጠንከር (arteriosclerosis) ፣ በሌላ የሰውነት ክፍሎች ውስጥ በሚገኝ የደም ቧንቧ ግድግዳ ላይ  የሚፈጠር የስብ ክምችት ከተጣበቀበት የደም ቧንቧ ላይ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል በመላቀቅ በአንጎል ወሰጥ በሚገኙ የደም ቧንቧዎች  ውስጥ በመሰንቀር የደም ፍሰትን መዝጋት (embolism) ፣  በአንጎል ወሰጥ በሚገኙ የደም ቧንቧ ግድግዳ ላይ የሚፈጠር የስብ ክምችት ከተጣበቀበት ግድግዳ ላይ በከፊል በሚለቃቅበት የግድግዳው ክፍል ላይ የደም መርጋት መፈጠር ወይም ትሮምቦሲስ (thrombosis) ፣ በአንጎል ወሰጥ የሚገኝ የደም ቧንቧ ግድግዳ መሽንቆር ወይም መፈንዳት  እና ደም መፍሰስ (rupture) ፣ በአንጎል ወስጥ የሚገኘ የደም ቧንቧ ግድግዳ መሳሳት ፣ መለጠጥ እና መሰርጎድ (aneurysm) እንዲሁም በአንጎል ወስጥ በሚገኝ የደም ቧንቧ ግደግዳ ላይ የሚፈጠር ብግነት ( vasculitis) ዋንኞቹ ናቸው።

  ከለይ በተገለፁት ምክንያቶች የተነሳ ደምን ወደ አንጎል በሚያደርሱ የደም ቧንቧዎች ላይ የሚፈጠር ጉዳት ወደ አንጎል ክፍሎች የሚደርሰውን የደም ፍሰት በማሰተጓጉል ወይም ወደ አንጎል ክፍሎች የሚደርሰውን የደም መጠን በመቀነስ በአንጎል የደም ቧንቧዎች ላይ በሚፈጠር ጉዳት የተነሳ በነርቭ ሥርዓት ላይ የሚከሰት የጤና ችግር ወይም  ስትሮክ (stroke) እንዲፈጠር ሊያደርጉ ይችላሉ። 

     በአንጎል የደም ቧንቧዎች ላይ በሚፈጠር ጉዳት የተነሳ በአንጎል ወይም በነርቭ ሥርዓት ላይ የሚከሰት የጤና ችግር ወይም ስትሮክ የሚከሰተው በዋናነት በሁለት ምክንያቶች ናቸው። እነዚህም ደምን ወደ አንጎል ክፍሎች በሚያደርሱ የደም ቧንቧዎች መጥበብ ወይም መዘጋት የተነሳ የሚፈጠር ስትሮክ (ischemic stroke) እና ደምን ወደ አንጎል ክፍለ‍ኦች በሚያደርሱ የደም ቧንቧዎች ላይ በሚፈጠር መሽንቆር ፣ መፈንዳት ፣ መቀደድ ወይም የደም መፍሰስ የተነሳ የሚፈጠር ስትሮክ (hemorrhagic stroke) ናቸው።